Posts

አደናጋሪው የሕግ ቋንቋ ጉዳይ…

በውብሸት ሙላት የሕግ ቋንቋ በብዙ መልኩ የተቀዣበረ ነው፡፡ ቀዥባራነቱን አንዳንዶች እንደ ውበት ይወስዱታል፡፡ ሌሎች ደግሞ የሕግ ባለሙያዎች ብቻ እንደሚያውቁት የአስማት/የመተት ቋንቋ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ ሌላም ሌላም ይሉታል፡፡ ለማንኛውም በእንግሊዝኛ ተናጋሪ አገሮች ዘንድ የግልጽ ቋንቋ ተሟጋቾች እየተበራከቱ በመምጣታቸው የሕግ ማኅበረሰቡ ግልጽ ቋንቋ ይጠቀሙ ዘንድ የሚያበረታቱ፣ እንዲጠቀሙ የሚሞግቱ የቋንቋና የሕግ ባለሙያዎች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ በአገራችን ግን ስለዚህ ጉዳይ ስለመነሳቱ ይህ ጸሐፊ አያውቅም፡፡ በመሆኑም ስለሕግ ቋንቋ አንዳንድ ነገሮችን አንስተን እንወያያለን፡፡ መነሻ ወግ አንድ በዕድሜ ገፋ ካሉ የእግሊዝኛ ቋንቋ መምህርና ደራሲ ጋር እያወጋን ነው፡፡ በሕይወታቸው ሦስት ጊዜ የእንግሊዝኛ አንድ ጊዜ የአማርኛ የፍትሐ ብሔር ሕግ ኮድ (መጽሐፍ) ገዝተዋል፡፡ አራቱንም መጻሕፍት ለሕግ ባለሙያዎች ሰጥተዋቸዋል፡፡ የስጦታቸው ምክንያት በልገስና ስሜት ሳይሆን ከገዟቸው በኋላ ሲያነቧቸው ሊገቧቸው ስላልቻሉ በብስጭት ነው፡፡ በእልህ ገዟቸው በብስጭት ሰጧቸው፡፡ እስካሁን ለምን ያነበቧቸው እደማይገቧቸው ግልጽ አልሆነላቸውም፡፡ አንድ የጓደኛዬ ጓደኛ ከሚንስትር መለስ ባለ ደረጃ ቱባ ባለሥልጣን ነው፡፡ ከቱባ ባለሥልጣን ሚስቱ ጋር በመጣላቱ በፍች ትዳራቸውን ሊያፈርሱ ሆኖ በሚስቲቱ አመልካችነት ጉዳዩ ተጀምሮ የፍችው አቤቱታ መጥሪያ ይደርሰዋል፡፡ በአቤቱታው የመጀመሪያ ገጽ የክሱ መግለጫ በሚለው ክፍል ላይ እንዲህ የሚሉ ዓረፍተ ነገሮች ተቀምጠዋል፡፡ “1. በሕግ ችሎታ የለሽም አልተባልኩም፡፡ 2. ጉዳዩ በይርጋ አልታገደም፤” የሚሉ ዓረፍተ ነገሮች ናቸው፡፡ ይህ ሁለተኛ ዲግሪ ያለው ቱባ ባለሥልጣን ሚስቱ እንፋታ ብላ ባቀረበችው አቤቱታ ላይ ከላይ የ

የግብርና ሚኒስቴር የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በድጋሚ ሊሰጥ ነው

ግብርና ሚኒስቴር ለሁለተኛ ጊዜ በአራት ክልሎች ውስጥ ለሚገኙ 50 ሚሊዮን ማሳዎች በካዳስተር ካርታ የተደገፈ የገጠር መሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሊሰጥ ነው፡፡ የካዳስተር ካርታ ሥራውን የሚያካሂዱት የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጀንሲና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ናቸው፡፡ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ጌታሁን፣ የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሡልጣን መሐመድና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄነራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡ ነገር ግን የግብርና ሚኒስቴር ለዚህ ፕሮጀክት የሚያስፈልገውን ፋይናንስ በእጁ ባለማስገባቱ ሥራው እንዳልተጀመረ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ግብርና ሚኒስቴር የሚያስፈልገውን ገንዘብ የዓለም ባንክ እንዲያቀርብለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ የዓለም ባንክ ገንዘቡን በቅርቡ እንደሚለቅ ምንጮችም ገልጸዋል፡፡ ገንዘቡ እንደተለቀቀ ደኅንነት ኤጀንሲ ማሳዎቹን የአየር ፎቶ ያነሳል፡፡ ያነሳውንም ፎቶ ለካርታ ሥራ ኤጀንሲ ያስረክባል፡፡ ካርታ ሥራ ኤጀንሲ የማሳዎቹን ካርታ እንደሚሠራና ለሚኒስቴሩ እንደሚያስረክብ ታውቋል፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት መንግሥት በየክልሉ በባህላዊ የአሠራር ዘዴ በመጀመርያ ደረጃ የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት በማዘጋጀት 90 በመቶ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች ማደሉ ታውቋል፡፡ ነገር ግን ቀደም ሲል የቀረበው ካርታ የተጠናከረ መረጃ የማይሰጥ በመሆኑና በመጀመርያ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ላይ የነበሩበትን ክፍተቶች በማስተካከል እንደ አዲስ መረጃ የሚሰጥ ካርታ መስጠት እንደሚገባ ታምኖበታል፡፡ የገጠር መሬት አስተዳደር ሥርዓቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የካዳስተር የመሬት መረጃ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተኝቷል ተብሏል፡፡ አዲ

ለከተማ ኣስተዳደር ምክር ቤት ለሚካሄደው ምርጫ ሲኣን150 እጩዎችን ኣስመዘጋበ

Image
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ሚያዝያ ወር ለሚካሄደው ምርጫ የሚወዳደሩትን እጩዎች ይፋ አደረገ። ዛሬ ማምሻውን ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባገኘነው ጊዜያዊ መረጃ መሰረት  ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለመወዳደር 11 ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል። በዚህም መሰረት ኢህአዴግ 138 ፣ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ  87፣ የመላው ኢትዮጵያውያን ብሄራዊ ንቅናቄ መኢብን 85 እንዲሁም የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ኢራፓም 14 እጩዎችን አስመዝግበዋል። የመላው ኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መኦህዴፓ 14፣ የኢትዮጵያ የፍትህና የዶሞክረሲ ኃይሎች ግንባር ኢፍዴሃግ 9 ፣ የኢትዮጵያ ሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢሰዴፓ 6፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ ኢዴአን 3፣ የገዳ ስርዓት አራማጅ ፓርቲ ገስአፓ 2 ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓ 1 እጩዎችን ሲያመዘግቡ በድምሩም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 393 እጩዎች ተመዝግበዋል። አዲስ አበባ ላይ ለክፍለ ከተማ ምክር ቤት ኢህአዴግ 3ሺ 480 እጩዎቹን ሲያስመዘግብ ለወረዳ ምክር ቤትም እንዲሁ 34ሺ 794 እጩዎችን ነው ያስመዘገበው። ኦሮሚያ ክልል ላይም ለከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ምርጫ ኢህአዴግ ፥ 2 ሺህ 205 እጩዎችን ሲያስመዘግብ ፤ መኦህዴፓ 5፣ እንዲሁም ገስአፓ 1 እንዲሁም አምስት የግል ተወዳዳሪዎችም እጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል። ደቡብ ከልል ላይ ለከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለሚካሄደው ምርጫ ኢህአዴግ 1ሺህ 160 ፣ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ሲአን 150 ፣ ኢዴፓ፣ ኢፍዲሃግና ኢራፓም በድምሩ 12 እጩዎችን  ፣ የወላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ዎህዴግ 1 እንዲሁም ሁለት እጩዎችም በግ

የእለቱ የሲዳማ ዜና በደቡብ ቲቪ 2/14/2013

Image
የእለቱ የሲዳማ ዜና 2/14/2013 የእለቱ የሲዳማ ዜና በደቡብ ቲቪ

በደቡብ ክልል ስድስተኛው የአርሶ አደሮች ቀን በመጪው ሳምንት መጨረሻ ላይ በሀዋሳ ይከበራል

አዋሳ የካቲት 07/2005 ስድስተኛው የአርሶ አደሮችና ከፊል አርሶ አደሮች በዓል በደቡብ ሕዝቦች መስተዳድር በክልል ደረጃ ከየካቲት 16 ቀን እስከ 18/2005 እንደሚከበር የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ። በበዓሉ ላይ በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ አርሶ አደሮችና ባለድርሻ አካላት ይሸለማሉ። በቢሮው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ተወካይ አቶ ሊሬ አቢዩ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ለስድስተኛ ጊዜ በክልሉ በሚከበረው በዓል ላይ 660 አርሶ አደሮች ከፊል አርሶ አደሮች የልማት ባለሙያዎች በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሸለማሉ። ''የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የመለስን የብልፅግና ራዕይ እናሳካለን'' በሚል መሪቃል በሚከበረው የክልሉ አርሶ አደሮች በዓል ተሸላሚ ከሚሆኑ 660 ባለድርሻ አካላት 390ዎቹ አርሶ አደሮች መሆናቸውን ገልፀዋል። ከተሸላሚ አርሶ አደሮች መካከል 117 ከግብርና ተነስተው እሴት በመፍጠር ወደ ባለሀብትነት ደረጃ በማደግ በሌላ መስክ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙባቸው መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም 82 ሴት አርሶ አደሮችና 54 ወጣት አርሶ አደሮች እንዲሁም የእረፍት ጊዜያቸውን ከአርሶ አደሩ ጋር በማሳለፍ በግብርናው መስክ ለተገኘው ውጤት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ 167 የልማት ባለሙያዎች እንደሚገኙበት አስታውቀዋል። በክልል ደረጃ ተሸላሚ ከሚሆኑት መካከል 171 አርሶ አደሮችና ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚከናወነው የአርሶ አደሮች ቀን ላይ ተሸላሚ እንደሚሆኑ አቶ ሊሬ ጠቁመዋል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=5486&K=1