Posts

BIRDS IN THE STREETS

Image
Amora Gedel or roughly ‘Eagle’s Valley’ in Hawassa of the Southern Region is home toLakeHawassa, the chosen playground and home of Marabou Storks (locally known as Aba Koda). Fishermen and some tourists that work at and visit the lake have gotten these large birds hooked on the fish they throw to them. These days, you are more likely to find the humungous birds roaming the asphalt of the parking lots than at the edge of the lake, on their usual stomping grounds. http://addisfortune.net/articles/birds-in-the-streets/

ECX Exclusive Cooperative Auction Falls Short of Expectations

Image
Exclusive auction for farmer cooperative seats only rejects one offer and accepts the rest The Ethiopian Commodity Exchange’s (ECX) exclusive auction for farmers’ cooperatives seats attracted few and vastly differing offers, all but one of which were declared winners for the seats they sought. The Exchange has a total of 329 seats, 15 of which are held by farmers’ cooperatives. These cooperatives are even less significant in their trading participation, accounting for just 2.2pc of the 601,000tns traded in 2012. The reason for their low presence, according to both cooperatives and the ECX, is that they are permitted to bypass the Exchange in exporting their products. Additionally, most of them happen to have a limited financial capacity to compete with businesses for auctioned seats. ECX’s seats, which were auctioned at a starting price of 50,000 Br when the Exchange was launched in 2008, reached an average of 1.35 million Br in 2012, with the highest offer being 3.5 mil

ተቃዋሚዎች የሙስና እርምጃው ፖለቲካዊ እንዳይሆን ሰግተዋል

ኢህአዴግም እንደ ድርጅት ሙሰኛ ነው - ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ገቢዎች ከመንግስትም በላይ ስልጣን የተሰጠው አካል ነው - አቶ ሙሼ ሰሙ ማጥመጃው ትላልቅ ዓሳዎችን ካጠመደ እንተባበራለን - ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም የእርምጃውን አቅጣጫ ለማወቅ ቀጣዩን ማየት ያስፈልጋል - ዶ/ር መረራ ጉዲና በፌዴራል የፀረ ሙስና ኮሚሽን በሙስና ተጠርጥረው የተያዙ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጉዳይ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ እንዳይሆን ስጋት አለን የሚሉ ተቃዋሚዎች፤ እውነቱን የምናውቀው በእርምጃው ቀጣይነት ነው ብለዋል፡፡ መንግስት አላማው ሙስናን ማጥፋት ከሆነ ግን የሚደነቅና የሚበረታታ ተግባር ነው ሲሉ አወድሰዋል፡፡ አሁን የተወሠደው እርምጃ ግዙፉን የሙስና ችግር ዝም ብሎ መነካካት ነው ያሉት የመድረክ አመራር አባል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ኢህአዴግ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል ማለት አይቻልም፤ አሁንም ትልልቅ አሳዎች አልተነኩም ብለዋል፡፡ በመላ ሃገሪቱ ሙስና መስፋፋቱን የሚናገሩት ፕ/ር በየነ፤ ራሱ ገዢው ፓርቲ የሚያንቀሣቅሣቸው የንግድ ድርጅቶች ከሙስና የፀዱ አይደሉም በማለት ተችተዋል፡፡ የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ ሙሼ ሠሙ በሙስና የተጠረጠሩ ባለስልጣኖችና ባለሃብቶች ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉን ቢደግፉም ዋነኛ የችግሩ ምንጭ ግለሰቦች ሳይሆኑ ስርአቱ ነው ይላሉ፡፡ ስርአቱ ለእነዚህ ባለስልጣናት የመደራደርያ በር ስለከፈተላቸው የፈለጉትን ነጋዴ በፈለጉት ጊዜ ጠርተው እያሸማቀቁና ስሙን እያጠፉ በጠላትነት የሚያዩበት ሁኔታ ካልተቀየረ ሙስናን ማጥፋት አይቻልም ብለዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹን ማሰር ሙስናን የመዋጋት አካል መሆኑን ጠቁመው፤ ዋናው ግን የአስተሳሰብ ለውጥ ነው ባይ ናቸው - አቶ ሙሼ፡፡ የቀድሞው የቅንጅት አመራር አባልና አለማቀፍ የህግ ምሁሩ ዶ/ር ያዕቆብ ሃ/ማርያም

በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ ተማሪዎችና ወላጆችን በማሳተፍ ተግባራዊ የሆነዉ የማስተማር ዘዴ ዉጤት እያስገኘ ነዉ

Image
አዋሳ ግንቦት 13/2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ በትምህርት ስራው ላይ ተማሪዎችና ወላጆችን በማሳተፍ የተከናወነዉ ተግባር በተማሪዎች ውጤት ላይ ለውጥ ማምጣት መቻሉን የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አዝመራ አመኑ በወረዳው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በትምህርት ቤቶች ምምህራንና ተማሪዎች ዕቅድ በማውጣትና ተግባራዊ በማድረግ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ። በወረዳው በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆችን መሰረት በማድረግ ትምህርት ቤቶች ለትምህርት ስራው ምቹ እንዲሆኑ የተደረገዉ ጥረትም ለዉጤቱ መገኘት አስተዋጽኦ ማድረጉንም ገልጠዋል ። ለአራተኛና ስምንተኛ ክፍል የቲቶሪያል ማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት እንዲሁም ከአስረኛ ክፍል ጀምሮ ላሉት ተማሪዎች ከመደበኛው የትምህርት ሰዓት በተጨማሪ ቅዳሜን ጨምሮ ዘወትር ማታ ማታ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል። በወረዳው የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎና ውጤት ለማሻሻል ሴት ተማሪዎች ተለይተው ድጋፍ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን በወረዳው የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በቡድን በማደራጀት እርስ በእርስ ውድድር እንዲያደርጉና ተማሪዎች የልምድ ልውውጥ እንዲያገኙም እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ለአራተኛና ስምንተኛ ክፍል ወረዳ አቀፍ ፈተና አዘጋጅቶ በመፈተን ያሉ ክፍተቶችን ለይቶ የማካካሻ ትምህርት በመስጠት ለክልላዊ ፈተና ዝግጁ እንዲሆኑ የማድረግስራ እየተሰራ መሆኑንም አቶ አዝመራ ገልጸዋል። የሸበዲኖ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ጋቤራ በበኩላቸው በወረዳው በሚገኙ 35 ቀበሌዎች የወላጅ መምህራን ህብረትን በማጠናከርና በየደረጃው በተዋቀሩ የልማት ቡድኖችና አንድ ለአምስት ትስስሮች አማካኝነት በት

ልቅሶ የተካው የእልልታ ቀን

Image
‹‹የጨቅላ ሕፃናትን ሞት ቅነሳ በተመለከተ እ.ኤ.አ በ2015 እናሳካዋለን ያልነውን የሚሌኒየሙን ግብ አሁን በያዝነው አሠራር የምንቀጥል ከሆነ ግቡ ጋር ለመድረስ ተጨማሪ 150 ዓመት ያስፈልገናል፡፡›› ይህንን የተናገሩት የሕፃናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ችልድረን) የኦፕሬሽን ክፍል ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ኃይሉ ተስፋዬ ናቸው፡፡ ሁለት ዓመት ከሰባት ወር ገደማ ከቀረው ከሚሌኒየሙ እቅዶች መካከል አንዱ የሕፃናትና የእናቶች ሞት ቅነሳ ነው፡፡ ዶክተር ኃይሉም ግቡን ለማሳካት አሠራሮች ይቀየሩ የሚለውን ሐሳባቸውን ያንፀባረቁት፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜና እሑድ በሐዋሳ ከተማ በተደረገው የ‹‹ሁሉም›› የእናቶችና ሕፃናት ሞት ቅነሳ ዘመቻ ላይ ነው፡፡  እ.ኤ.አ በ2015 ይሳካል የተባለለት ትልቁ ዕቅድ ጨቅላ ሕፃናት በተወለዱ በ24 ሰዓታትና በተወለዱ በመጀመርያዎቹ ሰባት ቀናት ውስጥ ተገቢው ክትትል ካልተደረገላቸው መሞታቸው ቀጥሎ ግቡም አይሳካም፡፡ በዚህ አሠራር ከተቀጠለ ግን ግቡን ለማሳካት እ.ኤ.አ 2165 ድረስ መቆየት ግድ እንደሚል ዶክተሩ አስረድተዋል፡፡  የእናቶችን ሞት መቀነስን በተመለከተ ደግሞ የቤተሰብ ምጣኔ፣ የእርግዝና ክትትል፣ የወሊድና ከወሊድ በኋላ የሚደረግ ክትትልና እንክብካቤ ከመቼውም በላይ የሚሠራባቸው ከሆነ የሚሌኒየሙን ግብ ማሳካት እንደሚቻል እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡  የ‹‹ሁሉም›› ዘመቻ የእናቶችና ሕፃናት ሞት ቅነሳን ለማሳካት በዘመቻ መልኩ በሕፃናት አድን ድርጅት ሥር ከተመሠረተ አራት ዓመት ሆኖታል፡፡ በ36 አገሮች በየዓመቱ እየተከናወነ የሚገኘው ይህ ዘመቻ፣ የእናቶችና ሕፃናት ሞት የሚበዛባቸው አካባቢዎች ላይ ማኅበረሰቡን በዘመቻው አነሳስቶ የሞቱን ቅነሳ ለማድረግ ጥረት የሚደረግበት ፕሮግራም ነው፡፡   የሕፃናት