Posts

አርባምንጭ ከነማ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መብራት ኃይልና ሲዳማ ቡና አሸነፉ

ዛሬ ሚያዝያ 23/2005 ዓ.ም በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች አምስት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ አርባምንጭ ከነማ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መብራት ኃይል እና ሲዳማ ቡና ድል ሲቀናቸው ሙገር ሲሚንቶና መከላከያ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ስታድየም የተካሄደው የውኃ ስራ እና የአርባ ምንጭ ከነማ ጨዋታ በአርባምንጭ ከነማ 6 ለ 3 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የአርባምንጩ ገብረሚካዔል ያቆብ ሀትሪክ ሰርቷል፡፡ በጨዋታው አስደንጋጭ ጉዳት ያጋጠመው የአርባምንጩ እምሻው ካሱ ሆስፕታል ከተወሰደ በኋላ በደህና ጤንነት ላይ ቡድኑን መቀላቀል ችሏል፡፡ በአበበ ቢቂላ ስታድየም ሀረር ቢራን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና 5 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ሲዳማ ቡና አዳማ ከነማን አስተናግዶ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ረቷል፡፡ ወደ አሰላ ተጉዞ ሙገር ሲሚንቶን የገጠመው መከላከያ ያለምንም ጎል ተለያይቶ ነጥብ ሲጥል ሙገር ሲሚንቶ ከወራጅ ቀጠና የሚርቅበትን ነጥብ አጠናክሯል፡፡ በአዲስ አበባ ስታድየም በ11 ሰዓት በተደረገ ጨዋታ መብራት ኃይል ሀዋሳ ከነማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡  ሊጉን ደደቢት በ39 ነጥብ ሲመራ ኢትዮጵያ ቡና በ33፣ መብራት ኃይል እና ሀዋሳ ከነማ በ30፣ መከላከያ በ29፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በ25 ነጥቦች ይከተላል፡፡

የሲዳምኛን ቋንቋ ፣ ባህልና ታሪክ ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ፕሮግራሞች ተዘጋጁ

Image
አዋሳ ሚያዚያ 22/2005 የሲዳምኛን ቋንቋ፣ ባህልና ታሪክ ለማሳደግ ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ ፕሮግራሞች መዘጋጀታቸውን የዞኑ ባህል፣ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው ሀላፊ አቶ ወርቅነህ ፍላቴ ሰሞኑን እንደገለጹት ከፕሮግራሞቹ መካከል ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ከስምንት ወራት በፊት የተጀመረው የብሄረሰቡን ቋንቋ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ሶፍት ዌር የማዘጋጀት ስራ ይገኝበታል፡፡ ሲዳምኛ በዞኑ የስራና የትምህርት ቋንቋ እንደመሆኑ በዞኑ በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወጥና ደረጃውን የጠበቀ ቋንቋ መጠቀም ለዕደገቱ ከፍተኛ አሰተዋጾኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ ይህም እስከ ወረዳ በተዘረጋው የመንግስት መዋቅር ስር በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከአንድ ወር በኋላ በኮምፒተሮቻቸው የመጫን ስራ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡ ለሰፍት ዌሩ ስራ የወጣውን ጨረታ አሸንፎ ስራውን ያከናወነው ድርጅት በላቤት አቶ ታደለ አሰፋ በበኩላቸው የሶፍት ዌር ስራው 30 ከሚበልጡ የውጪ ሀገራት ቋንቋዎች ሶፍት ዌር በመቀመር መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ ከሀገር ውስጥ ሁኔታ ጋር ለማስተዋወቅና ለማጣጣም በሲዳምኛ ቋንቋ ከተዘጋጁ የተለያዩ የህትመት ውጤቶች ከ100 ሺህ በላይ ቃላት መሰባሰባቸውን አመልከተው ሙያዊ ቃላትን ጨምሮ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ቃላት በድግግሞሽ ሶፍት ዌር ውስጥ ሊገባ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ ይህንን ስራ ለመገምገምና ለእርምት ከተሳተፉት ባለሙያዎች አቶ አሰፋ ሙቁራ፣ አቶ ተፈራ ሌዳሞ እንዲሁም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሲዳምኛ ቋንቋ ዲፓርትመንት መምህር አቶ ማቴዎስ ወልደጊዮርጊስ በሰጡት አስተያየት ሶፍት ዌሩ ቋንቋው በማህበራዊ ፣ በኢኮኖሚና በፓለቲካ ጉዳዮች የተሟላ እንደሚያደርገው ጠቁመው ቋንቋ ለስነጹሁፍ እድገት ከ

በደቡብ ክልል የግብርና ግብይት ማሻሻያ ፕሮግራምን ለማጠናከር እየተሰራ ነው፡፡

Image
አዋሳ ሚያዚያ 21/2005 በደቡብ ክልል ከሰባት ሚሊዮን ዶላር በላይ በጀት የሚካሄደው አርሶ አደሩን ያሳተፈ የግብርና ግብይት ማሻሻያ ፕሮግራምን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ አስታወቀ፡፡ በክልሉ በተጀመረው በዚሁ ፕሮግራም አፈጻጸም ላይ የሚመክር ክልል አቀፍ ጉባኤ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተጀምሯል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ በጉባኤው ላይ እንደገለጹት ለሰባት አመታት የተነደፈው ይኸው ፕሮግራም አርሶ አደሮች በግብርና ግብይት ተጠቃሚ እንዲሆኑና ኑሮቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያደርግ የድህነት ቅነሳ ፕሮግራም አካል ነው፡፡ በኘሮግራሙ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከልም ተቋማዊ የአቅም ግንባታ፣ የገበያ መሰረተ ልማት ማስፋፋትና ለድህረ ምርት ቴክኖሎጂ ግዥ የሚሆን ብድር ለአርሶ አደሮች ማቅረብ እንደሚገኙበት ገልፀዋል፡፡ ፕሮግራሙ ከተጀመረበት ከ1998 ዓ.ም መጨረሻ አንስቶ እስካሁን በክልሉ 14 ዞኖች በተመረጡ 40 ወረዳዎች በተለያዩ ሰብሎች ጥራት፣ አመራረት፣ የድህረ ምርት አያያዝና ግብይት ላይ ከ3 ሺህ 500 በላይ ባለሙያዎችና የልማት ጣቢያ ሰራተኞች ሰልጥነዋል፡፡ በገበሬ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች አማካኝነትም ከ100 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች እንዲሰለጥኑ መደረጉም አመልክተዋል፡፡ እንዲሁም በገበያ መሰረተ ልማት ማስፋፋት በኩልም በሀዋሳ፣ በዲላ፣ በሶዶና በቦንጋ ከተሞች አራት የቡና ቅምሻና የጨረታ ማዕከላት ግንባታ ተካሄዷል ብለዋል፡፡ የድህረ ምርት ቴክኖሎጂ በተመለከተም 1ሺህ 512 የእሻት ቡና መፈልፈያና ማድረቂያ፣ የዝንጅብል ማጠቢያና ማድረቂያ፣ በሞተርና በእጅ የሚሰሩ የበቆሎ መፈልፈያ፣ በእንስሳት የሚጎተት ጋሪ ፣ የእንሰት መፋቂያን ጨምሮ ሌሎችን ቴክኖሎጂዎች አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን መሰራጨታቸውን ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ቴክኖሎጂዎች

በኢትዮጵያ የጤና ትብብር ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

Image
የአለም የጤና ድርጅት በኢትዮጵያ ለ4 አመታት የሚቆይ ሀገር አቀፍ የጤና ትብብር ስትራቴጂ ይፋ አደረገ፡፡ ስትራቴጁ  የጤና አገልግሎት ማሻሻል፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን፣ የእናቶችና ህፃናት ሞት መቀነስ፣ የስነተዋልዶ ጤናን ማሻሻል እንዲሁም የተደራጀ መረጃን ማሳደግ ትኩረት ያደርጋል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ እንዳሉት ትብብሩ ሀገሪቱ ከቀረፀችው የጤና ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣም በመሆኑ የምእተ አመቱን ግብ ለማሳካት ከፈተኛ ፋይዳ አለው፡፡ ይህም የጤና ልማት ሰራዊትን በማደራጀት በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል ያስችላል ብለዋል፡፡ በአለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ሊዊስ ሳምቦ በበኩላቸው በሀገሪቱ በጤናው ዘርፍ የሚከናወኑ ስራዎችን ከዳር ለማድረስ ድርጅቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ http://www.ertagov.com/amharic/index.php/component/k2/item/641-%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8B%A8%E1%8C%A4%E1%8A%93-%E1%89%B5%E1%89%A5%E1%89%A5%E1%88%AD-%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AB%E1%89%B4%E1%8C%82-%E1%8B%AD%E1%8D%8B-%E1%88%86%E1%8A%90

አርባምንጭ ከነማ በዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳው ሽንፈትን በሲዳማ ከነማ አስተናዷል።

Image
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ  የ17ኛው ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ሚያዝያ 19/2005 ሶስት ጨዋታ የተካሄዱ ሲሆን  ሐዋሳ ላይ ሐዋሳ ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግዶ አንድ አቻ ተለያይተዋል።   ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በ32 ነጥብ ደደቢት ተከትሎ ፕሪምየር ሊጉ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጧል። ሐዋሳ ከነማ በ30 ነጥብ  ሶሰተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። አርባምንጭ ከነማ በዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳው ሽንፈትን በሲዳማ ከነማ  አስተናዷል። በሲዳማ ቡና 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በመሸነፉ። አዳማ ከነማ አሁንም ከወራጅ ቀጠና መውጣት ሳይችል ቀርቷል በሜዳው በመብራት ኃይል 1 ለ 0 ተሸንፏል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ጨዋታ ደደቢት በ36 ነጥብ እየመራ ነው ። http://www.ertagov.com/amharic/index.php/2013-03-11-06-12-23/2013-03-11-07-10-49/item/633-%E1%88%83%E1%8B%8B%E1%88%B3-%E1%8A%A8%E1%8A%90%E1%88%9B-%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%89%A1%E1%8A%93%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8A%93%E1%8C%8D%E1%8B%B6-%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B5-%E1%8A%A0%E1%89%BB-%E1%89%B0%E1%88%88%E1%8B%AB%E1%8B%A8