በደቡብ ክልል የግብርና ግብይት ማሻሻያ ፕሮግራምን ለማጠናከር እየተሰራ ነው፡፡
አዋሳ ሚያዚያ 21/2005 በደቡብ ክልል ከሰባት ሚሊዮን ዶላር በላይ በጀት የሚካሄደው አርሶ አደሩን ያሳተፈ የግብርና ግብይት ማሻሻያ ፕሮግራምን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ አስታወቀ፡፡ በክልሉ በተጀመረው በዚሁ ፕሮግራም አፈጻጸም ላይ የሚመክር ክልል አቀፍ ጉባኤ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተጀምሯል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ በጉባኤው ላይ እንደገለጹት ለሰባት አመታት የተነደፈው ይኸው ፕሮግራም አርሶ አደሮች በግብርና ግብይት ተጠቃሚ እንዲሆኑና ኑሮቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያደርግ የድህነት ቅነሳ ፕሮግራም አካል ነው፡፡ በኘሮግራሙ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከልም ተቋማዊ የአቅም ግንባታ፣ የገበያ መሰረተ ልማት ማስፋፋትና ለድህረ ምርት ቴክኖሎጂ ግዥ የሚሆን ብድር ለአርሶ አደሮች ማቅረብ እንደሚገኙበት ገልፀዋል፡፡ ፕሮግራሙ ከተጀመረበት ከ1998 ዓ.ም መጨረሻ አንስቶ እስካሁን በክልሉ 14 ዞኖች በተመረጡ 40 ወረዳዎች በተለያዩ ሰብሎች ጥራት፣ አመራረት፣ የድህረ ምርት አያያዝና ግብይት ላይ ከ3 ሺህ 500 በላይ ባለሙያዎችና የልማት ጣቢያ ሰራተኞች ሰልጥነዋል፡፡ በገበሬ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች አማካኝነትም ከ100 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች እንዲሰለጥኑ መደረጉም አመልክተዋል፡፡ እንዲሁም በገበያ መሰረተ ልማት ማስፋፋት በኩልም በሀዋሳ፣ በዲላ፣ በሶዶና በቦንጋ ከተሞች አራት የቡና ቅምሻና የጨረታ ማዕከላት ግንባታ ተካሄዷል ብለዋል፡፡ የድህረ ምርት ቴክኖሎጂ በተመለከተም 1ሺህ 512 የእሻት ቡና መፈልፈያና ማድረቂያ፣ የዝንጅብል ማጠቢያና ማድረቂያ፣ በሞተርና በእጅ የሚሰሩ የበቆሎ መፈልፈያ፣ በእንስሳት የሚጎተት ጋሪ ፣ የእንሰት መፋቂያን ጨምሮ ሌሎችን ቴክኖሎጂዎች አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን መሰራጨታቸውን ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ቴክኖሎጂዎች