ፌዴሬሽኑ ከደቡብ እግር ኳስ አመራር ጋር የደረሰበት ስምምነት አለመግባባት ፈጠረ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ግጭት ውስጥ ገብቶ ከቆየ በኋላ፣ ባለፈው ሚያዝያ 1 ቀን 2005 ዓ.ም. ሁለቱ ፌዴሬሽኖች ባካሄዱት የጋራ ስብሰባ ከስምምነት ቢደርሱም፣ ስምምነቱ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ውስጥ አለመግባባት መፍጠሩ ተሰማ፡፡ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ በፌዴሬሽኑ ልዩ ልዩ ክፍሎች ወሳኝ ድርሻ ያላቸው ሙያተኞችና ሠራተኞች ባለፈው ረቡዕ ባደረጉት ስብሰባ፣ በፌዴሬሽኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደተነጋገሩ፣ የፌዴሬሽን ምንጮች በተለይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ እንደምንጮቹ፣ በዕለቱ በተካሄደው ስብሰባ በፌዴሬሽኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በርካታ ነጥቦች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ በአንዳንዶቹ ነጥቦች ላይ የጋራ መግባባት ሲፈጠር፣ በአንዳንዶቹ ግን በተለይም ሥራ አስፈጻሚዎቹን ለሁለት በመክፈል ክፉና ደግ አነጋግሯል፡፡ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መካከል አለመግባባት ከፈጠሩት ነጥቦች፣ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና በደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ፣ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ሳህሉ ገብረወልድ ያለ ሥራ አስፈጻሚው ይሁንታ ወደ ሐዋሳ በማምራት ከደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ልዩነቱን ለማጥበብ የደረሱበት ስምምነት እንደሆነ ምንጮቹ ያስረዳሉ፡፡ በብሔራዊ ፌዴሬሽኑና በደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መካከል ተደረሰበት የተባለው ስምምነት ‹‹የደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መጋቢት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. በሐዋሳ ጠርቶት የነበረው ስብሰባ ከመነሻው ሁለት ተልዕኮዎች እንደነበሩት፣ አንዱና የመጀመርያው በክልሉ ያለውን የስፖርት ልማት እንቅስቃሴ ለተጋባዥ የክልል ፌዴሬሽኖችና ከተማ አስተዳደሮች በማስጐብኘት ልምድ ልውውጥ ማድረግ፣ በሌ