በጥረት የተገኘ ስኬት
በጥረት የተገኘ ስኬት /ከበለጠ አድነዉ /ሃዋሳ ኢዜአ/ ቁጠባ የግለሰብን ኑሮ ከመቀየር ጀምሮ ለሀገር እድገት የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው፡፡ዛሬ በዓለማችን ላይ አንቱ ተብለው የሚጠቀሱ ባለሀብቶች ምንጫቸው ትንሿን ገንዘብ ብዙ እንድትሆን በተለያዩ የቆጠባ ዘዴዎች ቆጥበው ነው፡፡አሁን አሁን በተለያዩ ተቋማት ውስጥ በሚቋቋሙ የብድርና ቁጠባ ተቋማት፣በባንክ፣በማህበራትና በሌሎችም የቆጠባ ዘዴዎች በመቆጠብ በርካቶች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡በዚህም በርካታ ወገኖች ኑሯችውን ቀይረውበታል፡፡ ወይዘሮ አበባ ዘነበ ይባላሉ፡፡የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡ባለቤታቸው ከብድርና ቁጠባ ተቋም ባገኙት 500 ብር መነሻ ካፒታል የጀመሩት ባህላዊ የአልባሳት ጥልፍ ሥራ ስኬታማ አያደረጋቸው ነው፡፡የጥልፍ ሥራው በአጭር ጊዜ ውስጥ ትርፋማ ስላደረጋቸው ዘመናዊ የጠረጴዛና የጥልፍ ስፌት ማሽኖችን ገዝተው የብሄረሰቦችን ልዩ ልዩ አልባሳት በማዘጋጀትና በማስተዋወቅ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ወይዘሯዋ በራሳችን ባህላዊ አልባሳት መዋብ እንችላለን ብለው በመነሳሳት ሳይታከቱ በመስራታቸው ዛሬ ከከተማውና ከክልሉ አልፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝተው ለተለያዩ ስብሰባዎች፣ ለጉብኝትና ለበአላት የሚውሉ አልባሳት እንዲዘጋጅላቸው በርካታ ጥያቄዎች እየቀረበላቸው ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ኢንባሲዎች ሳይቀሩ የየሀገራቸው የባህል ልበስ እንዲዘጋጅላቸው ጥያቄ እያቀረቡላቸው መሆኑን ይናገራሉ፡፡የአካባቢው አስተዳደር የስራ ውጤታቸውን በማየት የመስሪያ ቦታ፣ የሙያና የምክር ድጋፍ በመስጠት የሚያደርግላቸው እገዛ ለስራቸው መሻሸል ከፍተኛ ብርታት ሆናቸዋል፡፡ ወይዘሮ አበባ በአሁኑ ወቅት ኑሮአቸውን ከመለወጣቸውም በላይ ካፒታላቸው 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ደርሷ