Posts

የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ የፊቼ ጫምባላላ በኣል ከግማሽ ሚሊዮን በምበልጥ ህዝብ በታላቅ ድምቀት በሃዋሳ ከተማ ተከበረ

Image
የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ የፊቼ ጫምባላላ በኣል ከግማሽ ሚሊዮን በምበልጥ ህዝብ በታላቅ ድምቀት በሃዋሳ ከተማ ተከበረ   ለተጨማሪ http://www.allcomtv.com/etv-vod?etvod=2013080716    

‹‹መንግሥት የሃይማኖት ብዝኃነትን ሲጠብቅ ነፃነትን እንዳይጋፋ መጠንቀቅ አለበት›› ተሰናባቹ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ

Image
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ላለፉት ሦስት ዓመታት በአዲስ አበባ የቆዩት አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ በእስልምና ተከታዮችና በመንግሥት መካከል ስላለው አለመግባባት፣ በዓባይ ወንዝና በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ስላለው ፖለቲካዊ ትኩሳትና ሌሎች ጉዳዮች የመንግሥታቸውን አቋምና የራሳቸውን ግንዛቤ ለሪፖርተር ጋዜጣና ሌሎች ሁለት ሚዲያዎች ባለፈው ሰኞ አካፍለዋል፡፡ አምባሳደሩ የሦስት ዓመታት የአዲስ አበባ ተልኳቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸው መመለሳቸውን አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል በእስልምና ተከታዮችና በመንግሥት መካከል የሚስተዋለው አለመግባባትና ግጭት አንዱ ነው፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሔሮችና ሃይማኖቶች የሚኖሩባት አገር ነች፡፡ ይህ ስብጥር እንደረጋ እንዲቆይ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት የእምነት ነፃነትና እኩልነትን አረጋግጧል፤›› በማለት አስተያየታቸውን የጀመሩት አምባሳደር ቡዝ፣ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ እንዲሁም ሃይማኖቶች በመንግሥት ላይ ጣልቃ እንዳይገቡ በግልጽ በሕገ መንግሥቱ መቀመጡ መሠረታዊ ነው ይላሉ፡፡ ይህ መሆኑ የትኛውም ሃይማኖት ነፃነት እንዲኖረውና ለተከታዮቹም የመረጡትን ሃይማኖት የመከተል መብት ይሰጣል ብለዋል፡፡ ‹‹አሁን ካለው ሁኔታ የምንረዳው ግን አንዳንድ ሰዎች ይህንን የመቀየርና የራሳቸውን እምነት በሌሎች ላይ በግድ የመጫን ፍላጎትና አመለካከት መኖሩን ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ይህ ሃይማኖታዊ ፅንፈኝነት ወይም አክራሪነት ሊባል ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት እየጣረ ያለውም ይህንን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ ነው፡፡ ምክንያቱም በሕገ መንግሥቱ ላይ ያለውን የመንግሥትና የሃይማኖት ግንኙነት ፅንሰ ሐሳብ የሚጎዳና በአገሪቱ የቆየውን የሃይማኖት ብዝኃነት የሚያደፈርስ በመሆኑ ነው፤›› በማለት ይገልጻ

በሲዳማ ባህላዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በመላው ኣለም ላይ ከምገኙት የሲዳማ ተወላጆች እና ከሲዳማ ወዳጆች ጋር ለመምከር የሚያስችል ፓልቶክ ሩም ተከፈተ

Image
በመላው ኣለም የምትገኙ ሲዳማዎች እና የሲዳማ ወዳጆች በፓልቶኩ ሩም በመገኘት እንድትወያዩ እና ሃሳብ እንድትለዋወጡ በኣዘጋጆቹ ተጋብዛችሃል። ወደ ፓልቶክ ሩም ለመግባት በመጀመሪያ ወደ ኢትዮጵያ ይግቡ ቀጥለውም Sidama cultural Heritage ላይ ክሊክ ያድርጉ  

በዛሬው እለት በመከበር ላይ ያለውን የሲዳማ ቋንቋ ሲምፖዚዬም እና የጫምባላላ በዓልን በተመለከተ በደቡብ ክልል ቴሌቪዥን የተዘጋጀውን ፕሮግራም

Image
በዛሬው እለት በመከበር ላይ ያለውን የሲዳማ ቋንቋ ሲምፖዚዬም እና የጫምባላላ በዓልን በተመለከተ በደቡብ ክልል ቴሌቪዥን የተዘጋጀውን ፕሮግራም  ይከታተሉ ከታች ካለው ሊንክ ላይ ተጨነው ይከታተሉ http://www.allcomtv.com/etv-vod?etvod=2013080616

የሲዳማ ቋንቋ ሲምፖዚዬም በመካሄድ ላይ ነው፤የሲዳሚኛ ቋንቋ ሶፊትዎር ተመርቋል

Image
ለተጨማሪ ዜና ከታች ይጫኑ http://www.allcomtv.com/etv-vod?etvod=2013080616