Posts

ሁለተኛዉን የሙዚቃ ቀን በዓል በሀዋሳ ከተማ ለማክበር ዝግጅት አየተደረገ ነው፡፡

Image
ሀዋሳ ሚያዚያ 19/2005 የብሄር ብሄረሰቦችን ባህልና የቱሪስት መስህቦችን የማስተዋወቅ አላማ ያደረገዉ ሁለተኛዉ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቀን በዓል በተለያዩ ፕሮግራሞች በሀዋሳ ከተማ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የከተማው አስተዳደርና አርቲስቶች ገለጹ፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ይህንኑ በዓል አስመልከቶ የከተማው አስተዳደር የስራ ሃላፊዎችና ታዋቂ አርቲስቶች ትናንት በሀዋሳ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል ። ከግንቦት 9 እስክ 11/2005 በሚካሄደዉ የሙዚቃ ቀን በዓል ላይ የኪነጥበብና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ሰዎች ይሳተፋሉ፡፡ የከተማው አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባና የባህል ፣ቱሪዝምና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ምህረት ገነነ እንዳስታወቁት ሀዋሳ የበርካታ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ማዕከል እንደመሆኗ ባህላቸውን፣ እሴታቸውንና ለማስተዋወቅና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በአሉ ከፍተኛ ፋይዳ ያለዉ ነዉ ። ፕሮግራሙ ከማዝናናት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፋይዳው ክፍተኛ በመሆኑ በተለይ የክልሉና የሀዋሳን ሁለንታናዊ ገጽታንና የእድገት እንቅስቃሴ ለሌላው በማሳየትና ልምድ ለመለዋወጥ እንደሚያግዝ በመታመኑ ፕሮግራሙን ለማሳካት አስፈላጊዉ ዝግጅት ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታዉቀዋል ። ታዋቂ የሀገራቸን አርቲስቶች ባለፈው አመት አዲስ አበባ ላይ ያከበሩት የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቀን ለሁለተኛ ጊዜ በሀዋሳ ለማክበር ፕሮግራም ይዘው ሲመጡ በደስታ ተቀብለው ለማስተናገድ ባለሀብቶችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካለትን ያሳተፉ አብይ፣ ንዑሳንና ኮሚቴዎችን አቋቁመው እየተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከሀገራችን ታዋቂ አርቲስቶች መካከል አቶ ተስፋ አለም ታምራትና አቶ ይገረም ደጀኔ በበኩላቸው " ዝክረ ሀዋሳ ሀገር አቀፍ

Hardywood Bourbon Sidamo

Image
Beer style:  Imperial Coffee Stout aged in Bourbon Barrels An assertive Imperial Stout aged 12 weeks in bourbon barrels and conditioned on custom roasted Sidamo coffee from Lamplighter Roasting Company, Bourbon Sidamo showcases the signature flavors of whiskey, roasted malt and Ethiopian coffee. This robust stout displays a midnight hue with a caramel head and offers a dark chocolate character laced with hints of blueberry from this unique coffee bean, rounded out by charred White Oak infused by an angel’s share of Kentucky goodness. Best with:  Pairs beautifully with rich, soft cheeses, gamey meats in savory sauce, cream-based and dark fruit desserts. Original Gravity (O.G.):  1.092 Strength (ABV):  10.3 % ABV Color (SRM):  45 °L Bitterness (IBU):  55 IBUs Next release date:  Sat, 03/02/2013 - 2:00pm Package:  Draft 1/6 bbl (5.1 gal) keg Bottles 12 x 750 ml bottles Category:  Barrel Series beer

አዲሱ የኢትዮጵያ የቋንቋ ፖሊሲ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀርብ ነው

Image
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 13 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተዘጋጀው የቋንቋ ፖሊሲ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀርብ ነው። ረቂቅ ፖሊሲው ላለፉት ሁለት ዓመታት ሀገራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ ጋር በመተባበር በባለድርሻ አካላት ሲገመገም ነው የቆየው። ትላንትና ከትናንት ወዲያ  በተካሄደው የመጨረሻ ግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ፥ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ሌሎችም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት የተውጣጡ 230 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። በሚኒስቴሩ የቋንቋና የባህል ልማት ዳይሬክተር አቶ አውላቸው ሹምነካ እንዳሉት ፖሊሲው የግልና የጋራ የቋንቋ መብቶችን የያዘ ነው። ከፊደል ቀረጻ ጀምሮ እስከ ትግበራ ያለው ሂደት በስርዓት እንዲመራ ፖሊሲው አጋዥ ይሆናል ሲሉ አቶ አውላቸው ለሪፖርተራችን ራሔል አበበ ነግረዋታል። በመድረኩ የቋንቋና የህግ ማዕቀፍ፣ ቋንቋና አፍ መፍቻ ፣ ቋንቋና ከፍተኛ ትምህርት የሚሉና ሌሎችም 10 ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን ፥ በቋንቋ ዙሪያ የህንድና የደቡብ አፍሪካ ተሞክሮ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የቋንቋ መብቶች በተገቢው መንገድ ተግባራዊ እንዲሆኑና እንዲደረጉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል የተባለው ፖሊሲ ግብአት ከተሰበሰበት በኋላ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።

በለኩ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ የሚሸጥ መድሃኒት እየተበራከተ ነው.......ነዋሪዎች

Image
አዋሳ ሚያዚያ 15/2005 በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ በሌኩ ከተማ በሀገ ወጥ መንገድ በከተማው የሚሸጡ መድሃኒቶች መበራከት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ በከተማው በገበያ ፣በመንገድ ዳርና ሱቆች በህገ ወጥ መንገድ የሚሸጡ መድሃኒቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መቷል፡፡ ይህም ለነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሪፖርተር አስተያየታቸውን የሰጡ አንዳንድ የከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ከነዋሪዎቹ መካከል ወይዜሮ ጥሩወርቅ ወልዴ፣ ወይዜሮ አበባው በቀለና ወይዘሮ ምትኬ ጫኒያለው እንዳሉት በተለይ ረቡዕና ቅዳሜ መድሃኒቱ ገበያ ላይ እንደማንኛውም ሸቀጥ ቀርቦ እየተሸጠ ይገኛል፡፡ መድሃኒቱ የሚሸጠው ምንም ስለመድሃኒቱ ዕውቀት በሌላቸው ግለሰቦች መሆኑ ጉዳዩን እጅግ አሳሳቢ እድሮጎታል፡፡ በተለይ የሰው መድሃኒት ከከብቶች፣ ከበግና ከፍየል በድሃኒቶች ጋር አንድ ላይ ተቀላቅሎ መሸጡ የነገሩን አሳሳቢነት በህብረተሰቡ ዘንድ እንዲጨምር ማድረጉን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ቡርሶ ቡላሾ ነዋሪዎች ያነሱት ቅሬታ ትክክል መሆኑን በማመን ችግሩን ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ ከወረዳ አስተዳደር፣ ከፖሊስና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ ህገ ወጥ መድሃኒቶቹ ጎረቤት ወረዳዎችና ዞኖች በማቋረጥ ወደ ከተማ የሚገቡ ስለሆነ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ከአጎራባች ወረዳዎችና ዞኖች ጋር በመሆን እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎችን ከዳር ለማድረስ የህብረተሰቡ የተቀናጀ ትብብርና እገዛ ወሳኝ በመሆኑ በህገ ወጥ መንገድ በመድሃኒት ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦችን በማጋለጥ ህብረተሰቡ እንዲተባበር ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ h

የኢትዮጵያ ምርጫ፤ ሰብአዊ መብትና ዉዝግብ

Image
ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ብራስልስ ላይ እንዳሉት መንግሥታቸዉ ከዓለም አቀፉ ድርጅት ሸላሚዎች ጋር አይግባባም፥ እንዲያዉም ይቃረናል።ከዋሽግተን ዲሲ የደረሰንን ዘገባ ከተከታተላችሁት፥ የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አርብ ማታ ይፋ ያደረገዉ ዓመታዊ ዘገባ ከጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም መግለጫ ጋር መቃረኑን አስተዉላችኋል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ኀላፊ፥--- ከተቃዋሚ ፓርቲ ባለሥልጣናት አንዱ፥ --- የፖለቲካ ተንታኝ፥ ---- ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማይርያም ደሳለኝ፥--- የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሹም፥--- አይግባቡም።አይደማመጡም፥ ይቃረናሉም።እንዴት? ለምን? ላፍታ አብረን እንጠይቅ ------ የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች እንደዘገቡት፥ኢትዮጵያዉያን ሥደተኞች ለበርካታ አመታት እንደሚያደርጉ፥ እንደኖሩበት፥ከኖርዌ እስከ ዋሽግተን፥ ከአዳራሽ እስከ አደባባይ እንደተሰለፉ ያለፈዉ ሳምንት-ይሕን ሳምንት ተካ።ጥያቄዉ አንድም ብዙም ነዉ።መፈክሩ ግን ይቀነቀናል።ጥያቄዉ ይዥጎደጎዳል።ቅዳሜ፥-ስታቫንገር-ኖርዌ ተደገመ። ቅዳሜ፥ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ምናልባት አዲስ አበባ ይሆኑ ይሆናል።ከአራት ቀን በፊት ሮብ ግን ሽትራስቡርግ-ፈረንሳይ ነበሩ።ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳት ከማርቲን ሹልስ ጋር ባደረጉት ዉይይት ከተነሱ ጉዳዮች የኢትዮጵያ መንግሥት የሠብአዊ መብት፥ የፕሬስ ነፃነት፥ የፍትሕ አያያዝ ዋናዎቹ ነበሩ። ድምፅ ሲሰጥ ርዕሠ-መንበሩን ፓሪስ ፈረንሳይ ያደረገዉ የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፥ የሳይንስ እና የባሕል ድርጅት (UNESCO) የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ወንጀል በይግባኝ አምስት ዓመት እስራት ያስፈረደባትን አምደኛ፥ ፀሐፊ