Posts

Ethiopia: Yougovia With Vibe From Hawassa

Image
The interior of the new club, Yougovia, is spacious and painted with vibrant colors. It was on January 26, 2013 that Yougovia Club and Lounge came to the Addis Abeba night club scene after much preparation. The first branch located in Hawassa, 273Km from the capital, opened 13 years ago, and is still going strong. The success and the popularity gained there, made it possible to open a second branch in the basement of Sheger Building on Namibia Street near Bole Medhanealem. The owner, Birhan Tedla, named the club "Yougovia" from a story his brother-in-law told him, of how when the Italians left Mehal Meda in Amhara Region, they said yougovia, we leave you even as we love you. Historical accuracy aside, Birhan fell in love with the word and made it the name for his first night club in Hawassa. Birhan has other businesses including Oasis International Hotel, a 40 bedroom three-star hotel, which he established with a capital of 30 million Br along Lake Hawassa, and

ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ (መለስ ዋንጫ) የፊታችን እሁድ ይጀመራል፤ በ9 ሰኣት ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ይጫወታል

Image
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ላለፉት ሁለት ወራት በአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ (መለስ ዋንጫ) የፊታችን እሁድ ይጀመራል። በዚህም መሰረት እሁድ አዲስ አበባ ላይ ፥ የአምናው ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ በ9 ሰአት  እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት በ11 ሰአት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ክልል ላይ በሚደረግ ጨዋታ በይርጋአለም ስቴዲየም ፥ በ9 ሰአት ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚጫወቱ ሲሆን ፥ አርባ ምንጭ ላይ ደግሞ አርባ ምንጭ ሃረር ቢራን በተመሳሳይ ሰአት ያስተናግዳል። መብራት ሃይል ከሙገር ሲሚንቶ ፣ ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ከኢትዮጵያ መድን የሚገናኙባቸው ጨዋታዎች የካቲት 21 የሚደረጉ ይሆናል። http://www.fanabroadcasting.com/index.php?option=com_content&view=article&id=2446:2013-02-19-13-43-22&catid=102:slide

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ሶስተኛ ዓመት አራተኛ ዙር ስድስተኛ መደበኛ ጉባኤ በሃዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነዉ

Image
ሃዋሳ የካቲት 12/2005 በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በዘንድሮ ግማሽ በጀት ዓመት በየዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት የተመዘገበባቸው መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ ። የክልሉ ምክር ቤት ሶስተኛ ዓመት አራተኛ ዙር ስድስተኛ መደበኛ ጉባኤ በሃዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነዉ ። ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የክልሉን የግማሽ በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት ካለፈዉ ዓመት ክንውን በየስራ ዘርፉ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመውሰድና በማስፋት እስትራተጂ በመጠቀም ውጤታማ ተግባራት ተከናወነዋል ። በመንግስትና በህብረተሰቡ የተሟላ ተሳትፎ የኪራይ ሰብሳቢነትን ችግሮች ለመቅረፍ በሚያሰችል መልኩ በገጠርና በከተማ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ለውጥ ማምጣት የተቻለ መሆኑን አስታዉቀዋል ። ባለፉት ስድስት ወራት በግብርና ልማት፣ በመንገድ ግንባታና በቀበሌ ተደራሽ መንገድ ስራዎች የገጠር ቀበሌዎችን ዕርስ በዕርስና ከዋና መንገድ ጋር በማገናኘት 705 ኪሎ ሜትር መንገድ ተገንብቶ መጠናቀቁን አርሶና አርብቶ አደሩ ምርቱን ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆኑን አመልክተዋል ። መንገዶቹ በሚገነቡባቸው አካባቢዎች በማህበር ለተደራጁና በጉልበት ሰራ ለተሰማሩ ከ106 ሺህ በላይ ሰዎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ጠቁመው ከ668 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ለመንገዱ ግንባታ ከ65 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነጻ የጉልበት አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። የትምህርት ጥራት ፍትሀዊነትና ተደራሽነት በማረጋገጥ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ለማስቻል እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በሚሰጡ ስልጠናዎች ጥራትና ተፈላጊነት ዙሪያ የታቀዱ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመዋል። በህዝብ ንቅናቄ የታጀበው

ከሲዳማ እና ቤንች ማጂ ዞኖች 106 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ተመርቶ ብሄራዊ ባንክ ቀረበ

Image
ሃዋሳ የካቲት 12/2005በደቡብ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት በባህላዊ መንገድ የተመረተ 106 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ መቅረቡን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ ገለጸ ፡፡ በቢሮው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ወርቁ ተሰብስቦ ለባንኩ የቀረበው ከቤንች ማጂና ሲዳማ ዞኖች ነዉ ። በባህላዊ መንገድ የተመረተዉ ወርቅ በህጋዊነት ተደራጅተው በሚንቀሳቀሱ 18 የወርቅ አምራቾችና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ለባንኩ መቅረቡን አስረድተዋል ። የዘንድሮዉ የግማሽ በጀት አመት ክንውን ከእቅዱ አኳያ ዝቅተኛ ቢሆንም ከ2001 ሙሉ በጀት አመት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ከሁለት ዕጥፍ በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል ። በየዞኖቹ በባህላዊ መንገድ የሚመረተው ወርቅ በህገ ወጥ መንገድ እንዳይባክን የግብይት ጣቢያዎችን ከማጠናከር ባሻገር የግብይት ስርዓት ህጋዊ መልክ በማስያዝና አቅርቦቱን በቀጣይ ለማሻሻል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ቢሮዉ ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን አቶ መላኩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=5642&K=1

አደናጋሪው የሕግ ቋንቋ ጉዳይ…

በውብሸት ሙላት የሕግ ቋንቋ በብዙ መልኩ የተቀዣበረ ነው፡፡ ቀዥባራነቱን አንዳንዶች እንደ ውበት ይወስዱታል፡፡ ሌሎች ደግሞ የሕግ ባለሙያዎች ብቻ እንደሚያውቁት የአስማት/የመተት ቋንቋ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ ሌላም ሌላም ይሉታል፡፡ ለማንኛውም በእንግሊዝኛ ተናጋሪ አገሮች ዘንድ የግልጽ ቋንቋ ተሟጋቾች እየተበራከቱ በመምጣታቸው የሕግ ማኅበረሰቡ ግልጽ ቋንቋ ይጠቀሙ ዘንድ የሚያበረታቱ፣ እንዲጠቀሙ የሚሞግቱ የቋንቋና የሕግ ባለሙያዎች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ በአገራችን ግን ስለዚህ ጉዳይ ስለመነሳቱ ይህ ጸሐፊ አያውቅም፡፡ በመሆኑም ስለሕግ ቋንቋ አንዳንድ ነገሮችን አንስተን እንወያያለን፡፡ መነሻ ወግ አንድ በዕድሜ ገፋ ካሉ የእግሊዝኛ ቋንቋ መምህርና ደራሲ ጋር እያወጋን ነው፡፡ በሕይወታቸው ሦስት ጊዜ የእንግሊዝኛ አንድ ጊዜ የአማርኛ የፍትሐ ብሔር ሕግ ኮድ (መጽሐፍ) ገዝተዋል፡፡ አራቱንም መጻሕፍት ለሕግ ባለሙያዎች ሰጥተዋቸዋል፡፡ የስጦታቸው ምክንያት በልገስና ስሜት ሳይሆን ከገዟቸው በኋላ ሲያነቧቸው ሊገቧቸው ስላልቻሉ በብስጭት ነው፡፡ በእልህ ገዟቸው በብስጭት ሰጧቸው፡፡ እስካሁን ለምን ያነበቧቸው እደማይገቧቸው ግልጽ አልሆነላቸውም፡፡ አንድ የጓደኛዬ ጓደኛ ከሚንስትር መለስ ባለ ደረጃ ቱባ ባለሥልጣን ነው፡፡ ከቱባ ባለሥልጣን ሚስቱ ጋር በመጣላቱ በፍች ትዳራቸውን ሊያፈርሱ ሆኖ በሚስቲቱ አመልካችነት ጉዳዩ ተጀምሮ የፍችው አቤቱታ መጥሪያ ይደርሰዋል፡፡ በአቤቱታው የመጀመሪያ ገጽ የክሱ መግለጫ በሚለው ክፍል ላይ እንዲህ የሚሉ ዓረፍተ ነገሮች ተቀምጠዋል፡፡ “1. በሕግ ችሎታ የለሽም አልተባልኩም፡፡ 2. ጉዳዩ በይርጋ አልታገደም፤” የሚሉ ዓረፍተ ነገሮች ናቸው፡፡ ይህ ሁለተኛ ዲግሪ ያለው ቱባ ባለሥልጣን ሚስቱ እንፋታ ብላ ባቀረበችው አቤቱታ ላይ ከላይ የ