Posts

LIVERPOOL SCHOOL OF MEDICINE AND THE GLOBAL FUND

Image
Photo by  http://www.msf.org.uk/country-region/ethiopia Hawassa – In Sidama Zone these days it is not uncommon to see health supervisors on motorbikes traveling quickly throughout each of the 19 districts, transporting information and education as well as test samples. These are people who have become bridges between their own rural communities and far-off healthcare facilities. They are part of a project which has newly energized effort to control tuberculosis (TB) in Ethiopia. Read more: http://www.stoptb.org/assets/documents/global/awards/tbreach/TBREACH_Flyer%20Lille%20LSTM%20and%20GF%20Ethiopia.pdf

Birth Preparedness and Complication Readiness among Pregnant Women in Southern Ethiopia-

Image
Abstract Background Birth preparedness and complication preparedness (BPACR) is a key component of globally accepted safe motherhood programs, which helps ensure women to reach professional delivery care when labor begins and to reduce delays that occur when mothers in labor experience obstetric complications. Objective This study was conducted to assess practice and factors associated with BPACR among pregnant women in Aleta Wondo district in Sidama Zone, South Ethiopia. Methods A community based cross sectional study was conducted in 2007, on a sample of 812 pregnant women. Data were collected using pre-tested and structured questionnaire. The collected data were analyzed by SPSS for windows version 12.0.1. The women were asked whether they followed the desired five steps while pregnant: identified a trained birth attendant, identified a health facility, arranged for transport, identified blood donor and saved money for emergency. Taking at least two steps was consider

የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሸጉጤ በወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ለመምከርና ጥሩ የሥራ አፈጻጸም ያላቸውን ኢንቨስተሮች ለማበረታታት በጠሩት ስብሰባ ላይ፣ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ መማረራቸውን አስታውቀዋል፡፡

Image
ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተማረሩ -  ልማት ባንክ ቅሬታቸውን አልተቀበለም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከአዲስ አበባ 275 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሐዋሳ ከተማ የተሰበሰቡ ኢንቨስተሮች፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ብድር እየሰጠ አይደለም ሲሉ አማረሩ፡፡  ሐሙስ ሰኔ 27 ቀን 2005 ዓ.ም. የትምህርት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሸጉጤ በወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ለመምከርና ጥሩ የሥራ አፈጻጸም ያላቸውን ኢንቨስተሮች ለማበረታታት በጠሩት ስብሰባ ላይ፣ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ መማረራቸውን አስታውቀዋል፡፡  ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ‹‹በትራንስፎርመር እጥረት›› በሚል ምክንያት የኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግር እየገጠማቸው መሆኑን በመጥቀስ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡  በተወሰነ ደረጃ በኢትዮ ቴሌኮም በኩልም ችግር መኖሩን የሚጠቅሱት ኢንቨስተሮች በክልሉ በኩልም የመሬት አቅርቦት፣ በዞኖችና ወረዳዎች የመልካም አስተዳደር እጦትና የወሰን ማስከበር ችግሮች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡  በደቡብ ክልል ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም. ድረስ 6,150 ኢንቨስተሮች ፈቃድ አውጥተው ቦታ ወስደዋል፡፡ ለስብሰባ የተጠሩት ውጤታማ ናቸው የተባሉ 1,500 የአገር ውስጥና የውጭ አገር ኢንቨስተሮች ናቸው፡፡  ኢንቨስተሮቹ የተሰማሩት በእርሻ፣ በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎት መስጫዎችና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ነው፡፡ እነዚህ ኢንቨስተሮች ሥራቸውን ለማስፋፋት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ቢጠይቁም ሊሰጣቸው እንዳልቻለ፣ በአንፃሩ ባንኩ ለውጭ ኩባንያዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር ሲሰጥ መታዘባቸውን በመናገር ምሬታቸውን ገል

በሃዋሳ ከተማ ከ11 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የትራፊክ ኮምፕሌክስ ህንፃ እየተገነባ ነው

ሃዋሳ ሐምሌ 2/2005 በደቡብ ክልል ሃዋሳ ከተማ ከ11 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የአሽክርካሪ ብቃት ምዘና የሚደረግበት ዘመናዊ የትራፊክ ኮምፕሌክስ ህንፃ ግንባታ ከ85 በመቶ በላይ መጠናቀቁን የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡ በአርባምንጭ፣ በሆሳዕናና በሚዛን አማን ከተሞች ከ30 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ተጨማሪ የትራፊክ ኮምፕሌክስ ግንባታ ለማካሄድ አሰፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁም ተገልጿል፡፡ በቢሮ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ዋና የስራ ሂደት አስተባበሪ አቶ ውቤ ለሳ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የክልሉ መንግስት በመደበው ወጪ የተጀመረው የተቋሙ ግንባታ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ ግንባታው ከሶስት ወር በኋላ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል፡፡ በክልሉ በየጊዜው የሚከሰተው የትራፊክ አደጋ በአብዛኛው የአሽክርካሪዎች ብቃት ማነስ ነው ያሉት አስተባባሪው ይህንና የቀድሞውን የመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ችግር በመቅረፍ ቀልጣፋ የአሽከርካሪዎች ምዘናን የሚያረጋግጥ ግልፅና ውጤታማ አሰራር ለመዘርጋት እንደሚያስችል የስራ ሂደቱ ባለቤት ተናግረዋል፡፡ በሃዋሳ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የአሽከርካሪዎች ምዘና የትራፊክ ኮምፕሌክስ ተቋም በኮምፒውተር መረጃ ኔትወርክ የተገናኙ የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎችና ዘመናዊና አዲስ የመፈተሻ ቴክኖሎጂ ይገኙበታል ብለዋል፡፡ አሰራሩን በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ የክልሉ መንግስት በመደበው 30 ሚሊዮን ብር በአርባምንጭ፣ በሆሳዕናና በሚዛን አማን ከተሞች የአሽከርካሪ ብቃት ምዘና የሚደረግባቸው ዘመናዊ የትራፊክ ኮምፕሌክስ ግንባታ ለማስጀመር ዝግጅቱ መጠናቀቁንና በሁለቱ ከተሞች ከያዝነው ወር ጀምሮ ስራው መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

የ121 ዓመት አድሜ ባለጸጋ የሆኑት የአቶ ጠቀቦ ሾታ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈጸመ::

ዲላ ሐምሌ 02/2005 የጌዴኦ አርሶ-አደር በነፍጠኛው ስርዓት ላይ ባካሄደው ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት እና የ121 ዓመት አድሜ ባለጸጋ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ። የአቶ ጠቀቦ ሾታ ቀብር በጌዴኦ ባህላዊ ስነ-ዓስርዓት በዲላ ዙሪያ ወረዳ ዛሬ ተፈጸመ ። አቶ ጠቀቦ ሾታ ከአስራ ሁለት ሚስቶቻቸው ሰማንያ ሰባት ልጆች እና ከአንድ ሺህ በላይ የልጅ ልጅ ያፈሩ እንደነበሩም በቀብር ስነስረአቱ ላይ በተነበበዉ የህይወት ታሪካቸው ላይ ተገልጿል ። አቶ ጠቀቦ ሾታ በ1884 ዓመተ ምህረት በዲላ ዙሪያ ወረዳ ሚቺሌ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መወለዳቸዉን ቀብር ስነ-ስርዓታቸው ላይ የተነበበው የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል ። በጌዴኦ አርሶ አደር ላይ ይደርስ የነበረውን የጭቆና አገዛዘ በጽኑ በመቃወም በ1952 ዓመተ ምህረት በነፍጠኛው ስርዓት ላይ ከፍተኛ ጥቃት በመሰንዘር የሚቺሌን ድል ካስመዘገቡ አባቶች መካከል አንዱ ነበሩ ። አቶ ጠቀቦ ሾታ ከዚህ የትጥቅ ትግል በመለስ በጌዴኦ ብሄርና በአጎራባች ወረዳዎች እና ክልል ህዝቦች መካከል ሰላማዊ ግንኙነት እንዲሰፍን በማድረግና ግጭቶች እንዳይከሰቱ የበኩላቸውን ከመወጣታቸውም ባሻገር የጌዴኦ ባህልን ለማሳደግ የዞኑን ልማት ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ተጠቁሟል ። በህዝባዊ ውይይቶች ህብረተሰቡን በመወከል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ በመሆን ለጌዴኦ ህዝብ እድገት የበኩላቸውን መወጣታቸውንና ለፈጸሙት መልካም ተግባር በጌዴኦ ባህል ለጀግና የሚሰጠውን የሀይቻነት ማእረግም ማግኘታቸውም ተመልክቷል ። የረጅም እድሜ ባለጸጋ የሆኑት አቶ ጠቀቦ ሾታ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ የደቡብ ብሄር ብሄርሰቦችና ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የጌዴኦ ዞን ካቢኔ አባላት የስድስቱም ወረዳና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁ