Posts

በደቡብ ክልል የግብርና ግብይት ማሻሻያ ፕሮግራምን ለማጠናከር እየተሰራ ነው፡፡

Image
አዋሳ ሚያዚያ 21/2005 በደቡብ ክልል ከሰባት ሚሊዮን ዶላር በላይ በጀት የሚካሄደው አርሶ አደሩን ያሳተፈ የግብርና ግብይት ማሻሻያ ፕሮግራምን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ አስታወቀ፡፡ በክልሉ በተጀመረው በዚሁ ፕሮግራም አፈጻጸም ላይ የሚመክር ክልል አቀፍ ጉባኤ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተጀምሯል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ በጉባኤው ላይ እንደገለጹት ለሰባት አመታት የተነደፈው ይኸው ፕሮግራም አርሶ አደሮች በግብርና ግብይት ተጠቃሚ እንዲሆኑና ኑሮቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያደርግ የድህነት ቅነሳ ፕሮግራም አካል ነው፡፡ በኘሮግራሙ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከልም ተቋማዊ የአቅም ግንባታ፣ የገበያ መሰረተ ልማት ማስፋፋትና ለድህረ ምርት ቴክኖሎጂ ግዥ የሚሆን ብድር ለአርሶ አደሮች ማቅረብ እንደሚገኙበት ገልፀዋል፡፡ ፕሮግራሙ ከተጀመረበት ከ1998 ዓ.ም መጨረሻ አንስቶ እስካሁን በክልሉ 14 ዞኖች በተመረጡ 40 ወረዳዎች በተለያዩ ሰብሎች ጥራት፣ አመራረት፣ የድህረ ምርት አያያዝና ግብይት ላይ ከ3 ሺህ 500 በላይ ባለሙያዎችና የልማት ጣቢያ ሰራተኞች ሰልጥነዋል፡፡ በገበሬ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች አማካኝነትም ከ100 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች እንዲሰለጥኑ መደረጉም አመልክተዋል፡፡ እንዲሁም በገበያ መሰረተ ልማት ማስፋፋት በኩልም በሀዋሳ፣ በዲላ፣ በሶዶና በቦንጋ ከተሞች አራት የቡና ቅምሻና የጨረታ ማዕከላት ግንባታ ተካሄዷል ብለዋል፡፡ የድህረ ምርት ቴክኖሎጂ በተመለከተም 1ሺህ 512 የእሻት ቡና መፈልፈያና ማድረቂያ፣ የዝንጅብል ማጠቢያና ማድረቂያ፣ በሞተርና በእጅ የሚሰሩ የበቆሎ መፈልፈያ፣ በእንስሳት የሚጎተት ጋሪ ፣ የእንሰት መፋቂያን ጨምሮ ሌሎችን ቴክኖሎጂዎች አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን መሰራጨታቸውን ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ቴክኖሎጂዎች

በኢትዮጵያ የጤና ትብብር ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

Image
የአለም የጤና ድርጅት በኢትዮጵያ ለ4 አመታት የሚቆይ ሀገር አቀፍ የጤና ትብብር ስትራቴጂ ይፋ አደረገ፡፡ ስትራቴጁ  የጤና አገልግሎት ማሻሻል፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን፣ የእናቶችና ህፃናት ሞት መቀነስ፣ የስነተዋልዶ ጤናን ማሻሻል እንዲሁም የተደራጀ መረጃን ማሳደግ ትኩረት ያደርጋል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ እንዳሉት ትብብሩ ሀገሪቱ ከቀረፀችው የጤና ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣም በመሆኑ የምእተ አመቱን ግብ ለማሳካት ከፈተኛ ፋይዳ አለው፡፡ ይህም የጤና ልማት ሰራዊትን በማደራጀት በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል ያስችላል ብለዋል፡፡ በአለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ሊዊስ ሳምቦ በበኩላቸው በሀገሪቱ በጤናው ዘርፍ የሚከናወኑ ስራዎችን ከዳር ለማድረስ ድርጅቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ http://www.ertagov.com/amharic/index.php/component/k2/item/641-%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8B%A8%E1%8C%A4%E1%8A%93-%E1%89%B5%E1%89%A5%E1%89%A5%E1%88%AD-%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AB%E1%89%B4%E1%8C%82-%E1%8B%AD%E1%8D%8B-%E1%88%86%E1%8A%90

አርባምንጭ ከነማ በዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳው ሽንፈትን በሲዳማ ከነማ አስተናዷል።

Image
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ  የ17ኛው ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ሚያዝያ 19/2005 ሶስት ጨዋታ የተካሄዱ ሲሆን  ሐዋሳ ላይ ሐዋሳ ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግዶ አንድ አቻ ተለያይተዋል።   ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በ32 ነጥብ ደደቢት ተከትሎ ፕሪምየር ሊጉ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጧል። ሐዋሳ ከነማ በ30 ነጥብ  ሶሰተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። አርባምንጭ ከነማ በዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳው ሽንፈትን በሲዳማ ከነማ  አስተናዷል። በሲዳማ ቡና 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በመሸነፉ። አዳማ ከነማ አሁንም ከወራጅ ቀጠና መውጣት ሳይችል ቀርቷል በሜዳው በመብራት ኃይል 1 ለ 0 ተሸንፏል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ጨዋታ ደደቢት በ36 ነጥብ እየመራ ነው ። http://www.ertagov.com/amharic/index.php/2013-03-11-06-12-23/2013-03-11-07-10-49/item/633-%E1%88%83%E1%8B%8B%E1%88%B3-%E1%8A%A8%E1%8A%90%E1%88%9B-%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%89%A1%E1%8A%93%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8A%93%E1%8C%8D%E1%8B%B6-%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B5-%E1%8A%A0%E1%89%BB-%E1%89%B0%E1%88%88%E1%8B%AB%E1%8B%A8

ኢኮኖሚውና ቢዝነሱ ፈዟል! እናነቃቃው እንጂ!

Image
ኢኮኖሚው ወድቋል፣ ሞቷል አይደለም እያልን ያለነው፡፡ ፈዟል ነው፡፡ በእውነት  ፈዟል፡፡ ከፍተኛ በጀት የሚጠይቁ፣ ተግባር ላይ ሲውሉና ሲሳኩም አገርን በእጅጉ የሚጠቅሙ፣ በሐሳብና በፍላጎት ብቻ ሳይሆን በተግባር ሥራቸው የተጀመረ ፕሮጀክቶች አሉ፡፡ ነገር ግን በሚያስተማምን ሁኔታ በቂ በጀት እያገኙ ያሉ ፕሮጀክቶች አይደሉም፡፡ ከውጭ ብድርና ዕርዳታ ከተገኘ ጥሩ፣ ካልተገኘ ደግሞ ራሳችን እንፈጽማቸዋለን ብለን የጀመርናቸው ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡ በራስ ተማምኖ መጓዝን የመሰለ የለም፡፡ እዚህ ላይ ስህተት የለም፡፡ ነገር ግን በራስ መተማመን በራስ ገንዘብን እውን ከማድረግ ጋር መያያዝ አለበት፡፡ ምርት እያደገ፣ ኤክስፖርት እያደገ፣ ግብር እያደገ፣ ወዘተ ሲሄድ ነው የውስጥ አቅም ሊጨምር የሚችለው፡፡ በዚህ ዙሪያ ዕድገትና የአቅም መጎልበት ካልታየ ሊገኝ የታሰበው በጀት ላይገኝ ስለሚችል በዕቅዶች ላይ መጓተት ያስከትላል፡፡ የስኳር ፕሮጀክቶች በቂ በጀት እያገኙ አይደሉም፡፡ የምድር ባቡር ሥራው በበጀት በአስተማማኝ ደረጃ ላይ አይደለም፡፡ መንግሥት ከግል የኮንስትራክሽን ድርጅቶችና ከሌሎች ዓበይት ሥራዎችን ከሚሠሩ የግል ድርጅቶች ጋር ተዋውሎ ላሠራው ሥራ ለመክፈልም ሲቸገር እየታየ ነው፡፡ ሥራው ተሠርቷል ክፍያ ግን አልተፈጸመም፡፡  ሁሉም ችግር በገንዘብ  ባይመካኝም የገንዘብ እጥረት አንዱና ዋነኛው ምክንያት ነው፡፡ ባንኮች ለደንበኞቻቸው በተገቢው ደረጃ ብድር እየሰጡ አይደሉም፡፡ ያላግባብ የሚሰጥ ብድርን ማረምና ማስተካከል ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን እየታየ ያለው ችግር ጉድለትን የማስተካከል ሳይሆን ለተገቢው ብድር ብቁና ንቁ ሆኖ አለመገኘት ነው፡፡ የውጭ ምንዛሪ ጉዳይም እንደዚሁ አስተማማኝ አይደለም፤ እጥረት አለበት፡፡ ሙስናም አለበት፡፡ የአቅም ማነስም አለበት፡

ሁለተኛዉን የሙዚቃ ቀን በዓል በሀዋሳ ከተማ ለማክበር ዝግጅት አየተደረገ ነው፡፡

Image
ሀዋሳ ሚያዚያ 19/2005 የብሄር ብሄረሰቦችን ባህልና የቱሪስት መስህቦችን የማስተዋወቅ አላማ ያደረገዉ ሁለተኛዉ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቀን በዓል በተለያዩ ፕሮግራሞች በሀዋሳ ከተማ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የከተማው አስተዳደርና አርቲስቶች ገለጹ፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ይህንኑ በዓል አስመልከቶ የከተማው አስተዳደር የስራ ሃላፊዎችና ታዋቂ አርቲስቶች ትናንት በሀዋሳ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል ። ከግንቦት 9 እስክ 11/2005 በሚካሄደዉ የሙዚቃ ቀን በዓል ላይ የኪነጥበብና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ሰዎች ይሳተፋሉ፡፡ የከተማው አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባና የባህል ፣ቱሪዝምና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ምህረት ገነነ እንዳስታወቁት ሀዋሳ የበርካታ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ማዕከል እንደመሆኗ ባህላቸውን፣ እሴታቸውንና ለማስተዋወቅና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በአሉ ከፍተኛ ፋይዳ ያለዉ ነዉ ። ፕሮግራሙ ከማዝናናት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፋይዳው ክፍተኛ በመሆኑ በተለይ የክልሉና የሀዋሳን ሁለንታናዊ ገጽታንና የእድገት እንቅስቃሴ ለሌላው በማሳየትና ልምድ ለመለዋወጥ እንደሚያግዝ በመታመኑ ፕሮግራሙን ለማሳካት አስፈላጊዉ ዝግጅት ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታዉቀዋል ። ታዋቂ የሀገራቸን አርቲስቶች ባለፈው አመት አዲስ አበባ ላይ ያከበሩት የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቀን ለሁለተኛ ጊዜ በሀዋሳ ለማክበር ፕሮግራም ይዘው ሲመጡ በደስታ ተቀብለው ለማስተናገድ ባለሀብቶችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካለትን ያሳተፉ አብይ፣ ንዑሳንና ኮሚቴዎችን አቋቁመው እየተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከሀገራችን ታዋቂ አርቲስቶች መካከል አቶ ተስፋ አለም ታምራትና አቶ ይገረም ደጀኔ በበኩላቸው " ዝክረ ሀዋሳ ሀገር አቀፍ