የፀረ ኤችአይቪ ሕክምና ተስፋ ፈንጣቂ ዕርምጃ
ባለፈው ሳምንት ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ሆና የተወለደች ሕፃን ወዲያው በተደረገላት ሕክምና ከቫይረሱ ነፃ የመሆኗ ዜና መሰማት በዓለም ኤችአይቪን በመዋጋት ረገድ ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ተስፋ ፈንጣቂ ሆኗል፡፡ አሜሪካ ሚሲሲፒ ውስጥ እ.ኤ.አ. 2010 ላይ የተወለደችው ሕፃን ከቫይረሱ ነፃ ልትሆን የቻለችው እንደተወለደች ባሉት 30 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ የፀረ ኤችአይቪ ሕክምና ተደርጐላታል፡፡ ሕክምናው በዚያም ሳያበቃ ለአሥራ ስምንት ወራት ዘልቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሕፃኗ ከቫይረሱ ነፃ መሆኗን ይፋ ያደረገው በባልቲሞር የሚገኘው የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ቡድን መሪ ዶክተር ዲቦራ ፐርሳውድ ግኝቱ ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ሆነው የሚወለዱ ሕፃናትን ከኤችአይቪ ኢንፌክሽን ነፃ በማድረግ ሕክምና ትልቅ ዕርምጃ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ቢሆንም ግን ተመራማሪዎቹ ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ሆነው የሚወለዱ ሕፃናትን ሕፃኗ ከተፈወሰችበት መንገድ በተሻለ ሕክምና ከኢንፌክሽኑ ነፃ ማድረግ፣ በተለይም ሕክምናውን ለስድስት ሳምንታት ማሳጠር ሊተኮርበት የሚገባ ነገር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሕፃናት የኤችአይቪ ፖዘቲቭ ኢንፌክሽንን በመከላከል ረገድ የኤችአይቪ ቫይረስ ከእናቶች ወደ ሕፃናት እንዳይተላለፍ የሚደረግ ሕክምና ዓይነተኛው መፍትሔ ነው፡፡ ነገር ግን ሕክምናው በቀላሉ በሚገኝባቸው እንደ አሜሪካ ባሉ የበለጸጉ አገሮች እንኳ ሕፃናት ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ሆነው ይወለዳሉ፡፡ ለምሳሌ አሜሪካ ውስጥ በየዓመቱ ከ100 እስከ 200 የሚሆኑ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሕፃናት ይወለዳሉ፡፡ የሮይተርስ ዘገባ እንደሚያመለክተው ዓለም ላይ በተለይም በማደግ ላይ በሚገኙ አገሮች በቀን አንድ ሺሕ የሚሆኑ ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ሕፃናት ይወለዳሉ፡፡ ግኝቱ ለእነዚህ ሕፃናት ትልቅ ተስፋ ነው፡፡ የ28 ዓመቷ አሜሪካዊ