የአቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወደ ፌዴራል መንግሥት ሚኒስትርነት መምጣት በደቡብ ክልል ላይ ጊዜያዊ ክፍተት የፈጠረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ለክልሉ ፕሬዚዳንትነት የስድስት ግለሰቦች ስሞች እየተነሱ ነው፡፡
የአቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወደ ፌዴራል መንግሥት ሚኒስትርነት መምጣት በደቡብ ክልል ላይ ጊዜያዊ ክፍተት የፈጠረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ለክልሉ ፕሬዚዳንትነት የስድስት ግለሰቦች ስሞች እየተነሱ ነው፡፡ ከእነዚህ መካከል ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርነታቸው በመነሳት በኦሮሚያ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ደሚቱ ሃንቢሳ የተተኩት አቶ ደሴ ዳልኬ አንደኛው ናቸው፡፡ ሌሎቹ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ማርቆስ ተክሌና በአሁኑ ወቅት የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን የሚያገለግሉት አራት ግለሰቦች ናቸው፡፡ እነሱም አቶ ታገሰ ጫፎ፣ አቶ ዓለማየሁ አሰፋ፣ አቶ ሳኒ ረዲና አቶ ደበበ አሰፋ ናቸው፡፡ ግምት ከተሰጣቸው መካከል የበለጠ ከፕሬዚዳንትነት ሥልጣኑ ጋር በተደጋጋሚ ስማቸው እየተጠራ የሚገኘው አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ሲሆኑ፣ በሁለተኛ ደረጃ አቶ ደሴ ዳልኬ ሊሆኑ ይችላል የሚል ግምት አለ፡፡ ባለፈው ሐሙስ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የከፍተኛ መንግሥት ባለሥልጣናትን ሹመት በፓርላማ አፀድቀዋል፡፡ የአሥሩ አዲስ ተሿሚዎች ሹመት የፀደቀው በአንድ ድምፅ ተአቅቦና በአብላጫ ድምፅ ነው፡፡ ተሿሚዎቹ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ አማካይነት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ባለፈው ረቡዕ አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ኩማ ደመቅሳ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊስ ጉዳዮች አማካሪ ሆነው መመደባቸው ተገልጿል፡፡ በቅርቡ በፓርላማ የትምህርት ሚኒስቴርን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ በዘርፉ ለሚታዩ ችግሮች ከሚኒስትር ጀምሮ እስከታች ያሉ አመራሮችን የወቀሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ በአቶ ኃይለ ማርያም አዲስ ሹመትና ሽግሽግ ከትምህርት ሚኒስትርነታቸው ተነስተዋ