በደቡብ ክልል በተጠነቀቀው በጀት ዓመት በሁሉም የልማት መስኮች የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል
አዋሳ ሐምሌ 06/2005 በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሁሉም የልማት መስኮች መላውን የክልሉን ነዋሪ ተጠቃሚ ያደረጉ አበረታታች ስራዎች መከናወናቸውን የትምህርት ሚኒስትር በመሆን የተሾሙት የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ። ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለክልሉ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ መደበኛ ጉባኤ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ እንዳሉት በተጠናቀቀው በጀት አመት በግብርና በትምህርት በጤና በመንገድ በንግድ ኢንዱስትሪ፣በከተማ ልማትና ሌሎች መስኮች የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማና መላውን ነዋሪ ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው። በግብርናው መስክ አርሶ አደሩ መስኖ ተጠቅሞ በበጋ ወራት በገበያ ተፈላጊ የሆኑና የተሻለ ዋጋ የሚያስገኙ ሰብሎችን እንዲያመርት እንዲሁም የራሱንና የቤተሰቡን ጉልበት በአግባቡ ልማት ላይ በማዋል ገቢውን እንዲያስድግ በተሰራ ስራ አበረታች ውጤት ከመመዝገቡ በተጨማሪ በአከባቢ አየር ለውጥ ምክንያት ወቅቱ፣ ስርጭቱና መጠኑ እየተዛባ ካለው የዝናብ ተፅዕኖ የሚያላቅቁ ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል፡፡ በአነስተኛ ወጪና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በሁለት ዙር የመስኖ ልማት 180ሺህ 905 ሄክታር መሬት በስራስር፣ ቦሎቄ፣ ቦቆሎ፣ እና የጓሮ አትክልቶች በመሸፈን 26 ሚሊዮን 606ሺህ 342 ኩንታል ምርት ማምረት መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ከክልሉ የሚመረተውን ቡና ጥራትና ደረጃ በማስጠበቅ በብዛት አምርቶ ለውጪ ገበያ በማቅረብ ሀገሪቱ የምታገኘውን የውጪ ምንዛሪ ለማሳደግና አምራች አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን 42 ሺህ 189 ቶን የታጠበና 40ሺህ 952 ቶን ያልታጠበ ቡና በግልና በማህበረት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ ተችሏል ብለዋል። በክልሉ በከተማና ገጠር 704 የውሃ ተቋማትን በመገንባት፣የማስፋፊያና የጥገና ስራ በማከናወን 1