Posts

ሲዳማን ጨምሮ ከደቡብ ክልል ዘንድሮ ከ83 ሺህ 100 ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ቀረበ

ሃዋሳ ሐምሌ 16/2005 በደቡብ ክልል በተጠናቀቀው የበጀት አመት 83 ሺህ 140 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ ገለጸ፡፡ በቢሮው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ቡናው የቀረበው በክልሉ ቡና አምራች ከሆኑ የተለያዩ ዞኖች በሚገኙ 380 የህብረት ስራ ማህበራትና ከ330 በሚበልጡ የግል ባለሃብቶች እንዲሁም የቡና ተክል ልማት ድርጅት አማካኝነት ነው፡፡ በዘመኑ ለማዕከላዊ ገበያ ገበያ ከቀረበው ከዚሁ ቡና ውሰጥ 42 ሺህ 189 ቶን የታጠበና ቀሪው 40 ሺህ 951 ቶን ደግሞ ያልታጠበ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በስራው ላይም 394 የቡና ማዘጋጃ ኢንዱስትሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ክንውኑ የእቅዱን 68 በመቶ መሸፉኑንና ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ ከዕቅዱ ሊያንስ የቻለው ህገ ወጥ የቡና ግብይትና ዝውውር መበራካት እንዲሁም የአለም ገበያ ዋጋ መቀነስና መዋዥቅ ጋር ተያይዞ ቡና አምራቹ ገበሬና አቅራቢው ወደፊት ዋጋው ይጨምራል በሚል በክምችት መያዙ አቶ መላኩ በምክንያትነት ከጠቀሱት ውስጥ ይገኙበታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከክልል እስከ ቀበሌ በየደረጃው የተቋቋመው የቡና ጥራትና ንግድ ቁጥጥር አሰተባባሪ ግብረ ሀይል በማጠናከር ህገ ወጥ ንግድ እንዲቆም ለማድረግ በዘመኑ በተካሄደው እንቅሰቃሴ ጀንፈል፣ መርቡሽ፣ እሸት ቡና ጨምሮ ከ21 ሺህ 700 ኩንታል በላይ ቡና ከህገ ወጦች ተይዞ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ በህጋዊ መንገድ በመሸጥ ለመንግስት ገቢ መሆኑን የስራ ሂደቱ ባለቤቱ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ግምሩክ ባለስልጣን የሀዋሳ ቅርንጫፍ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ62 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የኮንትሮባንድ እቃ ያዘ

Image
ሃዋሳ ሐምሌ 16/2005 በኢትዮጵያ ገቢዎችና ግምሩክ ባለስልጣን የሀዋሳ ቅርንጫፍ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ62 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የኮንትሮባንድ ዕቃ መያዙን አስታወቀ። የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ ፈቃደ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በአራት መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ክምችት ይገኝባቸዋል ተብሎ በተጠረጠሩ ከተሞች በተደረገ ፍተሻ 62 ሚሊዮን 400 ሺህ 986 ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ አዳዲስና ልባሽ ጨርቆች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ መድሀኒቶችና ሌሎች የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል። ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ውስጥ አዳዲስ አልባሳት፣ አሮጌ ልባሽ ጨርቅና ጫማ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ዘይትና ሌሎች ምግብ ነክ ምርቶች፣ መድሀኒቶች፣ ትምባሆና የትንባሆ ውጤቶች ከፍተኛውን መጠን የያዙ መሆናቸውን አቶ ያሬድ ገልጸዋል። በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ሲገባ የተያዘው የኮንትሮባንድ ዕቃ መጠን በገንዘብ ሲገመት ከ10 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው የተለያዩ ልባሽና አዳዲስ ጨርቆች መድሀኒቶችና የመዋቢያና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች መያዛቸውንና ኮንትሮባንድ የመያዝ አቅም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር እድገት ማሳየቱን ተናግረዋል። የኮንትሮባንድ ወንጀልን ለመቆጣጠር በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ ጥምር ኮሚቴ በክልል ደረጃና በክልሉ በሚገኙ አምስት ዞኖችና በምዕራብ አርሲ ዞንና በባሌ ዞን ደረጃ የፀረ ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ ከተዋቀረ ወዲህ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ መዳከሙን ገልጸዋል። በግማሽ ዓመቱ ኮንትሮባንድን በተመለከተ ለጽህፈት ቤቱ ከደረሱ ጥቆማዎች ውስጥ አብዛኞቹ ለውጤት መብቃታቸውንና በጥቆማዎቹ መሰረት በተሽከርካሪና በጋማ ከብት ተጭነው ወደ ሀ

ከሲዳማ ነጻ ኣውጭ ግንባር (ሲነግ) ተጠሪ ከሆኑት ከካላ ቤታና ሆጤሳ ጋር የወቅቱ የሲዳማ ፖለቲካ በተመለከተ የተደረገ ቃለ ምልልስ

Image
New

ሲዳማን ጭምሮ በደቡብ ክልል መሬትን ሳያርሱ የማልማት ዘዴ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ከፍተኛ ምርት ማግኘታቸውን አስታወቁ

አዋሳ ሐምሌ 15/2005 በደቡብ ክልል መሬትን ሳያርሱ የማልማት ዘዴ የተሳተፉ አርሶ አደሩች ከፍተኛ ምርት ማግኘታቸውን አስታወቁ፡፡ በአውስትራሊያ መንግስት ድጋፍ በወንዶ ገነት ግብርና ምርምር ተቋም የሀዋሳ መለስተኛ የበቆሎ ምርምር ማዕከል መሬትን ሳያርሱ የማልማት ምርምር ስራ እያካሄደ ነው። በክልሉ ሀድያ፣ ሲዳማና ጉራጌ ዞኖች በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች ከሁለት ዓመት በፊት በአምስት አርሶ አደሮች የተጀመረው መሬትን ሳያርሱ የማልማት የዕቀባ ግብርና በተያዘው ዓመት በ200 አርሶ አደሮች እየተከናወነ ይገኛል። ትናንት በምስራቅ ባድዋቾ ወረዳ ጨፋ 01 ቀበሌ በተከናወነ የመስክ ቀን ላይ ማሳቸው የተጎበኘላቸውና በምርምሩ የታቀፉ አርሶ አደሮች እንደገለጹት በግብርና ምርምር ተቋሙ በተደረገላቸው ድጋፍ መሬት ሳያርሱ በቆሎና ቦሎቄ በማልማት ቀደም ሲል ከሚያገኙት ምርት ብልጫ ያለው መሰብሰብ ችለዋል። አርሶ አደር ሞላ አመሌና እንደገለጹት በምርምሩ ታቅፈው መሬት ሳያርሱ በማልማታቸው ቀደም ሲል በሄክታር ሲያገኙ ከነበረው ምርት በ50 በመቶ ብልጫ ያለው ምርት ማግኘት እንደቻሉ ገልጸዋል። መሬት ሳያርሱ ለዘር የሚሆን መስመር በማዘጋጀት ብቻ የበቆሎና ቦሎቄ በማሰባጠር ዘርተው ቦሎቄ አንድ ዙር እንደሰበሰቡና በቆሎው እስኪደርስ ድረስ ሁለተኛ ዙር ቦሎቄ ዘርተው ቡቃያው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሌላው ወጣት አርሶ አደር ደግነት ደሳለኝ በበኩሉ እንዳለው ሳያርሱ በመዝራት ዘዴ አሰባጥሮ በማልማት የመሬቱን ለምነት መጠበቅ እንደሚቻል በተደረገው ምርምር ያገኘውን ዕውቀት መሰረት አድርጎ ወደ ልማቱ መግባቱንና በቆሎ ተሰብስቦ እስኪያልቅ በስሩ ቦሎቄ ሁለት ጊዜ በማምረት የቦሎቄ ዘር በማቅረብ ተጠቃሚ መሆን ችሏል። የቤተሰቡ የእርሻ ማሳ በከፍተኛ ደረጃ በጎርፍ የሚጠቃና ውሃ ይ

የአውሮፓ ኅብረት የፓርላማ ቡድን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አሳሳቢ ነው አለ

Image
-    የቃሊቲን እስር ቤት እንዳይጎበኝ መከልከሉን ገለጸ  ለሦስት ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረገው የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ የሰብዓዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ በአገሪቱ ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን አስታወቀ፡፡ ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በአስቸኳይ እንደፈቱም ጠይቋል፡፡ ከሐምሌ 8 እስከ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረገው የአውሮፓ ኅብረት የልዑካን ቡድን፣ በኢትዮጵያ የነበረውን ጉብኝት ካጠናቀቀ በኋላ ሰሞኑን በሒልተን ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነበር ይህንን የገለጸው፡፡  እንደ ቡድኑ ድምዳሜ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ዕንባ ጠባቂ ተቋም መቋቋማቸውና በቅርቡ የፀደቀው አገራዊ የሰብዓዊ መብት መርሐ ግብር የሚበረታታ ዕርምጃ መሆኑን ገልጾ፣ መንግሥት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ መሆኑን አስረድቷል፡፡  ከመንግሥትና ከተቃዋሚ ተወካዮች እንዲሁም ከሲቪል ማኅበረሰብ አካላት ጋር ሰፋ ያለ ምክክርና ውይይት ያደረገው ቡድኑ፣ በአገሪቱ ዲሞክራሲ ማበብ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ የሚተመንባቸው ነፃ ሚዲያና ሲቪክ ማኅበረሰባት በከፍተኛ ደረጃ እንዳይሠሩ የተደረጉ መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፀረ ሽብረተኝነት አዋጁን ጨምሮ የአገሪቱን የፖለቲካ ድባብ አፍነው ይዘውታል ያሉዋቸው ሕጎች እንዲከለሱ ቡድኑ መንግሥትን ጠይቋል፡፡ ለዚህም በእስር ላይ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና ጋዜጠኞች ሐሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን በመጠቀማቸው ለእስር የተዳረጉ መሆናቸውን በመግለጽ፣ በአስቸኳይ እንዲፈቱ መንግሥትን ጠይቋል፡፡ እስረኞችን በመጎብኘት የመጀመርያ መረጃ ለማግኘት አቅዶ እንደነበረ ያስታወቀው ቡድኑ፣ ቃሊቲ እስር ቤትን እንዳይጎበኝና እስረኞችን