ባለስልጣኑ የዕቅዱን ከ20 በመቶ በላይ ብልጫ ያለው ገቢ ሰበሰበ
አዋሳ ሚያዝያ 08/2005 ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ከዕቅዱ ከ20 በመቶ በላይ ብልጫ ያለው ግብር በማሰባሰብ የከተማውን አጠቃላይ ወጪ መሸፈን መቻሉን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ገለጸ፡፡ በንግድ ስራ የተሰማሩ ሁሉም ድርጅቶች የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ መጠቀም እንዳለባቸው አስጠንቅቋል፡፡ የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ፍስሐ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከሐምሌ 2004 ወዲህ ባሉት ዘጠኝ ወራት ከ385 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ገቢ ተሰባስቧል፡፡ የመደበኛና ማዘጋጃ ቤት አገልግሎትን ጨምሮ ቀጥታና ቀጥታ ካልሆነ እንዲሁም ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች የተሰበሰበው የገቢ ግብር የዕቅዱን ከ20 በመቶ በላይና ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ከዕቅድ በላይ ማከናወን የተቻለው በከተማ አስተዳደርና በስሩ በሚገኙ ስምንቱ ክፍለ ከተሞች አመራሩና ሰራተኛው ከሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳ አሰራር እንዲከተሉ የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር በመዘርጋት ለግብር ከፋዩ ህብረተሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መሰጠርት ግልጽ፣ ፈጣንና ተጠያቂነት የሰፈነበት ስርዓት እንዲኖር በመደረጉ ነው ብለዋል፡፡ የሀዋሳ ከተማ ሰፊ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የሚካሄድበትና ከዚህ የሚመነጨውን የገቢ ግብር አቅም አሟጦ ለመጠቀም በተደረገ ጥረት አፈጻጸሙ ከምንግዜውም የተሻለ ጥሩና አመርቂ ደረጃ ላይ መድረሱን ስራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡ በዚህ ገቢ የከተማው አስተዳደር ከመንግስት ይደረግለት የነበረውን ድጎማ በማስቀረት ለካፒታል ፕሮጀክቶችና ሰራተኛ ደመወዝና ስራ ማስኬጃን ጨምሮ የከተማውን አጠቃላይ ወጪ በራሱ ለመሸፈን መቻሉን ገልጸዋል፡፡ የከተማው አሰተዳደር የገቢ ግብር በየአመቱ እየጨመረ ባለፈው በጀት አመት 2