በደቡብ ክልል ትምህርት ቤቶች መካከል ሲካሄድ የቆየው የስፖርት ውድድር በሲዳማ ዞን ትምህርት ቤቶች የበላይነት ተጠናቀቀ፡፡
በውድድሩ በክልሉ 11 ዞኖች፣ ሶስት ልዩ ወረዳና በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ ከ250 የሚበልጡ የሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ ከ3ሺህ በላይ ወንድና ሴት ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በውድድሩ የሲዳማ ዞን ትምህርት ቤቶች በጤረጴዛ ኳስ፣ በአትለቲክስ ወንዶችና ሴቶች በአጠቃላይ ውጤት አሸናፊ በመሆን ሰባት ዋንጫዎችን ወስደዋል፡፡ የካምባታ ጣምባሮ ዞን ትምህርት ቤቶች ደግሞ በእጅ ኳስ ወንዶችና ሴቶች፣ መረብ ኳስ ሴቶች ሶስት ዋንጫ በማንሳት ዞኑ ውድድሩን በሁለተኛነት እንዲያጠናቅቅ አስችሎታል፡፡ የጉራጌ ዞን ትምህርት ቤቶች ቅርጫት ኳስ በሁለቱም ፆታ አሸናፊ በመሆን ዞኑ በሶስተኛ ደረጃ ውድድሩን እንዲያጠናቅቅ ያደረጉት ሲሆን የሰገን አከባቢ ህዝቦች ዞን ትምህርት ቤቶች በእግር ኳስ፣የወላይታ ዞን በወንዶች መረብ ኳስ አሸናፊ በመሆን አንዳንድ ዋንጫ ወስደዋል፡፡ የሀዲያ ዞን ትምህርት ቤቶች ከመጀመሪያው እስከ ፍፃሜው ባሳዩት ስፖርታዊ ጨዋነት የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ከየካቲት 10 እስከ 21/ 2005 በተካሄደው ውድድር ክልሉን ወክለው በአዲስ አበባ በሚካሄደው አገር አቀፍ የትምህርት ቤቶች ውድድር የሚሳተፉ ከ400 በላይ ስፖርተኞች ተመርጠዋል፡፡ የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍ ለውድድሩ አሸናፊዎች፣ ለኮከብ ዳኞች፣ ተማሪዎች፣ለውድድሩ መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት፣ ድርጅቶችና ግለሰቦች ዋንጫ፣ ሜዳሊያና ምስክርወረቀት ካበረከቱ በኃላ እንደገለጹት ስፖርት ለአንድ አገር ማህበራዊና ኢኮኖሚ እድገት ከሚኖረው ፋይዳ በተጨማሪ በብሄር ብሄርሰቦች መካከል ያለውን አንድነትና የባህል ትስስር ለማጠናከር የላቀ ሚና አለው፡፡ መንግስት ይኸንን በመገንዘብ ከሁሉም የባለ