Posts

ለእጩ ተመራቂ መምህራን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሊሰጥ ነው

Image
በዘንድሮው የትምህርት ዓመት ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ መምህራን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንደሚሰጣቸው የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡   ሚኒስቴር ዴኤታው አቶ ፉአድ ኢብራሂም እንደተናገሩት የትምህርተ ጥራትን ለማረጋገጥ በሚደርገው ጥረት የመምህራን የሞያ ብቃት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ምዘናው እጩ ተመራቂዎቹ ወደ ስራ ዓለም ከመግባታቸው በፊት እንዲሰጥ መደረጉ የትምህርት ጥራትን ለማምጣት የተዘረጋውን ፓኬጅ ውጤታማ በማድረግ ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል፡፡ በስራ ላይ ያሉት ነባር መምህራንም ምዘናውን እንዲወስዱ በማድረግ ወደሚፈለገው ደረጃ ለማምጣት ተከታታይ የሞያ ስልጠና ይሰጣል ማለታቸውን የዘገበው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንደገና ሊቋቋም ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኤጀንሲ በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ እንደገና ሊቋቋም ነው። የኤጀንሲው በአዲስ መልክ  መቋቋም ተልዕኮውን በላቀ ብቃት ለመወጣት ያስችለዋል የተባለ ሲሆን ተቋሙ  ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው ፥የሚመራውም በጠቅላይ ሚንስትሩ  በሚሾም ዳይሬክተር ጄኔራል   ይሆናል። ጥራት ያለው መረጃና አስተማማኝ የደህንነት አገልግሎት በመስጠት የአገሪቱን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነት ለዚህ ተቋም ተሰቶታል፡፡ በአገር ውስጥና በውጭ ሃገር የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ስራን በሃላፊነት በመምራት፤አስፈላጊ ሁኖ ከተገኘ ከውጭ ሃገር አቻ ተቋማት ጋር በትብብር መስራትና በጋራ ኦፕሬሽን ማካሄድም ለዚህ ተቋም ከተሰጡት ስልጣንና ተግባር ውስጥ ተጠቃሾች ናቸው። በአገሪቱ የኢኮኖሚ፣ እድገትና የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ሊቃጡ የሚችሉ ጥቃቶችንና የመልካም አስተዳደር አሻጥሮችን ተከታትሎ መረጃና ማስረጃ በማስባሰብ ለሚመለከታቸው አካላት እንዲያቀርብም አዲስ የሚቋቋመው ተቋም በአዋጁ ሃላፊነት ተጥሎበታል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መስሪያ ቤቱን በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ ለማቋቋም የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ተመልክቶ ለዝርዝር እይታ ወደ ሚመለከታቸው የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች መርቶታል። መስሪያ ቤቱ እንደገና እንዲቋቋም መደረጉም በሁሉም የምክር ቤቱ አባላት ዘንድ ድጋፍ  አግኝቷል ። ከዚህ በተጨማሪ በአዋጁ መሰረት የመረጃና የደህንነት ሙያ የስልጠናና የምርምር ተቋምም የሚቋቋም ይሆናል።

ውዝግብ ያስነሳው የአማራ ክልል ሕዝብ ቁጥር ከአምስት ዓመት በኋላ ተስተካከለ የሲዳማስ?

ውዝግብ ያስነሳው የአማራ ክልል ሕዝብ ቁጥር ከአምስት ዓመት በኋላ ተስተካከለ • ኮሚሽኑ የአማራ ክልል ሕዝብን ይቅርታ ይጠይቅ ተባለ •ኮሚሽኑ ስህተቱን የፈጠርኩት እኔ አይደለሁም ብሏል በ2001 ዓ.ም. ይፋ በተደረገው ሦስተኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት መሠረት የአማራ ክልል ሕዝብ ብዛት ከተገመተው በሁለት ሚሊዮን አንሶ በመገኘቱ የፈጠረውን ውዝግብና ኢተዓማኒነት ለመቅረፍ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በክልሉ ሕዝብ ብዛት ላይ በድጋሚ ጥናት እንዲካሄድ በወቅቱ በወሰነው መሠረት ጥልቅ ጥናት ተካሂዶ፣ የክልሉ ሕዝብ ቁጥር በ2.1 ሚሊዮን ከፍ ብሎ እንዲስተካከል የሚያስችል የዕድገት ምጣኔ ተገኘ፡፡  የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን በፓርላማው ውሳኔ መሠረት በሁለት ቆጠራዎች መካከል የሚደረግ ‹‹ኢንተር ሴንሳል›› ጥናት በ2004 ዓ.ም. በማካሄድ ያገኘውን ውጤት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሐሙስ አቅርቧል፡፡ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የስታትስቲክስ ባለሥልጣን ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሳሚያ ዘካሪያ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት፣ በ1999 ዓ.ም. እና በቀጣዩ ቆጠራ አጋማሽ ላይ በተደረገው ጥልቅ ጥናት በተገኘው ውጤት መሠረት የአማራ ክልል ሕዝብ ዓመታዊ የዕድገት ምጣኔ ከሌሎች ክልሎችና ከአገር አቀፍ ምጣኔው በታች 1.73 በመቶ መሆኑ ስህተት ነበር ብለዋል፡፡ ትክክለኛው የክልሉ የዕድገት ምጣኔም ከአገር አቀፍ ምጣኔው ጋር ተቀራራቢ የ2.3 በመቶ ዕድገት እንዳለው በጥናቱ መረጋገጡን ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡  በዚህ መሠረት በተስተካከለው የ2.3 ዓመታዊ የዕድገት ምጣኔ ሲሰላም የአማራ ክልል ሕዝብ በ2004 ዓ.ም. 19.2 ሚሊዮን መሆኑን ጥናቱ ማመልከቱን፣ ከዚህ በኋላም በዚህ ምጣኔ

Bamboo roundhouse by the Sidama people of Ethiopia

Image
This is a traditional split bamboo plaited roundhouse by the Sidama people of Ethiopia. The dome, with its pointy top, is designed to shed heavy rainfall where a circular dome would have a flat region prone to leaks. Bamboo once played an important role in the rural economies of East Africa but indiscriminate clearing of natural bamboo forests have resulted in losing natural resources and many of the traditional building skills. You can find out more about traditional bamboo construction at  The International Network for Bamboo and Rattan . http://naturalhomes.org/timeline/ethiopianroundhouse.htm

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በይፋ ተቋቋመ፤ ችግር ፈቺ የምርምርና የጥናት ስራዎችን እንዲያከናውን መንግሥት ተገቢውን ድጋፍ ይሰጣል

Image
አዲስ አበባ ሰኔ 13/2005 ዛሬ በይፋ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የአገሪቱን ልማት የሚያግዝ ስኬታማ ምርምርና ጥናቶችን እንዲያደርግ ለማስቻል መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለፀ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው የአካዳሚው ይፋዊ የማቋቋሚያ ጉባዔ ላይ የተገኙት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አቶ ደሴ ዳልኬ እንዳስታወቁትአካዳሚው በአገሪቱ ችግር ፈቺ የምርምርና የጥናት ስራዎችንና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማትን ለማሳደግ ትልቅ አቅም ይፈጥራል። የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ደምሴ ኃብቴ በበኩላቸው አካዳሚው ለአገሪቱ ልማት ጠቀሜታ ያላቸውን የተለያዩ የምርምር ስራዎች ለመስራት የአካዳሚው አባላት በአምስት የተለያዩ መስኮች ተከፍለው የጥናትና ምርምር ስራዎችን እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። አካዳሚው እስካሁን በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የሚሰሩ የምርምር ተቋማትን ግንኙነት፣ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ጥራት፣ በግብርና እና በጤና መካከል ያለው የፖሊሲ ቅንጅት ምን እንደሚመስል ጥናት አድርጓል። አካዳሚው የሚያወጣቸው የምርምርና የጥናት ስራዎች የኅብረተሰቡን ኑሮ የመለወጥ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ስራዎቹ ወደ ተግባር የሚሸጋገሩበትን አሰራር እንደሚከተልም ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል። ፕሮፌሰር ደምሴ እንዳሉት አካዳሚው በመጪው ኅዳር ወር በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የአፍሪካ የሳይንስ አካዳሚ ጉባዔን ለማስተናገድ የሚያስችሉ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ሚኒስትሮችና ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የአካዳሚው መስራች አባላት ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች በሳይንስ ማህበረሰቡ በ