Posts

የሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ በምርምር የተገኙ የተለያዩ የምግብ ሰብል ዝርያዎችና ቴክኖሎጂዎችን በማላመድና በማስተዋወቅ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡

Image
የሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ በምርምር የተገኙ የተለያዩ የምግብ ሰብል ዝርያዎችና ቴክኖሎጂዎችን በማላመድና በማስተዋወቅ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ዩኒቨርሰቲው በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች 120 የምርምር ፕሮጀክቶችን እያካሄደ ነው፡፡ በሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ የምርምር ልማት ዳይሬክቶሬት የህብረተሰብ አገልግሎት ዘርፍ ባለሙያ አቶ ባዩ ቡንኩራ  ለኢ ዜ አ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲው ሀዋሳን ጨምሮ በሲዳማ ዞን በተመረጡ ስድስት ወረዳዎች የተቋቋሙ የቴክኖሎጂ መንደሮች አማካኝነት አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው፡፡ በእነዚህ ወረዳዎች ከ360 በላይ ሞዴል አርሶ አደሮችን በማሳተፍ ካለፈው ክረምት ጀምሮ በዩኒቨርሰቲውና ሌሎች የምርምር ተቋማት የተገኙና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የተለያዩ ስኳር ድንች(በአማካኝ በሄክታር 283 ኩንታል) ፣ የቦሎቄ፣ የቢራ ገብስ፣ የቦቆሎና ሌሎችም የሰብል ዝርያዎች በአርሶ አደሩ ጓሮና ማሳ ላይ ጭምር በማላመድና በማስተዋወቅ ተጠቃሚ እየሆኑ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት ካለው የበልግ እርሻና በመስኖ ጭምር በመጠቀም አዳደስ የሰብል ዝርያዎች አርሶ አደሩ እንዲጠቀም ከማስፋፋት በተጨማሪ ከእርሻ አያያዝና ከማዳባሪያ አጠቃቀም ጋር ያሉ ችግሮችን በመለየትና በተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችም የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና ለማስፋፋት ዩኒቨርስቲው ሰፋፊ ፕሮግራሞችን ዘርግቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ችግር ፈቺ የሆኑ 120 የምርምር ፕሮጀክቶችን በተለይም በግብርና፣ በምግብ ሳይንስ፣ በደን፣ በጤና፣ ትምህርት፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በኢኮኖሚ፣ በተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፎች ምርምር  እያካሄደ ነው፡፡ http://www.ertagov.com/amharic/index.php/component/k2/it

የአለም የጤና ድርጅት የአዕዋፍ ኢንፉሌንዛ ከሰው ወደ ሰው ስለመተላለፉ መረጃ አላገኘሁም አለ

Image
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የአእዋፍ ኢንፉሌንዛ ቻይና ውስጥ መከሰቱ የተሰማው ባሳለፍነው ሳምንት ነው። ከአእዋፍ ወደ ሰው በመተላለፍ እስከ አሁን የሁለት ሰዎች ህይወትን አጥፍቷል ፡፡ በቻይና የአለም የጤና ድርጅት ተወካይ እንዳሉት ከሆነ ፥ ከበሽታው ተጠቂዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት በነበራቸው 80 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ በበሽታው እንዳልተያዙ ለማረጋገጥ ተችሏል ፡፡ ኤች ሰባት ኤን ዘጠኝ ተብሎ የተሰየመው ይህ ቫይረስ እስካሁን  ክትባትም ይሁን መድሃኒት አልተገኘለትም፡፡

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በመጪዎቹ ግንቦትና ሰኔ የሙከራ ምርት ይጀምራል

Image
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በመጪዎቹ ግንቦትና ሰኔ የሙከራ ምርት የሚጀምር ሲሆን ፥ ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅም ሶስቱ ነባር የስኳር ፋብሪካዎች ከሚያመርቱት በ2 እጥፍ የሚበልጥ ምርት እንደሚያስገኝ የስኳር ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ። የተንዳሆ ስኳር ልማት ፋብሪካ ከእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ በፊት ሊጠናቀቅ ባለማቻሉ በእቅድ ውስጥ እንዲካተት የተደረገ ነው። በመጠናቀቅ ላይ ነው የሚገኘው የዚሁ ፋብሪካ የመስኖ ልማትም በውሀና ኢነርጂ ሚንስቴር ነው የተሰራው ሲሆን ፥ በአሁኑ ወቅት ግድቡ ተግንብቶ ውሀ እንዲይዝ ተደርጓል ፣ ከ42 ኪሎሜትር በላይ የዋና ቦይ ዝርጋታም ተከናውኗል። ለስኳር ምርት ዋና ግብአት የሆነው የሸንኮራ አገዳ ልማትም ተከናውኗል ፥ በዚህም መሰረት ከ8 ሺህ ሄክታር በላይ የተተከለው የሸንኮራ አገዳ በጥሩ ሁኔታ እያደገ ነው ብለዋል በኮርፖሬሽኑ የዋና ዳይሬክተር አማካሪና የህዝብ ግንኙነት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዲንጋሞ። ፋብሪካው በመጀመሪያው ዙር 13 ሺህ ቶን ሸንኮራ በቀን በመፍጨት ነው ማምረት የሚጀምር ሲሆን ፥ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ደግሞ ቀደም ካሉት 3 ፋብሪካዎች ሁለት እጥፍ ሸንኮራ ይፈጫል ነው የተባለው። በአሁኑ ወቅት የፋብሪካው የመጀመሪያ ደረጃ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ያለ ሲገኝ ፥  ከሁለት ወራት በኋላ ደረጃ በደረጃ ወደ ምርት ይሸጋገራልም ነው ያሉት አቶ አስፋው ። ይህኛው እያመረተ የሁለተኛው ዙር ግንባታ ሲጠናቀቅም በቀን26 ሺህ ቶን ሸንኮራ ወደሚፈጭበት ደረጃ ይደርሳል ብለዋል ። http://www.fanabroadcasting.com/

ዘንድሮ “ኃይሌ ገብረስላሴ ማራቶን” በሃዋሳ ከተማ መካሄዱ ትኩረት እየሳበ ነው

Image
ኃይሌ በ40 ዓመቱ ይሮጣል በሃዋሳ በስሙ የሚያዘጋጀው ማራቶን ትኩረት እያገኘ ነው በቅርቡ 40ኛ ዓመቱን የሚይዘው ኃይሌ ገብረስላሴ በ “ግሬት ማንችስተር ራን” እንደሚሳተፍ የውድድሩ አዘጋጆች አስታወቁ፡፡ ስለተሳትፎው የተጠየቀው ኃይሌ ‹‹ሩጫ ስለሚያስደስትኝ መሮጤን እቀጥላለሁ፤ መቼ እንደሚያበቃልኝ አላውቀውም፤ ወደ ማንችስተር ተመልሼ ለመወዳደር የምችልበትን እድል መተው አልችልም›› ብሏል፡፡ ኃይሌ በ “ግሬት ማንችስተር ራን” የ10 ኪሎሜትር ሩጫ ለ6 ጊዜያት ሲያንፍ፤ ላለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት የውድድሩ አሸናፊ ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘንድሮ “ኃይሌ ገብረስላሴ ማራቶን” በሃዋሳ ከተማ መካሄዱ ትኩረት እየሳበ ነው፡፡ የውድድሩ አምባሳደር አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ለተሳታፊዎች ባቀረበው በጥሪ ለ20 ዓመታት ካሳለፈው የሩጫ ዘመን በኋላ ዓለምን ወደ አገሩ ኢትዮጵያ ሲጋብዝ በታላቅ ጉጉት እንደሆነ ገልጿል፡፡ የኃይሌ ገብረስላሴ ማራቶን በኢትዮጵያ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የውድድር አዘጋጆች በተሰባሰቡበት ቡድን የሚመራ ሲሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ቀለሙ ኢትዮጵያዊ ማራቶን ነው ተብሏል፡፡ ከ1200 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚኖሩት ከሚጠበቀው ኃይሌ ገብረስላሴ ማራቶን ጋር በመያያዝ የግማሽ ማራቶን፤ የ5 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እና የህፃናት ውድድሮችም ይደረጋሉ፡፡በውድድሩ ኦፊሴላዊ ድረገፅ በቀረበው መረጃ መሰረት በኃይሌ ገብረስላሴ ማራቶን ተሳታፊ ለሚሆኑ ራጮች የጉብኝት ፕሮግራም የተዘጋጀ ሲሆን የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ ለማስተዋወቅ ታስቧል፡፡ የኃይሌ ገብረስላሴ ማራቶን ጋር ተያይዞ በሚደረገው የገቢ ማሰባሰብ 200ሺ ዶላር ለእንጦጦ ፋውንዴሽን እንደሚበረከትም ታውቋል፡፡ በኃይሌ ገብረስላሴ ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች

መድረክ የብሄራዊ አንድነት መንግስት እንዲቋቋም ጠየቀ

ኢህአዴግ “ህዝባዊ መሠረት” ካላቸው ፓርቲዎች ጋር ተወያይቶ የአገሪቱን ችግሮች እንዲፈታ ተጠየቀ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) የኢትዮጵያን ወቅታዊና መሠረታዊ ችግሮች የመፍቻ አቅጣጫዎች ያመላክታል ብሎ ይፋ ባደረገው ማኒፌስቶው፤ በአሁን ወቅት አገሪቱ በዘርፈ ብዙ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ እንደምትገኝ ጠቅሶ፤ ከነዚህ ችግሮች ለመውጣት ገዥው ፓርቲ ሃላፊነት በመውሠድ ከሁሉም ህዝባዊ መሠረት ካላቸው የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ተወያይቶ መፍትሄ መሻት እንዳለበት አሣሠበ፡፡ መድረክ ለጋዜጠኞች ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ማኒፌስቶው፤ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊ መስክ፣ በትምህርት፣ በጤና እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ዘርፍ ውስጥ አሉ የሚላቸውን የሃገሪቱን ችግሮች ያላቸውን በዝርዝር አቅርቧል፡፡ ፓርቲው በፖለቲካው ዘርፍ ይስተዋላሉ ብሎ ካቀረባቸው ችግሮች መካከል በሃገራችን የመድብለ ፓርቲ ስርአት ግንባታ መጨናገፉ፣ የህግ የበላይነት እና ገለልተኛነት እንይረጋገጥ በየደረጃው ተጠያቂነት አለመኖሩ፣ ሃሣብን በነፃ የመግለፅ መብት ከመደብዘዝ አልፎ ለመጥፋት መቃረቡ፣ የዲሞክራሲ ተቋማት አለመኖርና አሉ የሚባሉትም (ፓርላማ፣ ምርጫ ቦርድ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ሠብአዊ መብት ኮሚሽን) በኢህአዴግ ፍፁማዊ ተፅዕኖ ስር የሚንቀሣቀሡ መሆናቸው፣ ከምርጫ 97 ጀምሮ በሲቪክ ማህበረሠብና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች (መያዶች) ላይ አዲስ ህግ በማውጣት ጥቃት መክፈቱ፣ ህገመንግስቱ ለነፃ ፕሬስ የሠጠውን መብት በጠራራ ፀሃይ እየጣሠ መሆኑ፣ ሃቀኛ ተቃዋሚዎችን የሚደግፉ ዜጐችን ሠርቶ የመኖር መብት መንፈጉ፣ በሃቀኛ ተቃዋሚዎች ላይ ሠፊ የማጥላላት ዘመቻ ማካሄድ እና ከሠላማዊና ከህጋዊ ፓርቲዎች ጋር ስለ ፖለቲካ ምህዳሩ ለመደራደር አሻፈረኝ ማለቱን በዝርዝር ገል