የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሸጉጤ በወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ለመምከርና ጥሩ የሥራ አፈጻጸም ያላቸውን ኢንቨስተሮች ለማበረታታት በጠሩት ስብሰባ ላይ፣ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ መማረራቸውን አስታውቀዋል፡፡
ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተማረሩ - ልማት ባንክ ቅሬታቸውን አልተቀበለም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከአዲስ አበባ 275 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሐዋሳ ከተማ የተሰበሰቡ ኢንቨስተሮች፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ብድር እየሰጠ አይደለም ሲሉ አማረሩ፡፡ ሐሙስ ሰኔ 27 ቀን 2005 ዓ.ም. የትምህርት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሸጉጤ በወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ለመምከርና ጥሩ የሥራ አፈጻጸም ያላቸውን ኢንቨስተሮች ለማበረታታት በጠሩት ስብሰባ ላይ፣ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ መማረራቸውን አስታውቀዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ‹‹በትራንስፎርመር እጥረት›› በሚል ምክንያት የኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግር እየገጠማቸው መሆኑን በመጥቀስ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ በተወሰነ ደረጃ በኢትዮ ቴሌኮም በኩልም ችግር መኖሩን የሚጠቅሱት ኢንቨስተሮች በክልሉ በኩልም የመሬት አቅርቦት፣ በዞኖችና ወረዳዎች የመልካም አስተዳደር እጦትና የወሰን ማስከበር ችግሮች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ በደቡብ ክልል ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም. ድረስ 6,150 ኢንቨስተሮች ፈቃድ አውጥተው ቦታ ወስደዋል፡፡ ለስብሰባ የተጠሩት ውጤታማ ናቸው የተባሉ 1,500 የአገር ውስጥና የውጭ አገር ኢንቨስተሮች ናቸው፡፡ ኢንቨስተሮቹ የተሰማሩት በእርሻ፣ በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎት መስጫዎችና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ነው፡፡ እነዚህ ኢንቨስተሮች ሥራቸውን ለማስፋፋት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ቢጠይቁም ሊሰጣቸው እንዳልቻለ፣ በአንፃሩ ባንኩ ለውጭ ኩባንያዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር ሲሰጥ መታዘባቸውን በመናገር ምሬታቸውን ገል