ሲዳማን ጭምሮ በደቡብ ክልል መሬትን ሳያርሱ የማልማት ዘዴ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ከፍተኛ ምርት ማግኘታቸውን አስታወቁ
አዋሳ ሐምሌ 15/2005 በደቡብ ክልል መሬትን ሳያርሱ የማልማት ዘዴ የተሳተፉ አርሶ አደሩች ከፍተኛ ምርት ማግኘታቸውን አስታወቁ፡፡ በአውስትራሊያ መንግስት ድጋፍ በወንዶ ገነት ግብርና ምርምር ተቋም የሀዋሳ መለስተኛ የበቆሎ ምርምር ማዕከል መሬትን ሳያርሱ የማልማት ምርምር ስራ እያካሄደ ነው። በክልሉ ሀድያ፣ ሲዳማና ጉራጌ ዞኖች በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች ከሁለት ዓመት በፊት በአምስት አርሶ አደሮች የተጀመረው መሬትን ሳያርሱ የማልማት የዕቀባ ግብርና በተያዘው ዓመት በ200 አርሶ አደሮች እየተከናወነ ይገኛል። ትናንት በምስራቅ ባድዋቾ ወረዳ ጨፋ 01 ቀበሌ በተከናወነ የመስክ ቀን ላይ ማሳቸው የተጎበኘላቸውና በምርምሩ የታቀፉ አርሶ አደሮች እንደገለጹት በግብርና ምርምር ተቋሙ በተደረገላቸው ድጋፍ መሬት ሳያርሱ በቆሎና ቦሎቄ በማልማት ቀደም ሲል ከሚያገኙት ምርት ብልጫ ያለው መሰብሰብ ችለዋል። አርሶ አደር ሞላ አመሌና እንደገለጹት በምርምሩ ታቅፈው መሬት ሳያርሱ በማልማታቸው ቀደም ሲል በሄክታር ሲያገኙ ከነበረው ምርት በ50 በመቶ ብልጫ ያለው ምርት ማግኘት እንደቻሉ ገልጸዋል። መሬት ሳያርሱ ለዘር የሚሆን መስመር በማዘጋጀት ብቻ የበቆሎና ቦሎቄ በማሰባጠር ዘርተው ቦሎቄ አንድ ዙር እንደሰበሰቡና በቆሎው እስኪደርስ ድረስ ሁለተኛ ዙር ቦሎቄ ዘርተው ቡቃያው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሌላው ወጣት አርሶ አደር ደግነት ደሳለኝ በበኩሉ እንዳለው ሳያርሱ በመዝራት ዘዴ አሰባጥሮ በማልማት የመሬቱን ለምነት መጠበቅ እንደሚቻል በተደረገው ምርምር ያገኘውን ዕውቀት መሰረት አድርጎ ወደ ልማቱ መግባቱንና በቆሎ ተሰብስቦ እስኪያልቅ በስሩ ቦሎቄ ሁለት ጊዜ በማምረት የቦሎቄ ዘር በማቅረብ ተጠቃሚ መሆን ችሏል። የቤተሰቡ የእርሻ ማሳ በከፍተኛ ደረጃ በጎርፍ የሚጠቃና ውሃ ይ