Posts

አርባምንጭ ከነማ በዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳው ሽንፈትን በሲዳማ ከነማ አስተናዷል።

Image
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ  የ17ኛው ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ሚያዝያ 19/2005 ሶስት ጨዋታ የተካሄዱ ሲሆን  ሐዋሳ ላይ ሐዋሳ ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግዶ አንድ አቻ ተለያይተዋል።   ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በ32 ነጥብ ደደቢት ተከትሎ ፕሪምየር ሊጉ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጧል። ሐዋሳ ከነማ በ30 ነጥብ  ሶሰተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። አርባምንጭ ከነማ በዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሜዳው ሽንፈትን በሲዳማ ከነማ  አስተናዷል። በሲዳማ ቡና 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በመሸነፉ። አዳማ ከነማ አሁንም ከወራጅ ቀጠና መውጣት ሳይችል ቀርቷል በሜዳው በመብራት ኃይል 1 ለ 0 ተሸንፏል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ጨዋታ ደደቢት በ36 ነጥብ እየመራ ነው ። http://www.ertagov.com/amharic/index.php/2013-03-11-06-12-23/2013-03-11-07-10-49/item/633-%E1%88%83%E1%8B%8B%E1%88%B3-%E1%8A%A8%E1%8A%90%E1%88%9B-%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%89%A1%E1%8A%93%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8A%93%E1%8C%8D%E1%8B%B6-%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B5-%E1%8A%A0%E1%89%BB-%E1%89%B0%E1%88%88%E1%8B%AB%E1%8B%A8

ኢኮኖሚውና ቢዝነሱ ፈዟል! እናነቃቃው እንጂ!

Image
ኢኮኖሚው ወድቋል፣ ሞቷል አይደለም እያልን ያለነው፡፡ ፈዟል ነው፡፡ በእውነት  ፈዟል፡፡ ከፍተኛ በጀት የሚጠይቁ፣ ተግባር ላይ ሲውሉና ሲሳኩም አገርን በእጅጉ የሚጠቅሙ፣ በሐሳብና በፍላጎት ብቻ ሳይሆን በተግባር ሥራቸው የተጀመረ ፕሮጀክቶች አሉ፡፡ ነገር ግን በሚያስተማምን ሁኔታ በቂ በጀት እያገኙ ያሉ ፕሮጀክቶች አይደሉም፡፡ ከውጭ ብድርና ዕርዳታ ከተገኘ ጥሩ፣ ካልተገኘ ደግሞ ራሳችን እንፈጽማቸዋለን ብለን የጀመርናቸው ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡ በራስ ተማምኖ መጓዝን የመሰለ የለም፡፡ እዚህ ላይ ስህተት የለም፡፡ ነገር ግን በራስ መተማመን በራስ ገንዘብን እውን ከማድረግ ጋር መያያዝ አለበት፡፡ ምርት እያደገ፣ ኤክስፖርት እያደገ፣ ግብር እያደገ፣ ወዘተ ሲሄድ ነው የውስጥ አቅም ሊጨምር የሚችለው፡፡ በዚህ ዙሪያ ዕድገትና የአቅም መጎልበት ካልታየ ሊገኝ የታሰበው በጀት ላይገኝ ስለሚችል በዕቅዶች ላይ መጓተት ያስከትላል፡፡ የስኳር ፕሮጀክቶች በቂ በጀት እያገኙ አይደሉም፡፡ የምድር ባቡር ሥራው በበጀት በአስተማማኝ ደረጃ ላይ አይደለም፡፡ መንግሥት ከግል የኮንስትራክሽን ድርጅቶችና ከሌሎች ዓበይት ሥራዎችን ከሚሠሩ የግል ድርጅቶች ጋር ተዋውሎ ላሠራው ሥራ ለመክፈልም ሲቸገር እየታየ ነው፡፡ ሥራው ተሠርቷል ክፍያ ግን አልተፈጸመም፡፡  ሁሉም ችግር በገንዘብ  ባይመካኝም የገንዘብ እጥረት አንዱና ዋነኛው ምክንያት ነው፡፡ ባንኮች ለደንበኞቻቸው በተገቢው ደረጃ ብድር እየሰጡ አይደሉም፡፡ ያላግባብ የሚሰጥ ብድርን ማረምና ማስተካከል ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን እየታየ ያለው ችግር ጉድለትን የማስተካከል ሳይሆን ለተገቢው ብድር ብቁና ንቁ ሆኖ አለመገኘት ነው፡፡ የውጭ ምንዛሪ ጉዳይም እንደዚሁ አስተማማኝ አይደለም፤ እጥረት አለበት፡፡ ሙስናም አለበት፡፡ የአቅም ማነስም አለበት፡

ሁለተኛዉን የሙዚቃ ቀን በዓል በሀዋሳ ከተማ ለማክበር ዝግጅት አየተደረገ ነው፡፡

Image
ሀዋሳ ሚያዚያ 19/2005 የብሄር ብሄረሰቦችን ባህልና የቱሪስት መስህቦችን የማስተዋወቅ አላማ ያደረገዉ ሁለተኛዉ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቀን በዓል በተለያዩ ፕሮግራሞች በሀዋሳ ከተማ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የከተማው አስተዳደርና አርቲስቶች ገለጹ፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ይህንኑ በዓል አስመልከቶ የከተማው አስተዳደር የስራ ሃላፊዎችና ታዋቂ አርቲስቶች ትናንት በሀዋሳ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል ። ከግንቦት 9 እስክ 11/2005 በሚካሄደዉ የሙዚቃ ቀን በዓል ላይ የኪነጥበብና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ሰዎች ይሳተፋሉ፡፡ የከተማው አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባና የባህል ፣ቱሪዝምና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ምህረት ገነነ እንዳስታወቁት ሀዋሳ የበርካታ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ማዕከል እንደመሆኗ ባህላቸውን፣ እሴታቸውንና ለማስተዋወቅና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በአሉ ከፍተኛ ፋይዳ ያለዉ ነዉ ። ፕሮግራሙ ከማዝናናት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፋይዳው ክፍተኛ በመሆኑ በተለይ የክልሉና የሀዋሳን ሁለንታናዊ ገጽታንና የእድገት እንቅስቃሴ ለሌላው በማሳየትና ልምድ ለመለዋወጥ እንደሚያግዝ በመታመኑ ፕሮግራሙን ለማሳካት አስፈላጊዉ ዝግጅት ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታዉቀዋል ። ታዋቂ የሀገራቸን አርቲስቶች ባለፈው አመት አዲስ አበባ ላይ ያከበሩት የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቀን ለሁለተኛ ጊዜ በሀዋሳ ለማክበር ፕሮግራም ይዘው ሲመጡ በደስታ ተቀብለው ለማስተናገድ ባለሀብቶችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካለትን ያሳተፉ አብይ፣ ንዑሳንና ኮሚቴዎችን አቋቁመው እየተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከሀገራችን ታዋቂ አርቲስቶች መካከል አቶ ተስፋ አለም ታምራትና አቶ ይገረም ደጀኔ በበኩላቸው " ዝክረ ሀዋሳ ሀገር አቀፍ

Hardywood Bourbon Sidamo

Image
Beer style:  Imperial Coffee Stout aged in Bourbon Barrels An assertive Imperial Stout aged 12 weeks in bourbon barrels and conditioned on custom roasted Sidamo coffee from Lamplighter Roasting Company, Bourbon Sidamo showcases the signature flavors of whiskey, roasted malt and Ethiopian coffee. This robust stout displays a midnight hue with a caramel head and offers a dark chocolate character laced with hints of blueberry from this unique coffee bean, rounded out by charred White Oak infused by an angel’s share of Kentucky goodness. Best with:  Pairs beautifully with rich, soft cheeses, gamey meats in savory sauce, cream-based and dark fruit desserts. Original Gravity (O.G.):  1.092 Strength (ABV):  10.3 % ABV Color (SRM):  45 °L Bitterness (IBU):  55 IBUs Next release date:  Sat, 03/02/2013 - 2:00pm Package:  Draft 1/6 bbl (5.1 gal) keg Bottles 12 x 750 ml bottles Category:  Barrel Series beer

አዲሱ የኢትዮጵያ የቋንቋ ፖሊሲ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀርብ ነው

Image
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 13 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተዘጋጀው የቋንቋ ፖሊሲ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀርብ ነው። ረቂቅ ፖሊሲው ላለፉት ሁለት ዓመታት ሀገራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ ጋር በመተባበር በባለድርሻ አካላት ሲገመገም ነው የቆየው። ትላንትና ከትናንት ወዲያ  በተካሄደው የመጨረሻ ግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ፥ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ሌሎችም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት የተውጣጡ 230 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። በሚኒስቴሩ የቋንቋና የባህል ልማት ዳይሬክተር አቶ አውላቸው ሹምነካ እንዳሉት ፖሊሲው የግልና የጋራ የቋንቋ መብቶችን የያዘ ነው። ከፊደል ቀረጻ ጀምሮ እስከ ትግበራ ያለው ሂደት በስርዓት እንዲመራ ፖሊሲው አጋዥ ይሆናል ሲሉ አቶ አውላቸው ለሪፖርተራችን ራሔል አበበ ነግረዋታል። በመድረኩ የቋንቋና የህግ ማዕቀፍ፣ ቋንቋና አፍ መፍቻ ፣ ቋንቋና ከፍተኛ ትምህርት የሚሉና ሌሎችም 10 ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን ፥ በቋንቋ ዙሪያ የህንድና የደቡብ አፍሪካ ተሞክሮ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የቋንቋ መብቶች በተገቢው መንገድ ተግባራዊ እንዲሆኑና እንዲደረጉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል የተባለው ፖሊሲ ግብአት ከተሰበሰበት በኋላ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።