በደቡብ ክልል ሐሰተኛ የብቃት ማረጋገጫ አቅራቢዎች ተበራክተዋል
ከተለያዩ ተቋማት በመመረቅ ሥራ ለመቀጠር ወሳኝ ለሆነው የብቃት ማረጋገጫ ሐሰተኛ ማስረጃ የሚያቀርቡ ግለሰቦች እየበዙ መሆናቸውን፣ አንዳንድ ቀጣሪ ድርጅቶች ሲገልጹ፣ የደቡብ ክልል ልቀት ማዕከል ችግሩን ለመቅረፍ ድረ ገጽ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ በተደጋጋሚ ምዘናውን ወስደው ብቁ መሆን ያልቻሉ በቢዝነስና በጤና ዘርፎች በተለይም የደረጃ ሦስትና አራት ዲፕሎማ የተወሰኑ ተመራቂዎች ነን የሚሉ፣ ሐሰተኛውን ሰነድ በማሠራት መጠቀም እንደ አማራጭ መውሰዳቸውን ድርጅቶቹ ጠቁመው፣ ትክክለኛውንና ሐሰተኛውን ለመለየት መቸገራቸውን ይናገራሉ፡፡ የደቡብ ክልል የልቀት ማዕከል በበኩሉ ሐሰተኛ የብቃት ማረጋገጫ ለሥራ ውድድር የሚያቀርቡ ግለሰቦች መኖራቸውን አምኖ፣ በርካታ ቀጣሪ መሥርያ ቤቶች እንዲጣራላቸው በሚልኩት ጥያቄ መሠረት ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሐሰተኛ ማስረጃዎችን አጣርቶ ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቁን አስረድቷል፡፡ በትምህርት፣ በቢዝነስ፣ በጤናና በሌሎች ተያያዥ የትምህርት ዘርፎች ለመጠርጠር አስቸጋሪ የሆኑ የምዘና ብቃት ማረጋጫዎች እንደሚቀርቡና ለማዕከሉ ካልተላከ በስተቀር መለየት ከባድ እንደሆነ በሐዋሳ ከተማ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንዳንድ ቀጣሪ ተቋማት ይገልጻሉ፡፡ “ለሥራ ቅጥር ማስታወቂያ አውጥተን ካልተጠራጠርን መለየት የማይቻሉ የሲኦሲ መረጃዎች ይቀርባሉ፡፡ ሐሰተኛ መሆናቸውን ማዕከሉ አጣርቶ ሲልክልን ብቻ ነው ምናውቀው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ችግሮቹን ካየን በኋላ ስንቀጥር ወደ ማዕከሉ ለመላክ ተገደናል፤” በማለት የሚናገሩት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአንድ የግል ድርጅት አስተዳደር ኃላፊ ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ አስቸኳይ ቅጥር ለማድረግ እንኳ እምነት ማጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ “ለሦስትና ለአራት ዓመታት በአግባቡ የሠለጠ