ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል ከ3 ሺህ 600 በላይ የቀበሌ ስራ አስኪያጆች የተሳተፉበት የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተካሄደ ነው፡፡
አዋሳ ግንቦት 09/2005 ህብረተሰቡን በቀበሌ ደረጃ ለሚያገለግሉ ስራ አስኪያጆች የተዘጋጀ ክልል አቀፍ የማስፈጸም አቅም ግንባታ ስልጠና በአምስት ማዕከላት እየተካሄደ መሆኑን የደቡብ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳደርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሀላፊ አስታወቁ፡፡ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የቢሮው ሀላፊ አቶ ታገሰ ጫፎ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት የፕሮግራሙ አላማ የመንግስት የመልካም አስተዳደር፣ የልማትና የለውጥ ስራዎች ዋና ማስፈጸሚያው ህብረተሰቡ በቅርበት በሚገኝበት በቀበሌ ደረጃ በመሆኑ ይህንን እንዲመሩና እንዲያስተባበሩ የተቀጠሩ የቀበሌ ስራ አሲኪያጆች ያሉባቸውን የማስፈጸም ብቃት ክፍተቶችን በመለየት አቅማቸውን ለመገንባት ነው፡፡ ከሁሉም የክልሉ የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች ለተወጣጡ ከ3 ሺህ 600 ለሚበልጡ ስራ አስኪያጆች የተዘጋጀው የማስፈጸም አቅም ግንባታ የስልጠና ፕሮግራም ከግንቦት 5 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሀዋሳ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በአርባ ምንጭ፣ በሆሳዕናና በሚዛን አማን ማዕከላት እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡ በተጠቀሱት አምስት ማዕከላት ሰልጣኞቹ በቆይታቸው በተሀድሶ መስመርና በኢትዮጵያ ህዳሴ፣ በመልካም አስተዳደር፣ በቀበሌ መረጃ አያያዝና አደረጃጀት፣ በቀበሌ ጽህፈት ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ፣ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስነ ስርዓት፣ በውጤት ተኮር ስርዓትና የተቀናጀ ዕቅደ ዝግጅት ዙሪያ በባለሙያዎች ትምህርት እንደሚሰጥና የጋራ ውይይትም እንደሚካሄድ አስረድተዋል፡፡ በየቀበሌው የሚኖረው ህብረተሰብ ከመንግስት የሚፈልገውን ማንኛውንም አገልግሎት ወደ ወረዳ፣ ዞንና ክልል መሄድ ሳይስፈልገው እዚያው ባለበት ቀበሌ መጠቀም እንዲችል በክልሉ ሁሉም የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች ስራ አስኪያጆች ተቀጥረውና ጽህፈት ቤቶች ተከፍተው ህብረተሰቡን እንዲያገለግ