Posts

አራት የደቡብ ክልል ውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አራቱ የደቡብ ክልል ውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ከፍተኛ ሀላፊዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኙ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡ የክልሉ ውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊው አቶ ውብሸት ፀጋዬ፣ የግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሀላፊው አቶ ይገረሙ ፋሲቆ፣ የክፍያዎች ሀላፊው አቶ አቦሰጥ መብራቱ፣ መሐንዲሱ አቶ ሞገስ ዩሀንስ እና ኮንትራክተር የነበሩት አቶ ተክለወልድ ማሞ በቁጥጥር ስር የሚገኙ ሀላፊዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡ አራቱ ባለስልጣናት በጋራ በመሆን በሲዳማ ዞን በበንሳ ወረዳ በመካሄድ ላይ በነበረ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከፍተኛ የሆነን ገንዘብ ለግል ጥቅም በማዋል በሚል መታሰራቸው ተገልጿል፡፡ ባለፈው ወር አስራ አራት የሚሆኑ የኦሮሚያ ውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ከሙስና ጋር በተያያዘ መታሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በተያያዘ ዜና ከታሰሩ ዘጠና ቀናት የሞላቸው የኢትዮጵያ ጉምሩክና ገቢዎች ባለስልጣናት በመጪዎቹ አስራ አምስት ቀናት ክስ እንደሚመሰረትባቸው ታወቀ፡፡ የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ዋና ሀላፊ አቶ መላኩ ፈንታና ስልሳ ሶስት የጉምሩክ ሀላፊዎች በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በምርመራ ላይ የሚገኙ ሲሆን ምርመራቸው በመጠናቀቁ ክስ ማሰማት ሂደቱ  በሁለት ሳምንት ውስጥ እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡ የኢንተር ኮንቲኔታል ባለቤት አቶ ስማቸው ከበደ፣ የአቶ ስዬ አብርሃ ወንድም የሆኑት አቶ ምህረተአብ አብርሃ እና የበርካታ የንግድ ድርጅቶች ባለቤት የሆኑት አቶ ከተማ ከበደ በቁጥጥር ስር ከሚገኙት 63 ሰዎች መካከል ናቸው፡፡ http://ethsat.com/amharic/%E1%8A%A0%E1%88%AB%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%8B%B0%E1%89%A1%

የደቡብ ክልል ውሃ ሃብት ልማት ቢሮ ከፍተኛ ሃላፊዎች ላይ ምርመራ ተጀመረ ;የክልሉ መንግስት በሲዳማ ዞን በበንሳ ወረዳ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሁሮ ጡሙሮ የተሰኘ የውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ያስጀምራል። ጨረታውን ደግሞ አቶ ተክለወልድ ማሞ የተሰኙ የውሃ ስራዎች ተቋራጭ ያሸንፋሉ ግለሰቦቹ 40 በመቶ ብቻ የተከናወነውን ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል በማለት ያለ አግባብ ክፍያ እንዲፈጸም በማድረጋቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

Image
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ውሃ ሃብት ልማት ቢሮ  ምክትል ሃላፊ አቶ ውብሸት ጸጋዬን ጨምሮ አራት የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ተጀመረባቸው። በደቡብ ክልል  ሰሞኑን የክልሉ ውሃ ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊው አቶ ውብሸት ጸጋዬ ፣ የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሃላፊው  ይገረመው ፋሲቆ ፣  የክፍያዎች ሃላፊው አቶ አቦሰጥ መብራቱ ፣ መሃንዲሱ አቶ ማገሳ ዮሃንስ እና ኮንትራክተሩ አቶ ተክለወልድ ማሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል። የክልሉ ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን  ኮሚሽነር ገበየሁ ገብሬ እንዳሉት ፥ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በመተባበር የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው።  የክልሉ መንግስት በሲዳማ ዞን በበንሳ ወረዳ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሁሮ ጡሙሮ የተሰኘ የውሃ ፕሮጀክት ግንባታ  ያስጀምራል። ጨረታውን ደግሞ አቶ ተክለወልድ ማሞ የተሰኙ የውሃ ስራዎች ተቋራጭ ያሸንፋሉ ግለሰቦቹ 40 በመቶ ብቻ የተከናወነውን ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል በማለት ያለ አግባብ ክፍያ እንዲፈጸም በማድረጋቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።  ግለሰቦቹ  በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እንዲጀመርባቸው የሚያስችል በቂ ማስረጃ መገኘቱንም ነው አቶ ገበየሁ የተናገሩት። የፈደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የጸረ ሙስና ትግሉን ሃገራዊ ለማድረግ ከክልሎች ጋር በመቀናጀት በጋራ እየሰራ ነው የሚገኘው። በፈደራል ተፈጽሞ መሸሸጊያውን ክልል ሊያደርግ  የሚሞክር የሙስና ተግባር መግቢያ እንዲያጣ ለማድረግ ይህ የፌደራልና የክልሎች ቅንጅታዊ ስራ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ነው እየተነገረ ያለው። በፌደራል ደረጃ በቅርቡ በገ

The USPFJ Strongly Condemns the Sabotage of the Sidama New Year ‘Fichchee’ by Ethiopian Government!

Press Statement By United Sidama Parties for Freedom and Justice (USPFJ) August 15, 2013 The current ‘Tigray People’s Liberation Front (TPLF) led Ethiopian regime continually denies the basic rights of Sidama nation to exercising their constitutional privileges enshrined in the supreme law of the country since it’s assumed power in June 1991. The regime uses a few dozens of handpicked Sidama cadres who are meticulously selected by the regime for their ability of implementing anti-Sidama policies of the regime in Sidama land whilst the regime expropriates its resources. The Sidama cadres are also selected for their capacity in obliviously torturing, arresting, killing and totally silencing the Sidama nation whenever the regime orders them to do so. Therefore, the Sidama people and its region remain the most marginalized in the country characterized by high unemployment, abject poverty and severe deprivation despite its lucrative economic contribution to the federal gov

መሬትን ሳያርሱ በማልማት በምርምር የተገኘውን ተሞክሮ ወደ አርሶ አደሩ ለማስፋት የሚያስችል መድረክ ተመሰረተ

Image
ሃዋሳ ነሐሴ 8/2005 በወንዶ ገነት ግብርና ምርምር ተቋም የሃዋሳ መለስተኛ የበቆሎ ምርምር ማዕከል መሬትን ሳያርሱ የማልማት ምርምር ስራ የተገኘውን ተሞክሮ ወደ አርሶ አደሩ ለማስፋት የሚያስችል የባለ ድርሻ አካላት የጋራ መድረክ ተመሰረተ ። መሬትን ሳያርሱ የማልማት ምርምር ስራዉን ወደ አርሶ አደሩ ለማስፋት እንዲቻል የጋራ መድረኩ የተመሰረተዉ ትናንት በሃዋሳ በተካሄደ ምክክር ላይ ነዉ ። በሀዋሳ የበቆሎ ምርምር መለስተኛ ማዕከል ዳይሬክተርና የምርምር ፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ጎሽሜ ሙሉነህ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩ ምርምሩ ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ በሚገኙ አምስት ሀገራት እየተካሄደ ነዉ ። መሬትን ሳያርሱ በማልማት በምርምር በተገኘው ተሞክሮ የቦሎቄና በቆሎን ምርታማነት በማሳደግ በምግብ ሰብል ራስን ለመቻል ያለመ ነው ብለዋል ። በክልሉ ሲዳማ ዞን በአንድ ወረዳ ከሁለት ዓመት በፊት በአምስት አርሶ አደሮች የተጀመረው መሬትን ሳያርሱ የማልማት የግብርና የምርምር ስራ በተጨማሪ በአራት ወረዳዎች በማስፋት ምርምሩ ውጤታማ እንደሆነም ተገልጧል ። የምርምር ማዕከሉ የቦሎቄና በቆሎ ተረፈ ምርት በማሳው ላይ እንዳለ በማቆየት የአፈር ለምነትን በመጠበቅ ምርታማነትን ማሳደግ እነደሚቻልም መረጋገፈጡ ተገልጧል ። በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች እስካሁን እየተሰራበት ያለ መሬትን ሳያርሱ የማልማት ልማዳዊ አሰራር ቢሆንም ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በመጠቀም ቢሰራበት ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ለአፈር ለምነት የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን አቶ ጎሽሜ ተናግረዋል። በደቡብ ክልል በሀድያ ሲዳማና ጉራጌ ዞኖች የሚገኙ የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ፣ የሎካ አባያ የቦርቻ የመስቃንና የምስራቅ ባድዋቾ ወረዳዎች በምርምሩ መታቀፋቸዉንና ባለፉት ሶስስት ዓመታት የተገኘው ውጤት አርሶ

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በ415 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚያካሄደው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ህንጻ ግንባታ በመፋጠን ላይ ነዉ

Image
ሃዋሳ ነሐሴ 8/2005 የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከመንግስት በተመደበለት 415 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚያካሄደው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፕሮጀክት ህንጻ ግንባታ በመፋጠን ላይ መሆኑን ገለጸ፡፡ ዩኒቨርሰቲው በ2006 የሚያስጀምራቸው ግንባታዎች ጨምሮ ከ2 ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ሌሎች በርካታ ፕሮጀክቶች እንደሚያካሂድም ተመልክቷል፡፡ በዩኒቨርስቲው የኮንስትራክሽንና ሜንቴናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደንበሹ ኒኤሬ ሰሞኑን እንደገለጹት ግንባታ በ2004 የተጀመረው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ ህንጻ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንበታ 164 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ነው ። በመገንባት ላየ ያለዉ ህንጻ በርካታ የመማሪያ ክፍሎች፣ የሌክቸር አዳራሽ፣ ቤተሙከራ፣ ቢሮዎች፣ የተማሪዎች መዝናኛዎችን የያዘ መሆኑን አስታዉቀዋል ። በሁለተኛው ምዕራፍ 251 ሚሊዮን ብር የተመደበለት የተማሪዎች ማደሪያና መስተንግዶ፣ የመመገቢያ አዳራሽ፣ የቴክኖሎጂ ላብራቶሪ ጨምሮ ለሌሎች ግንባታዎች እንደሚካሄዱ አስረድተዋል፡፡ በዩኒቨርስቲው ዋና ግቢ የሚገነባዉ ህንጻ የአካል ጉዳተኞች መወጣጫና መመላለሻዎችን ከግምት የሚያስገባ ሲሆን ከአጠቃላይ ግንባታዉ እስከአሁን ከ30 በመቶ በላይ መከናወኑን ጠቁመዋል፡፡ የፕሮጀክቱ ግንባታ በ2007 የስራ ዘመን ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ በመደበኛነት ብቻ 15ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተማር አቅም እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ መገንባት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀገሪቱ የምትፈልጋቸውን የተማረ የሰው ሃይል በብዛትና በጥራት በማፍራት በተለይ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት በየአመቱ የሚቀበላቸውን ተማሪዎች 70 በመቶ የሳይንስናቴክኖሎጂ ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ግብ በማሳካት ከፍተኛ አስተዋጾኦ እንዳለው አቶ ደንበሹ አስረድተዋል፡፡ በዩኒቨርስቲው