ታላቋ የአፍሪካ መዲና ከትንሿ ሸበዲኖ ምን ትማር?
የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የበርካታ ታላላቅ አለም አቀፋዊ ድርጅቶች መናኸሪያ ነች፡፡ ከተማችን አዲስ አበባ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገች መሄዷ ቢነገርላትም በፅዳትና በንፅህናዋ ረገድ ያለችበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ ዋና ዋና የከተማይቱ ጎዳናዎችና ትላልቅ አደባባዮች ሳይቀሩ የቆሻሻ ማጠራቀሚያና ዋጋ የማይከፈልባቸው መፀዳጃ ቦታዎች በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ እዚህም እዚያም እየተንጠባጠቡ የሚታዩትን እዳሪዎችን ላለመርገጥ እየዘለሉ መራመድ በብዙ የከተማዋ አካባቢዎች የተለመደ ተግባራት ናቸው፡፡ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ህዝብ እንደሚኖርባት በሚነገርላት በዚህችው ከተማ ውስጥ የሚገኙ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች አንድና ሁለት ተብለው የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ እነዚህም ቢሆኑ በማህበር ተደራጁ ለተባሉ ቡድኖች ተሰጥተው ለተጠቃሚው አገልግሎት የሚሰጡት ገንዘብ እየተከፈለባቸው ሆኗል፡፡ ለመፀዳጃ ቤት አገልግሎቱ ገንዘብ የመክፈል አቅም የሌላቸው የጎዳና ተዳዳሪዎች፤የኔ ቢጤዎችና ከተማዋን በአግባቡ የማያውቁ እንግዳ መንገደኞች የተፈጥሮ ጥሪን የመመለስ ግዴታ አለባቸውና እዳሪያቸውን በመንገዱና በየአደባባዩ ለመውጣት ይገደዳሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በከተማዋ እጅግ የተለመደና እንደ ባህል ሆኖ የኖረው ጉዳይ ነው፡፡ “ሐበሻ መንገድ ላይ ሲበላ እንጂ ሲፀዳዳ አያፍርም” እየተባለ ሲተረትበትም ኖሯል፡፡ በአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት፣ ንጉሱ ህዝቡ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት እንዲቆጠብ የሚያሳስብ አዋጅ አስነግረው የመፀዳጃ ቤትን ጠቀሜታ ለህዝባቸው ለማስተማር ጥረት አድርገው ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ በአፄ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ ዘመነ መንግስታት ሲከናወን የቆየ ተግባር ነው፡፡ የህዝብ የመፀዳጃ ቤቶች በከተማው ዋና ዋና ስፍራዎች ላይ እንዲገነቡ ተደርገው ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ ህብረተሰቡ ከመፀዳጃ ቤት ው