Posts

የሀዋሳ ሀይቅን ከብክለት ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት እየተካሄደ ነው

Image
አዋሳ ነሐሴ 3/2005 የሀዋሳን ሀይቅ ከብክለት ለመከላከል በ13 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚካሄደው የቆሻሻ ጎርፍ ማጣሪያ ፕሮጀክት ከግማሽ በላይ መከናወኑን የከተማው ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ፡፡ በማዘጋጃ ቤቱ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ መብራቴ መለሰ ከትናንት በስቲያ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከከተማው የተለያየ አቅጣጫ ወደ ሀይቁ የሚፈሰው ቆሻሻ ጎርፍ በጥናት ተለይቶ ሀይቁን ከብከለት ለመታደግ የሚያስችል ፕሮጀክት ተዘጋጅቶ በ2005 አጋማሽ ላይ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ በጥናቱ መሰረት ከፍተኛ የቆሻሻ ጎርፍ ወደ ሀይቁ የሚገባባቸው በሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ ሪፈራል ሆስፒታል፣ አሞራ ገደል፣ ጨምበላላና ጥምቀተ ባህር አካባቢዎች በኩል መሆኑን ተረጋግጧል ብለዋል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የሚፈሰው ቆሻሻ ጎርፍ አጣርቶ ንጹህ ውሃን ብቻ ወደ ሀይቁ የሚለቅ ፕሮጀክት ማዘጋጃ ቤቱ ማመቻቸቱን ገልፀዋል፡፡ ለኘሮጀክቱ ማከናወኛ 13 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ወደ ስራ የተገባው ሲሆን የዚሁ ኘሮጀክት ግንባታ እስካሁን ከአጠቃላይ ስራው ከ58 በመቶ በላይ መከናወኑን አስረድተዋል፡፡ ስራውም በአራት የተከፈለ ሲሆን የመጀመሪያው ወደ ሃይቁ የሚመጣውን ጎርፍ የሚቀበልና የጉርጓድ ገንዳዎች ሲኖሩት ቀጥሎ ማንኛውንም ባዕድ ነገር ለይቶ እያጣራ ንጹህ ውሃን ብቻ የሚለቅና ፍሰቱን የሚቆጣጠር በመጨረሻም የሚጣራው ቆሻሻ እዚያው ማስቀረት የሚችሉ የተለያዩ የዛፍ ችግኞች በየአካባቢዎቹ የመትከልና የማልማት ስራ መሆኑን አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡ ይህም ከከተማ ነዋሪና ከትላላቅ ተቋማት የሚወጣው ባዕድ ነገርና ኬሚካል ወደ ሀይቁ እንዳይገባ በማድረግ ከብክለት ለመከላከልና ደህንነቱን በዘላቂነት ለመጠበቅ የሚያስችል ፕሮጀክት ነው፡፡ የፕሮጀክቱ ስራም በመጪው አመት ጥቅምት ወር ድረስ

በሲዳማ ዞን ከበልግ እርሻ ከስድስት ሚሊዮን ኩንታል የሚበልጥ ምርት ተሰበሰበ

አዋሳ ነሐሴ 3/2005 በሲዳማ ዞን በምርት ዘመኑ በበልግ ከ100 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በዘር በመሸፈን ከስድስት ሚሊዮን ኩንታል የሚበልጥ ምርት መሰብሰቡን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ። በመምሪያው የግብርና ልማት እቅድና ዝግጅት የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ ደርቤ በትራ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በግብርናው ዘርፍ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማረጋገጥ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የምርጥ አርሶ አደሮችን ተሞክሮ ከማስፋት ባሻገር የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ በልግ አምራች በሆኑ ወረዳዎች 102 ሺህ 785 ሄክታር መሬት በአትክልትና ፍራፍሬ በስራስርና በቆሎ በመሸፈን ከስድስት ሚሊዮን የሚበልጥ ምርት በመሰብሰብ ከ300 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በዞኑ ባለፈው ዓመት በልግ ከ80 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በዘር ተሸፍኖ ከአራት ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል የሚበልጥ ምርት መሰብሰቡን ገልጸው ያለፈውን አመት መልካም ተሞክሮ በመቀመር ዘንድሮ ከፍተኛ ምርት መሰብሰብ መቻሉን አስታውቀዋል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=10683&K=1

በሲዳማ ዞን በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድና በተለያዩ የስራ ዘርፎች ለተደራጁ አባላት ከ193 ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር ተፈጠረ

አዋሳ ነሐሴ 1/2005 በሲዳማ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድና በተለያዩ የስራ ዘርፎች ለተደራጁ ከ30 ሺህ በላይ አባላት ከ193 ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር መፈጠሩን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለጸ፡፡ በመምሪያው የኢንተርፕራይዝ ልማት የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ደበበ ተገኝ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የገበያ ትስስሩ የተፈጠረው ማህበራት ሰፊና ቀጣይነት ያለው የገበያ ትስስር እንዲኖራቸውና ምርትና አገልግሎታቸውን በወቅቱ ለገበያ እንዲያቀርቡ ለማስቻል ነው፡፡ አባላቱ ከተሰማሩባቸው የስራ ዘርፎች መካከል ማንፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን፣ ምግብ ማቀነባበር፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ ንግድ፣ የከተማ ግብርና፣ ኮብል ድንጋይ ማንጠፍ እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት የገበያ ትስስር የተፈጠረው በዞኑ ባሉት ሁለት የከተማ አስተዳደሮችና 19 ወረዳዎች መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በዞኑ 30 ሺህ 620 አባላት በተለያዩ የስራ ዘርፎች የተሰማሩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ከ8 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የማህበሩ አባላትም ከ14 ነጥብ5 ሚሊዮን በላይ ገንዘብ መቆጠባቸውን ጠቁመዋል፡፡ ማህበራት በተደራጁበት የስራ ዘርፍ ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል የምክር፣ የንግድ ስራ አመራር ስልጠናና ሌሎችም ድጋፎች እየተደረገላቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በአዲሱ ስትራቴጂ ማዕቀፍ መሰረት አዲስ ማህበራት ለመበደር ከሚፈልጉት ገንዘብ ውስጥ 20 በመቶ መቆጠብ እንዳለባቸው መመሪያ የተቀመጠ ሲሆን በበጀት ዓመቱ 13 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ብድር መሰራጨቱን ተናግረዋል፡፡ በተለያዩ የእድገት ደረጃ ለሚገኙ ማህበራት በዞኑ ከሚገኙ አምስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ጋር በመተባበር በርካ

የፍቼ ጫምበላላ በሃዋሳ ተከበረ

Image
የሲዳማ ብሔር ባህል፣ ቋንቋና ታሪክን ጠብቆ በማስተዋወቅ የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አስገነዘቡ፡፡ የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላና የብሔሩ  19 ኛው የቋንቋና ባህል ሲምፖዚየም ትናንትናና ከትናንት በስቲያ በሃዋሳ በድምቀት ተከብሯል፡፡ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ጫምባላላ ባህላዊ የአከባበር ሥነ ሥርዓትን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት  ( ዩኔስኮ )  ለማስመዝገብ የቅድመ ዝግጅት ሥራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ ደሴ ዳልኬ እንደገለጹት፣ የሲዳማ ህዝብ ለረጅም ዓመታት ማንነቱ፣ ባህሉና ቋንቋው ተረስቶ መቆየቱን በማስታወስ ባለፉት  21  ዓመታት ሥርዓቱ ባመጣው መልካም አስተዳደር ባህሉና ቋንቋው ተክብሮ የመናገር፣ የመዳኘትና የመማር ዕድል ባለቤት ለመሆን በቅቷል፡፡ የብሔሩን ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክና ቅርስን በማጥናትና በማልማት የበለጸገና ያደገ ህብረተሰብ ለመፍጠርና የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ የሲዳማ ብሔር ከሌሎች የሀገሪቱ ብሔረሰቦች ጋር አምባገነኑን ሥርዓት በመገርሰስ ልማት፣ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ባደረገው ትግል ያስገኘው ጣፋጭ ውጤት ለብሔሩ ቋንቋ፣ ባህልና ማንነት መከበር ጉልህ ድርሻ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡ በዚህ የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መጥቷል ብለዋል፡፡ የዞኑ ህዝብ ከሌሎች የክልሉና የሀገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በመቀናጀት የተጀመረውን የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡ ቀደምት የሲዳማ

ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ህዝብ በሃዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ የተከበረውን የሲዳማ ኣዲስ ኣመት የፊቼን በኣል በተመለከተ ከክልሉ ሚዲያ ውጭ ያሉት ኢቲቪን ጨምሮ የኣገሪቱ ትላልቅ የሚዲያ ኣውታሮች ሽፋን ኣለመስጠታቸው ኣነጋጋሪ ሆኗል

Image
የወራንቻ ኔዎርክ የኣገሪቱን ትላልቅ ጋዜጦችን እና የሚዲያ ኣውታሮች ዌይብ ሳይቶች ላይ ባደረገው ቅኝት መረዳት እንደተቻለው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፤ ሬዲዮ ፋና፤ ዋልታ፤ እና የኢትዮጵያ ዜና ኣገልግሎት የፊቼ በኣልን በተመለከተ በእለቱ ምንም ዘገባ ኣለማቅረባቸው ታውቋል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ኣካል የሆነው ኣዲስ ዘመን ጋዜጣ ግን የጫንባላላን ኣከባበር በተመለከተ በፎቶ የተደገፈ ዜና እለቱ ይዞ ወጥቷል። ለሲዳማ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የክልሉ ህዝብ ትልቅ ባህላዊ እሴት የሆነውን የፊቼን በኣል በተመለከተ ስለ በኣሉ ኣከባበር የምገልጹ እና በኣሉን የምያስተዋውቁ ዜናዎችን ብሎም ፕሮግራሞችን እነዚህ ትላልቅ የኣገሪቱ የዜና ኣውታሮች ኣለማቅረባቸው፤ የፊቼን በኣል በዩኔስኮ በኣለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የምደረገውን ጥረት የዜና ኣውታሮቹ እየደገፉ ኣለመሆናቸውን ያሳያል ተብሏል። የፊቼን በኣል በኣለም ቅርስነት ለማስመዝጋብ የሲዳማ ዞን ኣስተዳደር እንድሁም የክልሉ መንግስት ከኢትዮጵያ ባህል እና ቱርዝም ሚኒስቴር ጋር በመሆን የምያደርገውን ጥረት የተሳካ ለማድረግ የኣገሪቱ የሚዲያ ኣውታሮች ባህሉን ለኣለም ህዝብ በማስተዋዎች የበኩላቸውን ልወጡ ይገባል።