Posts

Time for street corn on the cob

Image
Fantu Debele, a mother of four small children, has been preparing the corn for half a day and is about to carry it to a street near to her village, Cazainchis. She bought a sack of corn (corn on the cob) for 150 birr from the market, where many gather to bargain with the wholesalers, helped by the brokers who mediate. This is her main business and the way she provides for her four children, for whom she cares alone after her husband died six years ago. “I rise from bed early in the morning and cook breakfast for the kids, then leave for the market. I spend the whole day making up the corn, which I aim to get ready before six,” she says. She has been doing it for four years and predicts it would have been successful if she had had enough money and someone to help her. “The most difficult part of the job is purchasing the corn on the cob from the market and breaking it down so that the pot can hold it up to its brim,” she says. Many Ethiopians endure the cold winters by sipping

Coffee Crisis:Big Business Losses, Street Vendors Gain

Image
Coffee, the mainstay of the Ethiopian economy, is bringing some gloom to the big businesses and some boom to the lowly ones, such as street vendors. Sibhat Hailay, 25, from Hawzien, Tigray, came to Addis Abeba nine months ago, after quitting school in sixth grade.  He started selling cheap shoes and clothes for women by the road side around Megenagna. Five months into this business, the profits continued to be so small that he could hardly keep up with his expenses. In around April, he learned than selling coffee would bring him more profits. By way of a trial, he invested 300 Br in five kilos. “It is incomparable,” Sibhat says, when considering the new business against the old one. Several vendors like Sibhat have turned to coffee, over the past months, and are reaping the rewards – selling a kilo for an average of 65 Br. Last Wednesday, Sibhat was left with only 10kgs, having sold 20 of the 30kgs he had bought the day before. For the 57-year-old Molash Maru, a pension

ለዝዋይ - ሐዋሳ መንገድ ግንባታ የዓለም ባንክና ቻይና 750 ሚሊዮን ዶላር ብድር ተጠየቁ

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የአገሪቱን የመንገድ አውታር ወደ ላቀ ደረጃ ያደርሳሉ ካላቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው ከዝዋይ ሐዋሳ ድረስ ለሚገነባው የፍጥነት መንገድ፣ የዓለም ባንክና የቻይናው ኤግዚም ባንክ 750 ሚሊዮን ዶላር እንዲያበድሩት ጠየቀ፡፡ ባለሥልጣኑ የብድር ጥያቄውን ባለፈው ሰኞ ለዓለም ባንክ ሲያቀርብ፣ በሳምንቱ መጨረሻ ደግሞ ለቻይናው ኤግዚም ባንክ ማቅረቡ ታውቋል፡፡ ይህ መንገድ ከሞጆ ከተማ ተነስቶ እስከ ሐዋሳ ድረስ የሚዘረጋው ባለ አራት ረድፍ (ሌን) አዲስ መንገድ አካል ነው፡፡ ከሞጆ እስከ ዝዋይ ድረስ ለሚዘልቀው የመጀመሪያ ዙር መንገድ ግንባታ የአፍሪካ ልማት ባንክና የደቡብ ኮሪያ መንግሥት ብድር ለመስጠት ፈቃደኛነታቸውን ማሳየታቸውን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ መረጃዎች እንደጠቆሙት ለዚህ ግንባታ የአፍሪካ ልማት ባንክ 350 ሚሊዮን ዶላር፣ የደቡብ ኮሪያ መንግሥት አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር ብድር እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ የሚቀጥለው ክፍል ማለትም ከዝዋይ እስከ ሐዋሳ የሚዘልቀው መንገድ 750 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት ለዓለም ባንክና ለቻይና ኤግዚም ባንክ ቀርቧል፡፡ የሁለቱ ፋይናንስ ተቋማት ምላሽ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ እንደሚታወቅ ተነግሯል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት የአገሪቱን የተለያዩ አካባቢዎች በመንገድ አውታር በማገናኘት ሥራ ላይ ተጠምዶ አሳልፏል፡፡ በአሁኑ ወቅት በመንገድ አውታር ከማገናኘት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን በሚያጎለብት ደረጃ ማዘመን ያስፈልጋል በሚል ወደ ‹‹ሰከንድ ጄነሬሽን›› ቅኝት ተሸጋግሯል፡፡ መንገዶች ባለሥልጣን ይህንን እውን ያደረገው ከአዲስ አበባ አዳማ ድረስ የተዘረጋውን ግዙፍ የፍጥነት መንገድ ግንባታ በመጀመር ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት ከቻይና ኤግዚም ባንክ

የሀዋሳ ሀይቅን ከብክለት ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት እየተካሄደ ነው

Image
አዋሳ ነሐሴ 3/2005 የሀዋሳን ሀይቅ ከብክለት ለመከላከል በ13 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚካሄደው የቆሻሻ ጎርፍ ማጣሪያ ፕሮጀክት ከግማሽ በላይ መከናወኑን የከተማው ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ፡፡ በማዘጋጃ ቤቱ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ መብራቴ መለሰ ከትናንት በስቲያ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከከተማው የተለያየ አቅጣጫ ወደ ሀይቁ የሚፈሰው ቆሻሻ ጎርፍ በጥናት ተለይቶ ሀይቁን ከብከለት ለመታደግ የሚያስችል ፕሮጀክት ተዘጋጅቶ በ2005 አጋማሽ ላይ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ በጥናቱ መሰረት ከፍተኛ የቆሻሻ ጎርፍ ወደ ሀይቁ የሚገባባቸው በሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ ሪፈራል ሆስፒታል፣ አሞራ ገደል፣ ጨምበላላና ጥምቀተ ባህር አካባቢዎች በኩል መሆኑን ተረጋግጧል ብለዋል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የሚፈሰው ቆሻሻ ጎርፍ አጣርቶ ንጹህ ውሃን ብቻ ወደ ሀይቁ የሚለቅ ፕሮጀክት ማዘጋጃ ቤቱ ማመቻቸቱን ገልፀዋል፡፡ ለኘሮጀክቱ ማከናወኛ 13 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ወደ ስራ የተገባው ሲሆን የዚሁ ኘሮጀክት ግንባታ እስካሁን ከአጠቃላይ ስራው ከ58 በመቶ በላይ መከናወኑን አስረድተዋል፡፡ ስራውም በአራት የተከፈለ ሲሆን የመጀመሪያው ወደ ሃይቁ የሚመጣውን ጎርፍ የሚቀበልና የጉርጓድ ገንዳዎች ሲኖሩት ቀጥሎ ማንኛውንም ባዕድ ነገር ለይቶ እያጣራ ንጹህ ውሃን ብቻ የሚለቅና ፍሰቱን የሚቆጣጠር በመጨረሻም የሚጣራው ቆሻሻ እዚያው ማስቀረት የሚችሉ የተለያዩ የዛፍ ችግኞች በየአካባቢዎቹ የመትከልና የማልማት ስራ መሆኑን አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡ ይህም ከከተማ ነዋሪና ከትላላቅ ተቋማት የሚወጣው ባዕድ ነገርና ኬሚካል ወደ ሀይቁ እንዳይገባ በማድረግ ከብክለት ለመከላከልና ደህንነቱን በዘላቂነት ለመጠበቅ የሚያስችል ፕሮጀክት ነው፡፡ የፕሮጀክቱ ስራም በመጪው አመት ጥቅምት ወር ድረስ

በሲዳማ ዞን ከበልግ እርሻ ከስድስት ሚሊዮን ኩንታል የሚበልጥ ምርት ተሰበሰበ

አዋሳ ነሐሴ 3/2005 በሲዳማ ዞን በምርት ዘመኑ በበልግ ከ100 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በዘር በመሸፈን ከስድስት ሚሊዮን ኩንታል የሚበልጥ ምርት መሰብሰቡን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ። በመምሪያው የግብርና ልማት እቅድና ዝግጅት የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ ደርቤ በትራ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በግብርናው ዘርፍ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማረጋገጥ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የምርጥ አርሶ አደሮችን ተሞክሮ ከማስፋት ባሻገር የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ በልግ አምራች በሆኑ ወረዳዎች 102 ሺህ 785 ሄክታር መሬት በአትክልትና ፍራፍሬ በስራስርና በቆሎ በመሸፈን ከስድስት ሚሊዮን የሚበልጥ ምርት በመሰብሰብ ከ300 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በዞኑ ባለፈው ዓመት በልግ ከ80 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በዘር ተሸፍኖ ከአራት ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል የሚበልጥ ምርት መሰብሰቡን ገልጸው ያለፈውን አመት መልካም ተሞክሮ በመቀመር ዘንድሮ ከፍተኛ ምርት መሰብሰብ መቻሉን አስታውቀዋል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=10683&K=1