Posts

የቀድሞው የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ይሾማሉ

Image
ላለፉት ሶስት ዓመታት የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን የሰሩት አቶ ደሴ ዳልኬ፤ የደቡብ ክልል ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ሆነው እንደሚሾሙ ምንጮች ገለፁ፡፡ ላለፉት ስምንት ዓመታት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ያገለገሉት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከትላንት በስቲያ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን፤ እሳቸውን በመተካት አቶ ደሴ ዳልኬ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው ይሾማሉ ተብሏል፡፡ ባለፈው ሐሙስ በፓርላማ በተካሄደው የካቢኔ ሹመት ወ/ሮ ዳሚቱ ሐሚሳ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወቃል፡፡ በመጪው ሳምንት የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ የክልሉን ርዕሰ መስተዳደር ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ባለፈው ሳምንት ከአስር በላይ የሚኒስትሮች ሹመት በፓርላማ መጽደቁ ይታወቃል፡፡ http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=12564:%E1%8B%A8%E1%89%80%E1%8B%B5%E1%88%9E%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%88%A3%E1%8B%AD%E1%8A%95%E1%88%B5-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%89%B4%E1%8A%AD%E1%8A%96%E1%88%8E%E1%8C%82-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AD-%E1%8B%A8%E1%8B%B0%E1%89%A1%E1%89%A5-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8D-%E1%8D%95%E1%88%AC%E1%8B%9A%E1%8B%B3%E1%8A%95%E1%89%B5-%E1%88%86%E1%8A%90%E1%8B%8D-%E1%8B%AD%E1%88%BE%E1%88%9B%E1%88%89&Itemid=180

ትምህርት ሚኒስቴርነት፤ በማማረር ወይስ በማባረር…! ?

ትምህርት ሚኒስቴርነት፤ በማማረር ወይስ በማባረር…! ? መንጌ የነገረኝ ቀልድ ትቅደም፤ መንጌ ማለት አሉኝ ከምላቸው ጓደኞቼ ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እሳት የላሰ የአራዳ ልጅ ነው፡፡ “ካራዳ ልጅ ጋራ አብረው ቢሰደዱ፤ ባይበሉም ባይጠጡ ስንቅ ይሆናል ቀልዱ”  የተባለለት ጨዋታ አዋቂ! አንድ ሙዝ ነጋዴ ነበር አለኝ መንጌ… እሺ… ሙዙ ገበያ ሲያጣ ምን ያደርጋል መሰለህ… እ… የተሰቀለውን ያወርደዋል፡፡ መሬት የነበረውን መስቀያው ላይ ያንጠለጥለዋል፡፡ እንደርሱ ብቻ አይደለም፤ “ሙዝ አትፍዘዝ ተንቀሳቀስ…” ሲልም ያበረታታዋል… አለኝ፡፡ እኔ ፋራው የምጠይቀው ጥያቄ ነው እንጂ የሚገርመው… ከዛስ…  አልሸጥ ያለው ሙዝ ይሻጣል….  ወይስ ይንቀሳቀሳል…? መንጌ ይስቃል… እርስዎም ይሳቁ፡፡ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሙዙ ነጋዴ ናቸው፡፡ የሱቁ ባለቤቶች “እስቲ ደግሞ ለአኬር፤ ሙዝ አትፍዘዝ ተንቀሳቀስ” ይበሉ … ብለዋችው ይሁን; በራሳቸው ተነሳሽነት እንጃ ሞዛዞቻቸውን ቦታ አቀያይረዋቸዋል፡፡ (ሙዛ ሙዞቻቸውን ማለቴ ነው….) አቶ ሬድዋን የኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር… ተደርገዋል፡፡ የምርም ስለ ኢህአዴግዬ ዋይ ዋይ ለማለት እርሳቸው ሳይሻሏት አይቀሩም፡፡  ምክንያቱም አቶ በረከት ስምዖን ቻርጅ እንዳለቃቸው በጣም ያስታውቃሉ፡፡ (ጢን… ጢን.. ማለት ከጀመሩ ቆይተዋል) ስለዚህ ነጋ ጠባ ስለ ድርጅታቸው በየአደባባዩ እየተከሰቱ “በላውድ ስፒከር” ሊጮሁላት አይቻላቸውም፡፡ እናም፤ ባትሪ ፉሉ አቶ ሬድዋን መተካታቸው ለዚህ ቦታ ትክክል ይመስለኛል፡፡ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስቴር… ይሄኛው ያስቃል፡፡  የሰውዬው የስራ ልምድ እኮ አስተኳሽነት ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ የስራ ልምዳቸው እንደ ጥይት የሚተኳኮስ የትራንስፖርት ስርዓት ይዘረጉልናል፡፡ ብ

Ethiopia: Parliament Approves PM's Appointment of New Ministers_Hailemariam appointed Shiferaw Shigute as minister of education.

Image
House of Peoples Representatives today approved the appointment of ten ministers nominated by Prime Minister Hailmeriam Desalegn. Before announcing his appointments, PM Hailemariam told parliamentarians that Deputy Prime Minister Demeke Mekonnen is relieved of his post as minister of education. Hailemariam appointed Shiferaw Shigute as minister of education. Shiferaw has been serving as Chief Administrator of Southern Nations, Nationalities and Peoples' Region (SNNPR) since March 2006. Redwan Hussien, who was public mobilization and participation advisor minister to the PM and head of EPRDF Secretariat, has replaced Bereket Simon as Minister of Government Communications Affairs Office. Bereket and outgoing Addis Ababa City mayor Kuma Demeksa yesterday were appointed as policy and research advisor ministers to the Prime Minister. Workneh Gebeyehu, who was commissioner of the Federal Police Commission, is appointed as Minister of Transport replacing Diriba Kuma. Mekonnen

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወላሳ - የትምህርት ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ የመንግስት ሚኒስትሮችን እና የስራ ሃላፊዎችን ሹመት አጸደቀ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሰላኝ የቀረቡ እጩዎችን ሹመት በ1 ድምጸ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል። በዚህም መሰረት አቶ ደመቀ መኮንን - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወላሳ - የትምህርት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ራህመቶ-  የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር አቶ አህመድ አብተው አስፋው - የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ - የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ መሸሻ - በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ወይዘሮ ደሚቱ ሃንቢሳ ቦንሳ - የሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው አምባዬ በለው - የፍትህ ሚኒስትር አቶ በከር ሻሌ ዱሌ - የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ በለጠ ታፈረ ደስታ - የአካባቢ ጥበቃና የደን ሚኒስትር አቶ መኮንን ማንያዘዋል እንደሻው - የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን የተሾሙ ሲሆን ፥ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ አማካኝነት ቃለ መሃላቸውን ፈጽመዋል።

የስምንት ሚኒስትሮች ሹመት ሰሞኑን ይፀድቃል

የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ዛሬ ግምገማ ያካሂዳል የኢህአዴግ 36 ከፍተኛ መሪዎችን ያካተተው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመታዊ ግምገማ ለማካሄድ ዛሬ የሚሰበሰብ ሲሆን የስምንት ሚኒስትሮች ሹም ሽርና ሽግሽግ በሚቀጥለው ሳምንት ለፓርላማ ቀርቦ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል፡፡ ለሹመት የሚቀርቡት ባለስልጣናት፤ የፍትህ ሚኒስትር፣ የከተማና ኮንስትራክሽን ልማት ሚኒስትር፣ የግብርና ሚኒስትር፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር፣ የገቢዎች ሚኒስትር የደህንነትና መረጃ ሚኒስትር፣ የደንና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር እንዲሁም በፓርላማ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ናቸው ተብሏል፡፡ አንዳንዶቹ ሹምሽር እርምጃዎች ሲሆኑ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ወደ አዲስ አበባ አስተዳደር እንዲዛወሩ በተደረጉ ባለስልጣናት ምትክ የሚካሄድ ሽግሽግ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የእጩ ተሿሚዎችን ማንነት ለማወቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡ ዛሬ የሚካሄደው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ከሹምሽሩ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ቢታሰብም፣ የሰብስባው ዋና ርዕሰ ጉዳይ አመታዊ ግምገማና አመታዊ እቅድ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት አስፈፃሚ አካል የመቆጣጠር ስልጣን ያለው የአገሪቱ ፓርላማ ጠንካራ የቁጥጥር ሃላፊነቱን በተግባር ማሳየት እንደጀመረ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጭምር ቢናገሩም፤ በሚኒስትሮች ሹመት ዙሪያ ግን የቀድሞው አሰራር አልተሻሻለም፡፡ በተለያዩ ዲሞክራሲያዊ አገራት ውስጥ የእጩ ሚኒስትሮች ማንነት በይፋ ታውቆ ለበርካታ ሳምንታት በፓርላማና በዜጐች ዘንድ ውይይት የሚካሄድበት ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ግን የተሿሚዎች ማንነት የሚገለፀው ሹመታቸው በሚፀድቅበት እለት ነው፡፡ የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ዛሬ ስብሰባ እንደሚያካሂድ የገለፁት የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን፤ የስብሰባው ዓላማ የዓመቱን የስራ አፈፃፀም