Posts

የምርጫ ዝግጅትና ተቃዉሞዉ በኢትዮጵያ፤ የሲዳማ አርነት ንቅናቄም በምርጫዉ እንደማይታፍ አስታዉቋል።

Image
ኢትዮጵያ ዉስጥ የመፊታችን ዕሁድ እና በሳምንቱ ዕሁድ በሚደረገዉ አካባቢ ምርጫ ከሠላሳ-አንድ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፁን ለመስጠት መመዝገቡን የሐገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙት ሠላሳ ሰወስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ግን በመጪዉ ዕሁድ በሚጀምረዉ አካባቢያዊ ምርጫ ላለመሳተፍ ወስነዋል። ኢትዮጵያ ዉስጥ የመፊታችን ዕሁድ እና በሳምንቱ ዕሁድ በሚደረገዉ አካባቢ ምርጫ ከሠላሳ-አንድ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፁን ለመስጠት መመዝገቡን የሐገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የቦርዱ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ይስማ ጅሩ እንደገለጡት በሁለት በተከፈለዉ ምርጫ ሃያ-አራት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የወከሉ ከስድስት ሚሊዮን በላይ እጩዎች ይወዳደራሉ። የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር አቶ ይስማ ጅሩን አነጋግሯቸዋል።የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙት ሠላሳ ሰወስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ግን በመጪዉ ዕሁድ በሚጀምረዉ አካባቢያዊ ምርጫ ላለመሳተፍ ወስነዋል። ፓርቲዎቹ እራሳቸዉን ከምርጫዉ ያገለሉበትን ምክንያት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ማስረዳታቸዉን አስታወቀዋል። የጋራ ትብብር የመሠረቱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረቡት ቅድመ-ሁኔታ ካልተሟላ በምርጫዉ እንደማይሳተፉ በተደጋጋሚ አስታዉቀዉ ነበር። የጋራዉ ትብብር መሪዎች እንዳሉት ይሕን ምክንያታቸዉን ሠሞኑን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገልፀዋል። በተመሳሳይ ዜና የሲዳማ አርነት ንቅናቄም በምርጫዉ እንደማይታፍ አስታዉቋል። የንቅናቄዉ ባለሥልጣናት እንደሚሉት አባላቶቻቸዉና ደጋፊዎቻቸዉ ይታሰራሉ፥ ይሸማቀቃሉም። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝር ዝር ዘገባ አለዉ። የምርጫ ዝግጅት የተቃዋሚዎች ውሳኔ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ሀዋሳ ከነማ መሪነቱን ያዘ

ሚያዝያ 3/2005 በአዲስ አባባ ስታዲየም ከኢትዮጵያ መድህን ያካሄደው ሐዋሳ ከነማ መሪነቱን ከደደቢት ተረክቧል። በሌላ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዳማ ከነማ ባካሄዱት ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ፕሪምየር ሊጉን ሐዋሳ ከነማ  በ28 ነጥብ እየመራ ሲሆን አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው በ27 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ የሚገኘው ደደቢት ሚያዝያ 4/2005 ዓ.ም በ12 ሰዓት ከሲዳማ ቡና ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል። በተመሳሳይ ዜና የደደቢት አሰልጣኝ አብርሃም ተክለሃይማኖት ከኃላፊነታቸው ለቀዋል።

19 ቁጥርና የሐዋሳው ልጅ

Image
አዳነ ግርማ ከምርጥ አስር አፍሪካዊ ተጫዋቾች ውስጥ በመካተት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ነው፤   ጆሴፍ ፔፕ ጋርዲዮላ የባርሴሎናን ክለብ ማሠልጠን እንደጀመረ የመጀመሪያ ስራው ያደረገው የክለቡን ነባር ተጫዋቾች በማሰናበት በምትካቸው በዝነኛው የክለቡ ማሠልጠኛ ማዕከል ( ላሜሲያ ) ያደጉ ተጫዋቾችን በዘመቻ መልክ ማሰባሰብን ነበር። ከነዚህ ተመላሽ ካታሎናውያን መካከል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በፈረንሳዊው አርሴን ቬንገር ለሚሰለጥነው አርሴናል አምበልና የመሃል ሜዳ አንቀሳቃሽ የነበረው ሴስክ ፋብሪጋስ ቀዳሚው ነበር። አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተጫዋቹን ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ለማስኮብለል ከተጠቀመባቸው አማራጮች መካከል አንዱ ራሱ በባርሴሎናና በስፔን ብሔራዊ ቡድን ሲጫወት ይለብሰው የነበረውን የማሊያ ቁጥር ( አራት ቁጥር ) እንደሚሰጠው ቃል መግባት ይገኝበታል። ሜክሲኮአዊው ራፋኤል ማርኬዝ ከባርሴሎና ጋር የነበረውን ኮንትራት አጠናቆ ወደ አሜሪካው ሜጄር ሶከር ሊግ ማምራቱን ተከትሎ ተሰቅሎ የቆየውን ማሊያ አውርዶ ለወጣቱ ጨዋታ አቀጣጣይ ሲሰጠው ተጫዋቹም በተደረገለት እንክብካቤ ከፍተኛ ደስታ ይሰማው ጀመር። ምክንያቱ ደግሞ በአርሴናል ይለብሰው የነበረውን አራት ቁጥር ማሊያ በአዲሱ ክለቡ ባርሴሎናም ለብሶ መጫወት ፍላጎቱ ስለነበር ነው። ከላይ የገለጽኩት ሐሳብ ለዕለቱ መጣጥፌ መግቢያ ይሆን ዘንድ የተጠቀምኩት ሐሳብ ነው። የዛሬው ጽሑፌ ማጠንጠኛ የሆነው ተጫዋች ተወልዶ ያደገው በደቡብ ክልል ዋና ከተማ ውቢቷ ሐዋሳ ሲሆን የመጀመሪያ ክለቡም የከተማዋ ተወካይ የሆነው ሐዋሳ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ነው። በዚሁ ክለብ ከተከላካይነት እስከ አማካይ መስመር ባሉት ቦታዎች ላይ የተሰጡትን ሚናዎች በሚገባ እየተወጣ ማደጉ ለአሁኑ ሁ

የሀዋሳ ከተማ የባሀል ማዕከል ግንባታ የመጀመሪያው ምዕራፍ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል

Image
ሀዋሳ ሚያዚያ 2/2005 በሀዋሳ ከተማ 70 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የሚካሄደው የባህል ማዕከል ግንባታ የመጀመሪያው ምዕራፍ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ የከተማ ማዘጋጃ ቤት ገለጸ፡፡ በማዘጋጃ ቤቱ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ መብራቴ መለሰ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በሀዋሳ መስቀል አደባባይ በ2003 ሀምሌ የተጀመረው የማዕከሉ ግንባታ ሁለገብ አዳራሽ፣ አንፊ ቲያትር ቤትና ሙዚየም አካቶ የሚይዝ ነው፡፡ በተለይ ቲያትር ቤቱን ይዞ 1500 መቀመጫ የሚኖረውና ለሁለገብ የስብሰባ አገልገሎት የሚውለው አዳራሽ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ሲሆን በእስካሁን እንቅስቃሴ ከአጠቃላይ ስራው 80 በመቶው መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ የቀሩት ጥቃቅን ስራዎችና የውሰጥ ድርጅት ማሟላት እስከ መጪው ሰኔ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ አመልከተው ሁለተኛው ምዕራፍ የሆነውና በ30 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚካሄደው የሙዚየሙን ግንባታ ለመጀመር ዝግጅት መጠናቀቁንና ስራው እሰከ መጪው አመት መግቢያ ድረስ እንደሚጠናቀቅ አስረድተዋል፡፡ የባህል ማዕከሉ መገንባት ሀዋሳ የቱሪዝም ከተማ እንደመሆኗ በኢንተርናሽናልና በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄዱ ስብሰባዎችን በብቃት በማስተናገድ የቱሪዝም ኮንፍራስ ከተማናቷን ከማሳደግ በሻገር የክልሉ ባህላዊ ቅርሶችና እሴቶችን አሰባስቦ ፣ ጠብቆና ተንከባክቦ ለማቆየት ከፍተኛ አስተዋጾኦ እንደሚኖረው አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡ ማዕከሉ የቢዝነስና ማንጅመንት ፕላን ይኖሩታል ብለዋል፡፡  Source: http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=6846&K=1

የደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኪሳራው እንዲከፈለው ጠየቀ

Image
አለመግባባት የሚያጦዘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ -    የደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኪሳራው እንዲከፈለው ጠየቀ -    ‹‹ነገሩ ግልፅ እንዲሆንልኝ መነጋገር እፈልጋለሁ›› እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ከእንቅልፉ ተነሳ ሲባል መልሶ እያንቀላፋ፣ ተነቃቃ ሲባል እየደከመው ከረጅም ዓመታት በኋላ የለውጥ ጭላንጭል የታየበት ቢመስልም፣ ጊዜና ወቅት እየጠበቀ በሚፈጠር አለመግባባት እንደገና ወደ ጡዘት የሚያስገባ ምልክት እየተስተዋለበት ነው፡፡ የእግር ኳሱን ፋና የሚያጨልም ሰው (ጓዳ) ሠራሽ ቢሮክራሲ የበላይነት፣ የሥልጣን ማሳያ ሽኩቻ፣ ያለመግባባት ፍጥጫ ቀዝቃዛ ውኃ ሲቸልስበት ኖሯል፡፡ እነዚህ ጉዳዮች አሁንም እግር ኳሱ ቀና ቀና ማለት በጀመረበት ቅጽበት እንኳ የተቀየሩና የቀሩ አልመስል እያሉ ጉዞውን አስቸጋሪ እያደረጉበት ይገኛል፡፡ ከሰሞኑ የሚታየው ውዝግብም ኳሱ ከተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የውድድር መድረኮች ለዓመታት ተገልሎ የቆየበት ምክንየት ምን ነበር? የነበረውን ችግር ከሥር መሠረቱ ለመፍታት የተደረገው ጥረት ምንድነው? ዛሬስ ከዓመታት መገለል በኋላ ምን ዓይነት ለውጥና ዕድገት አምጥቶ ነው መድረኩን የተቀላቀለው? በሚሉትና ሌሎችም ተመሳሳይ የችግር አፈታት ሒደቶች ላይ የተመሠረተ ሳይሆን፣ የሥልጣን ድርሻና የበላይነት ላይ የተመሠረተ ሆኖ መታየቱ መንግሥትንም የሚያስተቸው መሆኑ አልቀረም፡፡ መንግሥት ‹‹ዘርፉ ከፖለቲካው ጨዋታ ውጭ እስከሆነ ድረስ ምንም ቢፈጠር ዝምታን ይመርጣል›› የሚለው የብዙዎች ትችት ወደ ኳሱም አካባቢ እየተዛመተ ስለመሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ እነዚሁ አካላት መንግሥት በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ እያከናወነ ካለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክንውኖች ስፖርቱን