Posts

Visit Ethiopia : Hawassa በቅርቡ ኣየር ላይ የዋለ እና የሲዳማን ዋና ከተማ ሃዋሳን ለቱሪዝም የሚያስተዋውቅ ፕሮግራም

Visit Ethiopia : Hawassa

የሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ለታላቁ የህዳሴው ግድብ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ

አዋሳ ግንቦት 10/2005 የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ለመገንባት የላቀ አስተዋጾኦ ያለውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ስራን ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ገለጹ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለህዳሴው ግድብ ድጋፍ ለማሰባሰብ ላለፉት ስምንት ወራት ሲያደርግ የቆየውን ሀገራዊ የንቅናቄ ፕሮግራም አስመልክቶ ትናንት ማምሻውን የሎተሪ ማውጣት፣ የሽልማትና የኪነ ጥበብ ዝግጅቶችን አቅርቧል፡፡ የህብረቱ ፕሬዝዳንት ተማሪ ወንደወሰን እንዳለ እና የክለብ ኢኒሼቲቭ ተጠሪ ተማሪ ብሩክ በቀለ እንደገለጹት የግድቡ ግንባታ መሰረት ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ የሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ ሁሉም ተማሪዎች በእኔነት ስሜት በስራው ላይ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ አስተባባሪ ኮሚቴዎችን አቋቋሙው በዋናው ግቢና በአምስቱም የዩኒቨርስቲው ካምፓሶች ለተማሪዎች ተደራሽ በመሆን ባደረጉ እንቅስቀሴ ከቀለባቸው በመቀነስና ከሎቶሪ ሽያጭ 200 ሺህ የሚጠጋ ብር አሰባስበዋል፡፡ በሀዋሳ ከተማና አካባቢው በሚገኙ ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች ተዘዋውረው በመቀሳቀስ ስለግድቡ አላማና ፋይዳ ያለውን ግንዛቤ የማስፋት ስራ ማከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡ እስከ ህዳሴው ግድብ ግንባታ ቦታ ድረስ በመሄድ ባዩት ስራ ከፍተኛ ኩራት እንደተሳማቸውንና በትምህርት ላይ እያሉም ሆነ ተመርቀው ከወጡ በኋላ ከገንዘብ ባሻገር በየሰለጠኑበት መስክ ለሀገራቸው ልማትና ፈጣን እድገት የበኩላቸው ለመወጣት ትልቅ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው አስረደተዋል፡፡ ተማሪ ታደለ ቤዛና ተማሪ ፌቨን አብረሃም በበኩላቸው አባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው የህዳሴው ግድብ የሁሉም ዜጋ ሀገራዊ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ በራሳቸው በኩል የዩኒቨርስቲው

በ200 ሚ.ብር የተሰራ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ዛሬ በሐዋሳ ይመረቃል

Image
በግል ባለሀብቷ በወ/ሮ አማረች ዘለቀ በ200 ሚሊዮን ብር የተሠራው ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ዛሬ ይመረቃል፡፡ ዘመናዊው ሴንትራል ሐዋሳ ሆቴል ባለ መንታ ሕንፃ ሲሆን 70 የመኝታ ክፍሎች፣ ከ40 እስከ 1ሺ ሰዎች መያዝ የሚችሉ ሰባት የመሰብሰቢያ አዳራሾች አሉት፡፡ የመዋኛ ገንዳ፣ የወንዶችና የሴቶች ስፓ፣ የወንዶችና የሴቶች የውበት ሳሎን፣ ፑል ባር፣ ናይት ክለብ፣ አካባቢው እየቃኙ የሚዝናኑበት ቴራስ ባር፣ ጂምናዚየም ሬስቶራንት፣ ኮኒ ባር እንዲሁም ጊዜያዊ የእንግዶች ማረፊያ እንዳለውም ታውቋል፡፡ በምድር ቤቱ የመኪና ማቆሚያ ያለው ሆቴሉ፤ የንጽህና መስጫ ላውንደሪ፣ የባንክ አገልግሎትና የጉዞ ወኪል ቢሮዎችን በማሟላት ባለ 5 ኮከብ የሚያሰኘውን ደረጃ የያዘ መሆኑን ባለቤቷ ገልፀዋል፡፡ የሆቴሉ ግንባታ በሦስት ዓመት በመጠናቀቁ የከተማው አስተዳደር “የጊዜ ገደቡን በተገቢው መንገድ የተጠቀመ ኢንቨስትመንት” ሲል አወድሶታል፡፡ ከትንሽ ደረጃ ተነስተው የትልቅ ኢንቨስትመንት ባለቤት ለመሆን የበቁት ወ/ሮ አማረች ዘለቀ፤ ጽናት በተመላበት ብርታታቸው ለሴቶች ትልቅ አርአያ ሆነዋል ተብሏል፡፡ ሆቴሉ ለ250 ዜጐች የሥራ ዕድል መፍጠሩ ታውቋል፡፡ http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=12320:%E1%89%A0200-%E1%88%9A%E1%89%A5%E1%88%AD-%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%88%B0%E1%88%AB-%E1%89%A3%E1%88%88-5-%E1%8A%AE%E1%8A%A8%E1%89%A5-%E1%88%86%E1%89%B4%E1%88%8D-%E1%8B%9B%E1%88%AC-%E1%89%A0%E1%88%90%E1%8B%8B%E1%88%B3-%E1%8B%AD%E1%88%98%E1%88%A8%E1%89%83%E1%88%

ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል ከ3 ሺህ 600 በላይ የቀበሌ ስራ አስኪያጆች የተሳተፉበት የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተካሄደ ነው፡፡

አዋሳ ግንቦት 09/2005 ህብረተሰቡን በቀበሌ ደረጃ ለሚያገለግሉ ስራ አስኪያጆች የተዘጋጀ ክልል አቀፍ የማስፈጸም አቅም ግንባታ ስልጠና በአምስት ማዕከላት እየተካሄደ መሆኑን የደቡብ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳደርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሀላፊ አስታወቁ፡፡ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የቢሮው ሀላፊ አቶ ታገሰ ጫፎ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት የፕሮግራሙ አላማ የመንግስት የመልካም አስተዳደር፣ የልማትና የለውጥ ስራዎች ዋና ማስፈጸሚያው ህብረተሰቡ በቅርበት በሚገኝበት በቀበሌ ደረጃ በመሆኑ ይህንን እንዲመሩና እንዲያስተባበሩ የተቀጠሩ የቀበሌ ስራ አሲኪያጆች ያሉባቸውን የማስፈጸም ብቃት ክፍተቶችን በመለየት አቅማቸውን ለመገንባት ነው፡፡ ከሁሉም የክልሉ የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች ለተወጣጡ ከ3 ሺህ 600 ለሚበልጡ ስራ አስኪያጆች የተዘጋጀው የማስፈጸም አቅም ግንባታ የስልጠና ፕሮግራም ከግንቦት 5 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሀዋሳ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በአርባ ምንጭ፣ በሆሳዕናና በሚዛን አማን ማዕከላት እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡ በተጠቀሱት አምስት ማዕከላት ሰልጣኞቹ በቆይታቸው በተሀድሶ መስመርና በኢትዮጵያ ህዳሴ፣ በመልካም አስተዳደር፣ በቀበሌ መረጃ አያያዝና አደረጃጀት፣ በቀበሌ ጽህፈት ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ፣ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስነ ስርዓት፣ በውጤት ተኮር ስርዓትና የተቀናጀ ዕቅደ ዝግጅት ዙሪያ በባለሙያዎች ትምህርት እንደሚሰጥና የጋራ ውይይትም እንደሚካሄድ አስረድተዋል፡፡ በየቀበሌው የሚኖረው ህብረተሰብ ከመንግስት የሚፈልገውን ማንኛውንም አገልግሎት ወደ ወረዳ፣ ዞንና ክልል መሄድ ሳይስፈልገው እዚያው ባለበት ቀበሌ መጠቀም እንዲችል በክልሉ ሁሉም የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች ስራ አስኪያጆች ተቀጥረውና ጽህፈት ቤቶች ተከፍተው ህብረተሰቡን እንዲያገለግ

EEPCo to Pay Compensation for Hawassa Power Surges

Image
The Hawassa branch of the Ethiopian Electric Power Corporation (EEPCo) is to pay compensation to close to 300 households and a private company, Awassa Greenwood Plc, for damages related to sudden power surges, two weeks ago. Awassa Greenwood Plc, a flower grower and exporter located on the outskirts of Hawassa town, 273Km south of Addis Abeba, has stopped work because of damages to its offices and facilities that resulted in a fire following the surge. “We have checked the damages and confirmed that the charges were filed within 24 hours of the damages,” said Zeleke Kebede, Public Communication Desk head of EEPCo’s branch office. “We only pay compensation to residents with title deeds.” “The fire spread at Greenwood because they use metal sheets for fences,” he added. Residents of rented houses in the town are also demanding compensation; however, there are fears that they may be excluded because they do not have any title deeds for the places they reside in. “We should b