Posts

የኬንያ ምርጫ ወዲህ የኢትዮጵያ ወዲያ

Image
የኬንያ ምርጫ ወዲህ የኢትዮጵያ ወዲያ шаблоны RocketTheme Форум вебмастеров ኬንያ በአፍሪካ በተለይ ደግሞ በምሥራቅ አፍሪካ የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ብቻ ሳይሆን የተረጋጋ ፖለቲካ ያላት ተብላ የምትደነቅ አገር ነበረች፡፡ እ.ኤ.አ በ2007  የተካሄደውን አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ የተከሰተው የእርስ በእርስ ግጭት ግን ከአንድ ሺሕ በላይ ሰዎችን ለሕልፈት ሲዳርግ፣ ከ600 ሺሕ የሚበልጡ ከቀዬአቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል፡፡ ባለፈው ሰኞ የተከናወነው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አጠቃላይ ሒደቱ ሰላማዊ የሚባል ቢሆንም፣ ከወዲሁ የሚያስፈራ ፍንጭ አሳይቷል፡፡ ምርጫው በአብዛኛው ሰላማዊ የሚሰኝ ቢሆንም፣ በወደብ ከተማዋ ሞምባሳ አካባቢ ሞምባሳ ሪፐብሊካን ምክር ቤት (MRC) በመባል የሚታወቅ ተገንጣይ ቡድን በቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት የ19 ሰዎች ሕይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡ ያለፈው ምርጫ የፈጠረው ጦስ ለኬንያውያን ያስፈራቸው መሆኑን በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡ ሲሆን፣ ምርጫው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በታገዘ የድምፅ አሰጣጥ ዘዴ ተከናውኗል፡፡ የብዙዎቹ  ሥጋት በዋና ተፎካካሪዎቹ መሀል ጎሳን መሠረት ባደረጉ የፖለቲካ ድጋፍና ድምፅ የማግኛ ሥልቶች ምክንያት፣ የምርጫ ውጤቱን አሜን ብሎ የሚቀበል ተፎካካሪ አይኖርም የሚል ነው፡፡ ይህ በድጋሚ ወደ ጎሳ ግጭት ሊመራል ይችላል በሚል፡፡ ኬንያና ኢትዮጵያ ወዴት? ኢኮኖሚዋ በምሥራቅ አፍሪካ የተሻለ አቅም እንዳለው የምትታወቀው ኬንያ ፊታውራሪ በሆነችበት የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ (EAC) ኡጋንዳና ታንዛኒያን አስከትላ በአካባቢው በአንድ ፓስፖርት፣ በአንድ ዓይነት ገንዘብና በአንድ የተማከለ ሕገ መንግሥት የሚመራ የፖለቲካ ማኅበረሰብም ለመፍጠር ተስፋ ተጥሎባት ነበር፡፡ እንዳተባ

የሃዋሳ ከተማ አሰተዳደር ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ፡፡

Image
አዋሳ የካቲት 27/2005 የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ስድስት ወራት ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አስታወቁ ። የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ191 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ አለው፡፡ ከንቲባው አቶ ዮናስ ዮሰፍ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ገቢዉ የተሰበሰበዉ ቀጥታና ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች፣ከማዘጋጃ ቤት አገልግሎትና ከሌሎች ገቢዎች ነዉ ። በከተማው የገቢ አስተዳደር ስራዎችን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የታክስ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ በመደረጉ የተሰበሰበው ገቢ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል ። ገቢዉ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ191 ሚሊዮን 252 ሺህ 029 ብር ብልጫ እንዳለው አስታዉቀዋል ። በከተማ አስተዳደሩ ተቀርፆ እየተተገበረ ያለው የታክስ ማሻሻያ ፕሮግራም፣ አዳዲስ ግብር ከፋዮች ወደ ታክስ ስርዓቱ መግባታቸውና ግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ግዴታውን በአግባቡ መወጣት መጀመሩ ለገቢው ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቁመዋል። በግማሽ በጀት ዓመቱ የግብር ከፋዩን ቁጥር ለማሳደግ አመራሩ፣ ባለሙያውና ሌሎች የባለድርሻ አካላት ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት በደረጃ ሀ እና ለ 1ሺህ 564 ግብር ከፋዮች ወደ ግብር ስርዓቱ መግባታቸውን የገለጹት አቶ ዮናስ እነዚህ ግብር ከፋዮች ግዴታቸውን በአግባቡ መወጣት ጀምረዋል ብለዋል ። በተጨማሪ በከተማ አስተዳደሩ የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን መጠቀም ያለባቸው ግብር ከፋዮች መሳሪያውን ገዝተው እንዲጠቀሙና የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ ጤናማና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን 1ሺህ 177 የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኖችን ለግብር ከፋዩ ህብረተሰብ እንዲሸጥ መደረጉን ገልጠዋል ። በቀጣ

መገናኛ ብዙሃን የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያደርጉትን የቅስቀሳ ፕሮግራም በተገቢው መንገድ ሊያስተናግዱ ይገባል

አዲስ አበባ የካቲት 27/2005 መገናኛ ብዙሃን በ2005 ዓ.ም ለሚካሄደው የአካባቢና የአዲስ አበባ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያደርጉትን የቅስቀሳ ፕሮግራም በተገቢው መንገድ እንዲያስተናግዱ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አሳሰበ፡፡ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከመጪው መጋቢት 4 ቀን እስከ ሚያዚያ 4/2005 ድረስ ለሚያቀርቡት የምርጫ ቅስቀሳ የሬዲዮና የቴሌቪዥን የአየር ሠዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል በዕጣ ተከናውኗል፡፡ የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ልዑል ገብሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት መገናኛ ብዙሃን ፓርቲዎች የሚያቀርቡትን የቅስቀሳ ፕሮግራም ህግና መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት በአግባቡ ማስተናገድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ድልድሉ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ባፀደቀው መመሪያ መሰረት መከናወኑንና 50 በመቶ ሁሉም ፓርቲዎች በእኩል የሚካፈሉት ሆኖ 30 በመቶ በሕዝብ ተወካዮችና በክልል ምክር ቤቶች ባላቸው ብልጫ፣ 20 በመቶውን ጊዜ ደግሞ ባቀረቡት እጩ ተወዳዳሪ ብዛት የሚጠቀሙ ይሆናል፡፡ በዚሁ መሰረትም 24ቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሬዲዮ 19 ሠዓት ከ20 ደቂቃ፣ በቴሌቪዥን 12 ሠዓትና በተለያዩ ጋዜጦች 48 አምዶችን ያለምንም ክፍያ የምርጫ ቅስቀሳቸውን እዲያካሂዱ መደልደሉን ተናግረዋል፡፡ ለዚሁ ስራ የተመደበው የአየር ሠዓትና የጋዜጣ አምድ በገንዘብ ሲተመን ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ያህል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ይህም ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ፖሊሲያቸውን፣ ስትራቴጂያቸውንና ፕሮግራማቸውን ለህብረተሰቡ በነጻነት እንዲያቀርቡ መንግሥት ካለው ቁርጠኝነት አንጻር የተደረገ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በተደረጉ ምርጫዎች ልምድ እንደታየው የተመደበላቸውን የአየር ሠዓትና የጋዜጣ አምድ ያለመጠቀም ችግር መታየቱን ያስታወሱት አቶ ልዑል ፓርቲዎች የተሰጣቸውን እ

ሲዳማ ኔትን ጨምሮ 16 የኣሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት እገዳ ተጣለባቸው

Image
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ 16  የአሸከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ እገዳ ጣለ። በደቡብ ክልል ፍቃድ አግኝተው ስልጠና የሚያካሂዱ 36 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማትን ፥ በክልሉ የሚከሰተውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል ሲባል የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ  ተቋማቱን  በአመታዊ እቅዱ ያሳትፋቸዋል። የቢሮው ሃላፊ አቶ ታገሰ ኤሮሞ እንደሚሉት ፥ እንዲሳተፉ በተደረገበት እቅድ ደግሞ አንድ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋም ለማሰልጠን ሊያሟላ የሚገባቸው መስፈርቶች ተካተዋል። የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ባለሙያዎች በተቋማቱ ላይ ባደረጉት ግምገማ ፥ 8 ያህሉ በተገኘባቸው ጉድለት በማስጠንቀቂያ ሲታለፉ ፥ 16ቱ ደግሞ ስልጠናውን  የሚሰጡበት ተገቢ ቦታ  የሌላቸው ፣ የራሳቸው የማለማመጃ  መኪና ሳይኖራቸው በኪራይ የሚጠቀሙ  ፤ በቂ ክህሎት ያለው አሰልጣኝ ሳይኖራቸው በመስራታቸው እርምጃው ሊወሰድባቸው እንደተቻለ ይናገራሉ። 12 ተቋማት ደግሞ በተካደው ግምገማ አንጻራዊ ለውጥ በማምጣታቸው ያለምንም ማስጠንቀቂያ ስራቸውን እንዲቀጥሉ የተደረጉ ናቸው። በቤንች ማጂ ፣ ስልጤ ዞን ወራቤ ፣ ጋሞ ጎፋ ፣ ሲዳማ ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጉራጌ ዞኖች ላይ የሚገኙ  ናቸው እነዚህ ተቋማት። ሲዳማኔት ፣ ፊውቸር ላይት ፣ ዎስመካ  ፣ ጋላክሲ ፣ መካነ ኢየሱስ ፣ መገናኛ ፣ ወራቤኬሪ ፣ ፍሬም ፣ ኢሻ ፣ ዱዛ ፣ ጂፎር ፣ ወገሹር ፣ አግነት ፣ እና ሚቴማ እርምጃው የተወሰደባቸው ተቋማት ናቸው። ተቋማቱ በስልጠና ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን በተጓደለ መልኩ እንዳያስመርቁም  ፤ በየጊዜው ልዩ ክትትል እየተደረገባቸው ስልጠናውን እንዲጨርሱ  አቅጣጫ መቀመጡን ነው ሃላፊው የተናገሩት። እገዳ ስለተጣለባቸው ተቋማት ህብረተሰቡ እንዲያውቅ

በደቡብ ክልል ትምህርት ቤቶች መካከል ሲካሄድ የቆየው የስፖርት ውድድር በሲዳማ ዞን ትምህርት ቤቶች የበላይነት ተጠናቀቀ፡፡

Image
በውድድሩ በክልሉ 11 ዞኖች፣ ሶስት ልዩ ወረዳና በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ ከ250 የሚበልጡ የሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ ከ3ሺህ በላይ ወንድና ሴት ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በውድድሩ የሲዳማ ዞን ትምህርት ቤቶች በጤረጴዛ ኳስ፣ በአትለቲክስ ወንዶችና ሴቶች በአጠቃላይ ውጤት አሸናፊ በመሆን ሰባት ዋንጫዎችን ወስደዋል፡፡ የካምባታ ጣምባሮ ዞን ትምህርት ቤቶች ደግሞ በእጅ ኳስ ወንዶችና ሴቶች፣ መረብ ኳስ ሴቶች ሶስት ዋንጫ በማንሳት ዞኑ ውድድሩን በሁለተኛነት እንዲያጠናቅቅ አስችሎታል፡፡ የጉራጌ ዞን ትምህርት ቤቶች ቅርጫት ኳስ በሁለቱም ፆታ አሸናፊ በመሆን ዞኑ በሶስተኛ ደረጃ ውድድሩን እንዲያጠናቅቅ ያደረጉት ሲሆን የሰገን አከባቢ ህዝቦች ዞን ትምህርት ቤቶች በእግር ኳስ፣የወላይታ ዞን በወንዶች መረብ ኳስ አሸናፊ በመሆን አንዳንድ ዋንጫ ወስደዋል፡፡ የሀዲያ ዞን ትምህርት ቤቶች ከመጀመሪያው እስከ   ፍፃሜው ባሳዩት ስፖርታዊ ጨዋነት የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ከየካቲት 10 እስከ 21/ 2005 በተካሄደው ውድድር ክልሉን ወክለው በአዲስ አበባ በሚካሄደው አገር አቀፍ የትምህርት ቤቶች ውድድር የሚሳተፉ ከ400 በላይ ስፖርተኞች ተመርጠዋል፡፡ የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍ ለውድድሩ አሸናፊዎች፣ ለኮከብ ዳኞች፣ ተማሪዎች፣ለውድድሩ መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት፣ ድርጅቶችና ግለሰቦች ዋንጫ፣ ሜዳሊያና ምስክርወረቀት ካበረከቱ በኃላ እንደገለጹት ስፖርት ለአንድ አገር ማህበራዊና ኢኮኖሚ እድገት ከሚኖረው ፋይዳ በተጨማሪ በብሄር ብሄርሰቦች መካከል ያለውን አንድነትና የባህል ትስስር ለማጠናከር የላቀ ሚና አለው፡፡ መንግስት ይኸንን በመገንዘብ ከሁሉም የባለ