የወጪ ንግድና የቡና ገበያ ዥዋዥዌ
የአገሪቷን የወጪ ንግድ ገቢን ለማሳደግ በየዓመቱ የሚያዘው ውጥንና ትግበራው ዘንድሮም አልተጣጣመም፡፡ የ12ቱ ወራት የወጪ ንግድ ክንውን በ2005 ዓ.ም. ዋዜማ ላይ ሲወጠን አገሪቱ በ2005 በጀት ዓመት ታገኛለች ተብሎ የተጠበቀውን ያህል ብቻ ሳይሆን ከቀዳሚው ዓመት ክንዋኔ ጋር ሲነፃፀርም አንሶ ተገኝቷል፡፡ የ2005 በጀት ዓመት የወጪ ንግድ ገቢ ዕቅድ አምስት ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ተገኘ የተባለው ግን 3.08 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ አምና 3.2 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ተገኝቶ ነበር፡፡ በበጀት ዓመቱ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ በተፈለገው ዕቅድ መጠን አለመስተካከሉ የአገሪቱ ዋና ዋና የወጪ ንግድ ምርቶች ገቢ በመቀነሳቸው ነው፡፡ በተለይ ከቡና የወጪ ንግድ ከተጠበቀው በታች የሆነ ገቢ ማስገኘቱ አንዱ ምክንያት ሆኗል፡፡ በበጀት ዓመቱ ከቡና 1.2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚገኝ ታሳቢ የተደረገ ቢሆንም፣ የተገኘው ግን 746.4 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ ይህ ገቢ በበጀት ዓመቱ ከቡና ይገኛል ተበሎ ከነበረው ገቢ በሁለት በመቶ አንሷል፡፡ ባለፈው ዓመት ተገኝቶ የነበረው ገቢ 832.9 ሚሊዮን ዶላር በመሆኑ በሁለቱ ዓመታት የተመዘገበው የውጭ ምንዛሪ ከ86 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቀንሶ ታይቷል፡፡ ከቡና የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከተጠበቀው መጠን በታች ይሁን እንጂ ለውጭ ገበያ የቀረበው የቡና መጠን ዕድገት አሳይቷል፡፡ በ2005 በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ የቀረበው የቡና መጠን በ19 በመቶ አድጐ ወደ 200 ሺሕ ቶን የሚጠጋ ቡና ለገበያ ቀርቧል፡፡ በዚህን ያህል መጠን አድጐ የተላከው ቡና ለምን ገቢው ቀነሰ የሚለው ጥያቄ የተለያዩ ምክንያቶች የሚቀርቡበት ቢሆንም፣ ዋነኛ ምክንያቱ ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ የቡና ዋጋ መቀነሱ ነው፡፡ በተለ