Posts

የዘመን መለወጫ በሲዳማ

በሲዳማ የጊዜ አቆጣጠር መሰረት የሳምንቱ ቀናት በስም አራትናቸው። እነሱም ቃዋዶ፣ ቃዋላንካ፣ ዴላ፣ዲኮ በሚል መጠሪያ ተለይተው የታወቃሉ። እንዲሁም አንድ ወር አጋና (ጨረቃ) እና ቱንሲቾ(ጨለማ) ተብሎ በሁለት ይከፈላል። እያንዳንዱ ወር በቋንቋው ተለይቶ የሚታወቅበት የራሱ መጠሪያ (ሥያሜ) ያለው ሲሆን ፤ ወራቱ አስራ ሁለት ናቸው። በነባሩ የሲዳማ ባህላዊ የጊዜ አቆጣጠር ውስጥ ጷግሜ ፎቃ የሚል ስያሜ ተሰጥቶቷል።     በነባሩ የሲዳማ የጊዜ ቀመር አቆጣጠር መሰረት በዓመት ውስጥ ያሉት አስራ ሁለት ወራት በአራት ወቅቶች የተከፈሉ ናቸው። ከዚሁ አንጻር ወቅቶቹ አሮ(በጋ)፣ሀዋዶ(ክረምት)፣በዴሳ (በልግ) እና ቢራ (መኸር) የሚል መጠሪያ አላቸው። በባህሉና በጊዜ ቀመሩ መሰረት ሲዳማ የራሱ ዘመን መለወጫ ቀን አለው።ይህም ፍቼ በሚል መጠሪያ ይታወቃል።      የዘመን መለወጫ( ፍቼ) በአል አከባበር     ፍቼ በሲዳማ ባህል በዓመት አንዴ በድምቀት የሚከበር የዘመን መለወጫ በዓል ነው። በባህሉ መሰረት አከባበሩ እስከ ሁለት ሳምንት ይዘልቃል። የፍቼ በዓል ቅደም ተከተላዊ የአከባበር ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት ለአከባበሩ መነሻና መድረሻ የሚሆኑ ክንውኖች አሉ። ከእነዚህ ክንውኖች የመጀመሪያው ላኦ(ምልከታ) ነው። ላኦ ፍቼ መቼ እንደሚውል አያንቶዎች (የስነክዋክብት ተመልካቾች አረጋውያን) የጨረቃንና የከዋክብትን አካሄድ ጥምረት ተመልክተው የሚለዩት ሲሆን፤ አያንቶዎች ፍቼ ቀኑ መቼ እንደሚውል በከዋክብት ምልከታ ከለዩ በኋላ ለጎሳ መሪዎች ይገልጻሉ። የጎሳ መሪዎች ቀኑ ተገልጾ ለህብረተሰቡ እንዲለፈፍ ሲያዙ በገበያ ስፍራዎች በላላዋ (በልፈፋ) ይገለጻል። ላላዋ (ልፈፋ) የጎሳ መሪዎች ስር ባሉ ስፍራዎች የሚከወን ሲሆን ፤ ለፋፊዎች በገያ ቀን የበግ ቆዳ ረዠም ዘንግ ላይ ሰቅለው በመያዝ

ለእጩ ተመራቂ መምህራን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሊሰጥ ነው

Image
በዘንድሮው የትምህርት ዓመት ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ መምህራን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንደሚሰጣቸው የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡   ሚኒስቴር ዴኤታው አቶ ፉአድ ኢብራሂም እንደተናገሩት የትምህርተ ጥራትን ለማረጋገጥ በሚደርገው ጥረት የመምህራን የሞያ ብቃት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ምዘናው እጩ ተመራቂዎቹ ወደ ስራ ዓለም ከመግባታቸው በፊት እንዲሰጥ መደረጉ የትምህርት ጥራትን ለማምጣት የተዘረጋውን ፓኬጅ ውጤታማ በማድረግ ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል፡፡ በስራ ላይ ያሉት ነባር መምህራንም ምዘናውን እንዲወስዱ በማድረግ ወደሚፈለገው ደረጃ ለማምጣት ተከታታይ የሞያ ስልጠና ይሰጣል ማለታቸውን የዘገበው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንደገና ሊቋቋም ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኤጀንሲ በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ እንደገና ሊቋቋም ነው። የኤጀንሲው በአዲስ መልክ  መቋቋም ተልዕኮውን በላቀ ብቃት ለመወጣት ያስችለዋል የተባለ ሲሆን ተቋሙ  ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው ፥የሚመራውም በጠቅላይ ሚንስትሩ  በሚሾም ዳይሬክተር ጄኔራል   ይሆናል። ጥራት ያለው መረጃና አስተማማኝ የደህንነት አገልግሎት በመስጠት የአገሪቱን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነት ለዚህ ተቋም ተሰቶታል፡፡ በአገር ውስጥና በውጭ ሃገር የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ስራን በሃላፊነት በመምራት፤አስፈላጊ ሁኖ ከተገኘ ከውጭ ሃገር አቻ ተቋማት ጋር በትብብር መስራትና በጋራ ኦፕሬሽን ማካሄድም ለዚህ ተቋም ከተሰጡት ስልጣንና ተግባር ውስጥ ተጠቃሾች ናቸው። በአገሪቱ የኢኮኖሚ፣ እድገትና የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ሊቃጡ የሚችሉ ጥቃቶችንና የመልካም አስተዳደር አሻጥሮችን ተከታትሎ መረጃና ማስረጃ በማስባሰብ ለሚመለከታቸው አካላት እንዲያቀርብም አዲስ የሚቋቋመው ተቋም በአዋጁ ሃላፊነት ተጥሎበታል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መስሪያ ቤቱን በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ ለማቋቋም የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ተመልክቶ ለዝርዝር እይታ ወደ ሚመለከታቸው የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች መርቶታል። መስሪያ ቤቱ እንደገና እንዲቋቋም መደረጉም በሁሉም የምክር ቤቱ አባላት ዘንድ ድጋፍ  አግኝቷል ። ከዚህ በተጨማሪ በአዋጁ መሰረት የመረጃና የደህንነት ሙያ የስልጠናና የምርምር ተቋምም የሚቋቋም ይሆናል።

ውዝግብ ያስነሳው የአማራ ክልል ሕዝብ ቁጥር ከአምስት ዓመት በኋላ ተስተካከለ የሲዳማስ?

ውዝግብ ያስነሳው የአማራ ክልል ሕዝብ ቁጥር ከአምስት ዓመት በኋላ ተስተካከለ • ኮሚሽኑ የአማራ ክልል ሕዝብን ይቅርታ ይጠይቅ ተባለ •ኮሚሽኑ ስህተቱን የፈጠርኩት እኔ አይደለሁም ብሏል በ2001 ዓ.ም. ይፋ በተደረገው ሦስተኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት መሠረት የአማራ ክልል ሕዝብ ብዛት ከተገመተው በሁለት ሚሊዮን አንሶ በመገኘቱ የፈጠረውን ውዝግብና ኢተዓማኒነት ለመቅረፍ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በክልሉ ሕዝብ ብዛት ላይ በድጋሚ ጥናት እንዲካሄድ በወቅቱ በወሰነው መሠረት ጥልቅ ጥናት ተካሂዶ፣ የክልሉ ሕዝብ ቁጥር በ2.1 ሚሊዮን ከፍ ብሎ እንዲስተካከል የሚያስችል የዕድገት ምጣኔ ተገኘ፡፡  የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን በፓርላማው ውሳኔ መሠረት በሁለት ቆጠራዎች መካከል የሚደረግ ‹‹ኢንተር ሴንሳል›› ጥናት በ2004 ዓ.ም. በማካሄድ ያገኘውን ውጤት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሐሙስ አቅርቧል፡፡ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የስታትስቲክስ ባለሥልጣን ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሳሚያ ዘካሪያ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት፣ በ1999 ዓ.ም. እና በቀጣዩ ቆጠራ አጋማሽ ላይ በተደረገው ጥልቅ ጥናት በተገኘው ውጤት መሠረት የአማራ ክልል ሕዝብ ዓመታዊ የዕድገት ምጣኔ ከሌሎች ክልሎችና ከአገር አቀፍ ምጣኔው በታች 1.73 በመቶ መሆኑ ስህተት ነበር ብለዋል፡፡ ትክክለኛው የክልሉ የዕድገት ምጣኔም ከአገር አቀፍ ምጣኔው ጋር ተቀራራቢ የ2.3 በመቶ ዕድገት እንዳለው በጥናቱ መረጋገጡን ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡  በዚህ መሠረት በተስተካከለው የ2.3 ዓመታዊ የዕድገት ምጣኔ ሲሰላም የአማራ ክልል ሕዝብ በ2004 ዓ.ም. 19.2 ሚሊዮን መሆኑን ጥናቱ ማመልከቱን፣ ከዚህ በኋላም በዚህ ምጣኔ

Bamboo roundhouse by the Sidama people of Ethiopia

Image
This is a traditional split bamboo plaited roundhouse by the Sidama people of Ethiopia. The dome, with its pointy top, is designed to shed heavy rainfall where a circular dome would have a flat region prone to leaks. Bamboo once played an important role in the rural economies of East Africa but indiscriminate clearing of natural bamboo forests have resulted in losing natural resources and many of the traditional building skills. You can find out more about traditional bamboo construction at  The International Network for Bamboo and Rattan . http://naturalhomes.org/timeline/ethiopianroundhouse.htm