ኢትዮጵያ የቀርከሃ ዘላቂ ልማት መሰረት በመጣል አረንጓዴ ኢኮኖሚን ግንባታ ስትራቴጂ ቀይሳለች -ግብርና ሚኒስቴር
ኢትዮጵያ የቀርከሃ ተክልን ዘላቂ ልማት መሰረት በመጣል አረንጓዴ ኢኮኖሚዊ የግንባታ ስትራቴጂ መቀየሷንና የዘርፉን ኢንዱስትሪ የማስፋፋት ስራም አጠናክራ መቀጠሏን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ አህጉራዊ የቀርከሃ አውደ ጥናት መጋቢት 6/2005 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ሲጀመር የግብርና ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ምትኩ ካሳ እንዳስታወቁት በኢትዮጵያ ያለው የቀርከሃ ሃብት እንዲጠበቅና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስችል ስትራቴጂ ተነድፎ ተግባራዊ እየተደረገ ነው፡፡ የቀርከሃ ልማት በአገሪቱ እንዲጠናከርና ከተክሉ የሚገኙ ልዩ ልዩ ውጤቶችንና ምርቶችን በማስፋፋት ጥቅም እንዲውሉ መንግስት የጀመረውን ጥረትና ቁርጠኝነት ደረጃ በደረጃ እያጠናከረ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ የዓለም ዓቀፉን የቀርከሃና ራታን ኔት ወርክ ለሁለት ዓመታት በሊቀ መንበርነት እንድትመራ በ15ኛው የተቋሙ የምስረታ ዓመት ላይ በቅርቡ መመረጧን አስታውሰው የተቋሙ ምክር ቤት በቻይና ባካሄደው 8ኛ ጉባኤ ይህን ኃላፊነት ለኢትዮጵያ መስጠቱንም ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በአውሮፓውያን 2014 ዘጠነኛውን የኔትወርኩ ምክር ቤት ጉባዔን ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ መመረጧን ገልጸው ጉባኤውን አዲስ አበባ ለማስተናገድ መዘጋጀቷንም አመልክተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከ15 ዝርያ የሚበልጡ የቀርከሃ ተክል ያለባት አገር መሆኗን አስታውሰው ይህን ተክል በማልማት የአካበቢ መጎሳቆልንና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል አገራዊና አህጉራዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም ዓቀፋዊ ሚናዋን ኢትዮጵያ እንደምትጫወት አስታውቀዋል፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታደሰ ኃይሌ በበኩላቸው ቀርከሃ ለፋብሪካ ግብዓት ከሚውሉ የደን ውጤቶች አንዱ በመሆኑ ለኢንቨስትመንትና የስራ ዕድል በ