Posts

Metropolis coffee: Guji Shakiso, Sidamo, Ethiopia

Image
We just featured an Ethiopian coffee from Kuma. For all of you who’ve been enjoying it, we’ve got another Ethiopian for you to try. We’re really pumped to have  Metropolis  back in the house. This time they sent us a Sidamo from the Guji region. Kelly from Metropolis told me that they have a nickname for it, “The Guj” (long u: gūj). I thought that was neat. I’ve been working on new training materials about coffee. So I’ve been refreshing myself about the different regions we experience with our coffee program. Ethiopia is the number one producer of coffee in Africa, the 6th globally. There are 15 million workers in the coffee production industry there. The coffees are picked in the Fall. Many Ethiopian coffees are made using the fully-washed process. The workers start out by removing the skin and pulp from the bean while the coffee fruit is still moist. The coffee skins are removed, then allowed to ferment, where enzymes loosen the sticky fruit pulp. This is where a lot of the sw

ሲዳማ ዞን ውስጥ መዋለ ንዋይ የሚያፈሱ ባላሃብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሽቆልቆል ላይ ነው፤ ባለፈው በጀት ኣመት በዞኑ ከ 267 ሚሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘጋቡ ባላሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ ሲሆን በዚህ ኣመት ግን 15 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ካፒታል ያስመዘጋቡ ባላሃብቶች ብቻ ናቸው ፍቃድ የወስዱት

አዋሳ ሚያዚያ 09/2005 በሲዳማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 15 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ወልደሚካኤል ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ፈቃዱ የተሰጠው በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራት ጥያቄ ላቀረቡ አምስት ባለሃብቶች ነው፡፡ ባለሃብቶቹ ከተሰማሩባቸው የስራ መስኮች መካከል አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ ግብርናና ኢንዱስትሪ እንደሚገኙበት አስታውቀዋል፡፡ ባለሃብቶቹ በሚያካሂዱዋቸው ኘሮጀክቶች ለ100 ቋሚና 994 ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠራቸውን ገልጸዋል፡፡ መምሪያው በገጠር የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማጥናትና በመለየት ለባለሃብቶች ከማስተዋወቅ በተጨማሪ በግብርና፣ በማህበራዊ አገልግሎትና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሀብተቶች ከ620 ሄክታር በላይ የገጠር መሬት መስጠቱን የስራ ሂደቱ አስተባባሪ ተናግረዋል፡፡ ከባለሃብቶች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ልማታዊ መንግስት ለግል ኢንቨስትመንት እያደረገ ያለው ድጋፍና እገዛ በርካታ ባለሃብቶች በሀገር ውስጥ እንዲፈጠሩ ከማድረጉም ባሻገር በድህነት ላይ ለሚደረገው ትግል የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉና ለብዙዎች የስራ ዕድል እንዲፈጠር ከፍተኛ እገዛ እያደረገ በመሆኑ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡ በሲዳማ ዞን ባለፈው በጀት ዓመት ከ267 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 45 ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=7107&K=1

ቴሌቪዥን ያደመቀው ምርጫ

Image
ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ነበር፡፡ ከአንድ የኢሕአዴግ ደጋፊ ወዳጄ ጋር ወደ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች አብረን ሄደን ነበር፡፡ በምርጫ ጣቢያዎቹ ስለተመለከትናቸው ጉዳዮች እያወራን ወደ ቤታችን እተመለስን ሳለን ከሁለት ወንዶች ጋር ፈጠን ፈጠን እያለች የምትጓዝ ሴት ጓደኛዬን ‹‹ደህና ነህ? እንዴት ነህ?›› በማለት ጠጋ ብላ፣ ‹‹አንተ አታውቀኝም እኔ ግን አውቅሃለሁ፤›› ትለዋለች፡፡ ጓደኛዬ ግራ በተጋባ አኳኋን ሰላምታ እየተለዋወጠ ሳለ ጊዜ ሳትሰጠው፣ ‹‹አልመረጥክም አይደለም? እባክህ ቁጥሩ አልሞላልንም፡፡ ጎድሎብናል ሂዱና ምረጡ፤›› ትላለች፡፡ በነገሩ ግራ መጋባቱ የሚያሳብቅበት ጓደኛዬ፣ ‹‹አይ መርጫለሁ›› ይላል፡፡ ‹‹ጓደኛህስ?›› ትለውና እሱም እየቀለደ፣ ‹‹ተይው እሱ አሸባሪ ነው፡፡ ተቃዋሚ ነው፤›› ይላታል፡፡ ‹‹አሃ የእኛ መስሎኝ'ኮ ነው›› የሚለውን ስሜታዊ ንግግሯን ሳትጨርሰው ወደ እኔ እያየች፣ ‹‹ለነገሩ ተቃዋሚም'ኮ ይመርጣል፤›› ትላለች፡፡ ‹‹ምንድን ነው የጎደለባችሁ?›› ብዬ ስጠይቃት፣ ‹‹ቁጥር አልሞላልንም፣ ሰው አልመጣም፤›› በማለት እቅጩን ነገረችን፡፡ ጓደኛዬ የሴትየዋ ንግግር እኔ ጆሮ መድረሱ ትንሽም ቢሆን ያስጨነቀው ይመስል፣ ‹‹አሃ መስማት የምትፈልገውን አገኘህ አይደል?›› እያለ መቀለድ ይጀምራል፡፡ እሑድ ሚያዝያ 6 ቀን 2005 ዓ.ም. በተካሄደው የአካባቢና የከተማ አስተዳደር ምርጫ፣ 31.6 ሚሊዮን መራጮች መመዝገባቸውን የአገሪቱ ምርጫ ቦርድ ያሳወቀ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገሪቱ 44,509 የምርጫ ጣቢያዎችም ለድምፅ መስጫ አገልግሎት ክፍት ሆነው ውለዋል፡፡ እንዲሁም ደግሞ ለዚሁ ለአካባቢ፣ ለአዲስ አበባና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምርጫዎች ከፍተኛ ዕጩዎች ያቀረበው ኢሕአዴግ በመሆኑ፣ ብቻውን 3.7 ሚሊዮን ተወዳ

ባለስልጣኑ የዕቅዱን ከ20 በመቶ በላይ ብልጫ ያለው ገቢ ሰበሰበ

Image
አዋሳ ሚያዝያ 08/2005 ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ከዕቅዱ ከ20 በመቶ በላይ ብልጫ ያለው ግብር በማሰባሰብ የከተማውን አጠቃላይ ወጪ መሸፈን መቻሉን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ገለጸ፡፡ በንግድ ስራ የተሰማሩ ሁሉም ድርጅቶች የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ መጠቀም እንዳለባቸው አስጠንቅቋል፡፡ የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ፍስሐ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከሐምሌ 2004 ወዲህ ባሉት ዘጠኝ ወራት ከ385 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ገቢ ተሰባስቧል፡፡ የመደበኛና ማዘጋጃ ቤት አገልግሎትን ጨምሮ ቀጥታና ቀጥታ ካልሆነ እንዲሁም ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች የተሰበሰበው የገቢ ግብር የዕቅዱን ከ20 በመቶ በላይና ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ከዕቅድ በላይ ማከናወን የተቻለው በከተማ አስተዳደርና በስሩ በሚገኙ ስምንቱ ክፍለ ከተሞች አመራሩና ሰራተኛው ከሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳ አሰራር እንዲከተሉ የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር በመዘርጋት ለግብር ከፋዩ ህብረተሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መሰጠርት ግልጽ፣ ፈጣንና ተጠያቂነት የሰፈነበት ስርዓት እንዲኖር በመደረጉ ነው ብለዋል፡፡ የሀዋሳ ከተማ ሰፊ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የሚካሄድበትና ከዚህ የሚመነጨውን የገቢ ግብር አቅም አሟጦ ለመጠቀም በተደረገ ጥረት አፈጻጸሙ ከምንግዜውም የተሻለ ጥሩና አመርቂ ደረጃ ላይ መድረሱን ስራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡ በዚህ ገቢ የከተማው አስተዳደር ከመንግስት ይደረግለት የነበረውን ድጎማ በማስቀረት ለካፒታል ፕሮጀክቶችና ሰራተኛ ደመወዝና ስራ ማስኬጃን ጨምሮ የከተማውን አጠቃላይ ወጪ በራሱ ለመሸፈን መቻሉን ገልጸዋል፡፡ የከተማው አሰተዳደር የገቢ ግብር በየአመቱ እየጨመረ ባለፈው በጀት አመት 2

በሴቶች ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሲዳማ ቡና ድል ቀናቸው

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሴቶች ውድድር የምደቡ የመጨረሻ ጨዋታ ሚያዝያ 7/2005 በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ተካሂዷል፡፡ በጨዋታው ሽታየ ሲሳይ 4 ጎል አስመዝግባለች ዘንድሮ በፕሪምየር ሊጉ ያገባችው ጎል 25 በማድረስ መሪነቷን አጠናክራ ቀጥላለች፡፡ አዳማ ከነማ መከላከያን 2 ለ 1 ቢያሸነፍም በግብ ተበልጦ ግማሽ ፍፃሜወን ሳይቀላቀል ቀርቷል፡፡ ከምድቡ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሲዳማ ቡና ኃላፊ ሆነዋል፡፡ ኃላፊው ክለብ ቀድሞ የተለየበት የምድብ 2 ጨዋታ ደግሞ 8 ሰዓት ላይ እና 12 ሰዓት ላይ ተካሂዷል፡፡ መውደቃቸውን ያረጋገጡት የመድህንና የድሬዳዋ ጨዋታ በመድህን 4 ለ 3 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ በደደቢት እና ሃዋሳ ከነማ መካከል የተካሄደው ጨዋታ ደግሞ ደደቢት 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ልዩነት አሸንፏል፡፡ ደደቢት እና ሃዋሳ ከነማ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል፡፡ በግማሽ ፍፃሜው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሃዋሳ ከነማ፣ ደደቢት ከሲዳማ ቡና ይጫወታሉ፡፡