Posts

አመራሩ የኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከምንጩ ለይቶ መታገል ይገበዋል-የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር

Image
አዋሳ ግንቦት 01/2005 የኪራይ ስብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከምንጩ በመለየት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አመራሩ መረባረብ እንዳለበት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አሳሰቡ፡፡ በክልል የሚገኙ ከአንድ ሺህ በላይ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በከተሞች የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰራዊት ግንባታ አፈፃፀም ያለበት ሁኔታና ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ላይ ለሁለት ቀን ያካሄዱት ውይይት ትናንት ማምሻው ተጠናቋል፡፡ ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት በከተሞች የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አንድ በአንድ ለይቶ በማውጣት ለህብረተሰቡ ተገቢውን ምላሽ መስጠት የአመራሩ ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ በየከተሞች ጎልቶ እየታየ ለመጣው የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዋናነት ተጠያቂው አመራሩ በመሆኑ እነዚህን ችግሮች ሌት ከቀን በመረባረብ መፍታት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ የከተማ ነዋሪዎች ለልማት ስራዎች ያላቸውን ፍላጎትና መነሳሳት አደራጅተውና አቀናጅቶ በመምራት፣ ይህን የልማት አቅም የመጠቀም ውስንነት በአመራሩ ዘንድ በሰፊው የሚታዩ ችግሮች ስለሆነ በፍጥነት ተፈቶ ወደ ስራ መገባት አለበት ብለዋል፡፡ በከተሞች ከዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ ያሉ ስራዎችን አንድ በአንድ የመፈተሽ፣ በልማት ሰራዊት የሚሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን በየቀኑ የመከታተል፣ እንዲሁም ለስራው ስኬት የሚያግዙ ግብአቶችን በወቅቱ የማቅረብ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰቶ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በከተሞች የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ዓለማ ለማሳካት የዜጎች፣ የባለሙያዎች፣ የባላሃብቶችና የአመራሮች መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ የሚጠይቅ ቢሆንም አመራሩ የመሪነት ሚናውን በተገቢው መንገድ ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ጠንካራ የልማ

አማራጮች ያልቀረቡበት የዘንድሮ ምርጫ!

“ምርጫዎች ቀን ቆጥረው ይመጣሉ፤ ውጤቱን እንዲለውጡ ግን አንፈልግም” ሶሻሊስቶች ለህዝብ ጥቅም በሚል ሰበብ በሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚሹት በዲሞክራሲያዊ መንገድ አይደለም፡፡ በዚህም ሳቢያ ፍትሃዊ ምርጫ ማድረግ አይዋጥላቸውም፡፡ ተፈጥሯዊ ባህርያቸውም አይደለም፡፡ የእነሱ ዝነኛ ብሂል “የትም ፍጪው [ስልጣኑን] አምጭው” የሚል ነው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአገራችን በሚካሄዱ ምርጫዎች፣ ምርጫ ቦርድና አስፈጻሚዎቹ ለምርጫ ሕጎችና አሰራሮች አልፎ ተርፎም ለመርሆዎች ተገዢ አለመሆናቸውና ለጉዳዩ ትኩረት መንፈጋቸው ሳያንስ፣ ገዢው ፓርቲ በገሃድ “ተቃዋሚዎች መጡም አልመጡም ግድ የለንም” እስከማለት መድረሱ ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት ፈታኝ ጥያቄ ነው፡፡ የምርጫ ቦርድና የአስፈጻሚዎቹ ትኩረት፣ አማራጭ ሃሳቦች አብብው ሕዝብ በአማራጭ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረው ማገዝ ሳይሆን እንደ ዓመታዊ በዓል ቀን ቆጥሮ ምርጫውን በማንኛውም ኪሳራ(At any cost) ውስጥ ማስፈፀም እየሆነ የመጣ ይመስላል ፡፡ ይህ አካሄድ የሚጠቁመን ነገር ቢኖር ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደደ የመጣው ሃቀኛ ዴሞክራሲ ሳይሆን የመንግስታዊ ከበርቴና የልማታዊ መንግስታት አስተሳሰብ መሰረት የሆነው የተምሳሌታዊ ዴሞክራሲ መሆኑን ነው፡፡ መጀመርያ ተቃዋሚዎችን ከነአቤቱታቸው በማስወገድ፣ ቀጥሎ በምርጫው አካሄድና ወግ አልባነት የተቆጣውን መራጭ ሕዝብ፣ ከቁጣው ለማብረድና እምነቱን በተጽእኖ ለማስለወጥ፣ ቤት ለቤት በሚያደርጉት መጠነ ሰፊ ፕሮፓጋንዳና ወከባ ማስጨነቃቸው፣ የፈለጉት የሕዝቡን “የይስሙላ ተሳትፎ” እንጂ ውጤት የማስለወጥ ሕጋዊ መብቱን እንዳልሆነ አይተናል፡፡ ልማታዊ መንግስታት፣ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የመሸነፍና የለውጥ ጥያቄ እንዲነሳባቸው አይፈቅዱም፡፡ ለዚህ ሲባልም የምርጫ ውድድር ቀንን ጠብቆ ምርጫ

የአካባቢ ምርጫ ትኩረት ነፋጊዎች

በኢትዮጵያ አምስት ዓይነት ምርጫዎች ይካሄዳሉ፡፡ እነዚህም ጠቅላላ ምርጫ፣ የአካባቢ ምርጫ፣ ማሟያ ምርጫ፣ ድጋሚ ምርጫና ሕዝብ ውሳኔ ይሰኛሉ፡፡ በያዝነው ወር ሚያዝያ 6 እና 13 ቀን 2005 ዓ.ም. የተካሄደው የአካባቢ ምርጫ ውጤት በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ እንደሚሆን የሚጠበቅ ቢሆንም፣ ከተወዳዳሪዎች አለመመጣጠን የተነሳ ብቻውን ተወዳድሯል የሚባለው ኢሕአዴግ ምርጫው ሳይደረግ ውጤቱን ያውቀዋል፡፡ የአካባቢ ምርጫ በቅድመ ምርጫው፣ በምርጫው ዕለትና በድኅረ ምርጫው ትኩረት እንዲነፈግ ያደረጉት ዓበይት ምክንያቶች ምንድን ናቸው? የአካባቢ ምርጫ በየደረጃው በሚገኙ የዞን፣ የወረዳ፣ የከተማ፣ የማዘጋጃ ቤት፣ የክፍለ ከተማ ወይም የቀበሌ ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ነው፡፡ በመላው አገሪቱ የተካሄደው ምርጫ ከኢሕአዴግ ውጪ የብዙ ዜጎችን ትኩረት እንዳላገኘ የተለያዩ መገናኛ ብዙኀን የዘገቡ ሲሆን፣ ከዚህ በተቃራኒ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ምርጫውን ‹‹ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ምሳሌ የሚሆን›› ሲሉ ነው የገለጹት፡፡ ለዚህ ድምዳሜ ፕሮፌሰሩን ያደረሳቸው ምክንያት ደግሞ ምርጫው ሰላማዊና የተሳካ መሆኑ፣ እንዲሁም የዜጎች ንቁ ተሳትፎ ከሁሉም አቅጣጫ የተረጋገጠበት መሆኑ ነው፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ የፖለቲካ ተንታኞችና የጥናት ውጤቶች ግን ከምርጫ ቦርድ ይፋዊ አቋም በተቃራኒ የአካባቢ ምርጫዎች ካላቸው መጠነ ሰፊ ጠቀሜታ አኳያ የተሻለ ትኩረት እንዲያገኙ አገሪቱ ቅድሚያ ሰጥታ ልትሠራበት እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡ የዕጩዎች ብዛት፣ የግንዛቤ ችግር፣ የፌዴራል መንግሥት ጫና፣ የፖለቲካ ባህልና የፖለቲካ ፓርቲዎች ደካማ ይዞታን በአንኳር ምክንያትነት የሚያነሱት አስተያየት ሰጪዎች እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ከሕግ

The enset (Ensete ventricosum) gardens of Sidama: composition, structure and dynamics of a traditional poly-variety system

Image
Bizuayehu Tesfaye Abstract The composition and structure of 300 enset gardens from 10 different locations in Sidama were examined. Average size of the gardens was 0.74 ha. The gardens are composed of mixtures of various named enset varieties and different groups recognisable on the basis of ‘sex’ (male and female) and use (cooking and processing). The gardens exhibit high diversity, with a given garden containing up to 24 varieties (mean = 8.2). However, the components are not represented equally. Typically, the gardens consisted of one or two very abundant varieties and a much larger number of less common ones. Enset gardens are dynamic because the number and composition of varieties and different types changed from garden to garden, from location to location and across time. Their composition, structure and dynamics have been influenced by human, socio-economic factors (farm size, land per capita, cropping patterns and size of livestock), temporal circumstances and landscape

በዎንሾ ወረዳ በህብረተሰብ ተሣትፎ የተለያዩ የትምህርት ልማት ስራዎች ተከናወኑ

Image
አዋሳ ሚያዚያ 29/2005 በሲዳማ ዞን የዎንሾ ወረዳ አንድ ሚሊዮን ብር በሚገመት የህብረተሰቡ ተሣትፎ የተለያዩ የትምህርት ልማት ስራዎች መከናወናቸውን የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ተሰማ ተፈራ ሰሞኑን እንደገለጹት በህብረተሰቡ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ከተሰሩት የትምህርት ልማት ስራዎች መካከል አራት አዳዲስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና 52 ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም 50 ነባር የመማሪያ ክፍሎች፣ ስምንት ቤተመጻህፍት፣ አምስት ቤተ ሙከራዎችና ከአንድ ሺህ በላይ ወንበሮች ዕድሳትና ጥገና ከመደረጉም በላይ የተለያዩ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሳደግና የማስፋፋት ስራዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል፡፡ ስድስቱን የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆችን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ከማድረግ አንፃርም የትምህርት ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የተማሪውን ውጤት ለማሻሻልም በየሳምነቱ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የታገዘ የማጠናከሪያ ትምህርት እንደሚሰጥ አመልክተው በአንድ ለአምስት ቁርኝትና በትምህርት ልማት ሰራዊት በማደራጀት በውጤት ደከም ያሉትን የመደገፍና ክትትል የማድረግ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል፡፡ ባለፈው የትምህርት ዘመን በ8ኛ፣ በ9ኛና በ10ኛ ክፍሎች በአማካኝ 65 በመቶ ማሳለፍ መቻላቸውን ጠቁመው ዘንድሮ 90 በመቶ ለማሳለፍ እቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በመምህራን በኩልም የሚስተዋሉ ክፍተቶችና የሚደግሙና የሚያቋርጡ ተማሪዎችን ቁጥር ለመቀነስ በየትምህርት ክፍሉ፣ በክበባትና በተማሪዎች ፓርላማ በመታገዝ ወቅታዊ ግምገማና ክትትል ስለሚደረግ ክፍተኛ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የጽህፈት ቤቱ ምክት