Posts

በደቡብ ክልል ስድስተኛው የአርሶ አደሮች ቀን በመጪው ሳምንት መጨረሻ ላይ በሀዋሳ ይከበራል

አዋሳ የካቲት 07/2005 ስድስተኛው የአርሶ አደሮችና ከፊል አርሶ አደሮች በዓል በደቡብ ሕዝቦች መስተዳድር በክልል ደረጃ ከየካቲት 16 ቀን እስከ 18/2005 እንደሚከበር የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ። በበዓሉ ላይ በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ አርሶ አደሮችና ባለድርሻ አካላት ይሸለማሉ። በቢሮው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ተወካይ አቶ ሊሬ አቢዩ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ለስድስተኛ ጊዜ በክልሉ በሚከበረው በዓል ላይ 660 አርሶ አደሮች ከፊል አርሶ አደሮች የልማት ባለሙያዎች በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሸለማሉ። ''የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የመለስን የብልፅግና ራዕይ እናሳካለን'' በሚል መሪቃል በሚከበረው የክልሉ አርሶ አደሮች በዓል ተሸላሚ ከሚሆኑ 660 ባለድርሻ አካላት 390ዎቹ አርሶ አደሮች መሆናቸውን ገልፀዋል። ከተሸላሚ አርሶ አደሮች መካከል 117 ከግብርና ተነስተው እሴት በመፍጠር ወደ ባለሀብትነት ደረጃ በማደግ በሌላ መስክ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙባቸው መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም 82 ሴት አርሶ አደሮችና 54 ወጣት አርሶ አደሮች እንዲሁም የእረፍት ጊዜያቸውን ከአርሶ አደሩ ጋር በማሳለፍ በግብርናው መስክ ለተገኘው ውጤት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ 167 የልማት ባለሙያዎች እንደሚገኙበት አስታውቀዋል። በክልል ደረጃ ተሸላሚ ከሚሆኑት መካከል 171 አርሶ አደሮችና ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚከናወነው የአርሶ አደሮች ቀን ላይ ተሸላሚ እንደሚሆኑ አቶ ሊሬ ጠቁመዋል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=5486&K=1

የኢህኣዴግ_ ደኢህዴን ኣባል እና በተወካዮች ምክር ቤት የሲዳማ ህዝብ ተወካይ ብሎም የህዝብ ተመራጭ የነበሩት የተከበሩ ወይዘሮ ከበቡሽ ካዊሶ ገዥውን ፓርቲ በመክዳት በኣሜሪካ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀዋል ተባለ

የኢህኣዴግ_ ደኢህዴን ኣባል ፤ በተወካዮች ምክር ቤት የሲዳማ ህዝብ ተወካይ እና የህዝብ ተመራጭ የነበሩት የተከበሩ ወይዘሮ ከበቡሽ ካዊሶ ገዥውን ፓርቲ በመክዳት በኣሜሪካ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀዋል ተባለ ከሲዳማ ኣርነት ግንባር ድህረገጽ ላይ የተገኘው መረጃ  እንደምያሳየው ፤ የተከበሩት ወይዘሮ  ከበቡሽ ለምን ገዥውን ፓርቲ  እንደከዱ እና በምን መንገድ ወደ ኣሜሪካን ልገቡ እንደቻሉ የታወቀ ነገር የለም። ተጨማሪ ዘጋባ ከታች ያንቡ፦ Member of Ethiopian Parliament Defects to US February 10, 2013-A member of Ethiopia ruling party, Mrs. Kebebush Kawisso, has defected to US and is currently seeking political asylum, according to our sources. She was the representative of Sidama people’s democratic organization (SPDO), an organization that EPRDF created and uses to suppress the democratic aspirations of Sidama people. Sources disclosed that, ongoing atrocities against Sidama people led to her decision to defect in protest. Her defection comes in the midst of ever increasing miseries launched against Sidama people by Tigeans controlled Ethiopian government. It's recalled that Sidamas who have spoken up against injustice have been

Ethiopia’s Upcoming Local Elections Unlikely to be Free and Fair!

Image
Press Release By United Sidama Parties for Freedom and Justice (USPFJ) February 12, 2013 The Ethiopia’s regime is preparing to hold its so called nationwide local and the city of Addis Ababa elections. According to its fake, inadequate and nonfunctional election board that solely serves the interests of the rulers ( http:// www.electionethiopia.org/en/ ), local elections in the city of Addis Ababa and others parts of the country are scheduled for 14-21 April 2013. The regime appears to be pretending that it is lobbying its voters in its attempt to show international Diplomats and Western politicians and donors that it’s implementing its constitution in civil and democratic way. The reality on the ground however indicates that there is no level playing field that would allow various political entities to freely lobby their voters for the stated elections.  The Ethiopian government has failed in various occasions to abide by the vary constitution it has promulgated

የ2005 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮና የካቲት 17 ይጀመራል ፤የያዝነውን አመት ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከነማ በ19 ነጥብ ይመራል

በአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ለሳምንታት ተቋርጦ የቆየው የ2005 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመጪው የካቲት 17 እንደሚጀመር ፌዴሬሽኑ አስታወቀ፡፡ በእለቱ ከሚከናወኑት የ10ኛ ሳምንት ግጥሚያዎች መካከል ኢትዮጵያ ቡና ከደደቢት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ የሚያካሂዷቸው ጨዋታዎች ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡ የያዝነውን አመት ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከነማ በ19 ነጥብ ይመራል፡፡ ደደቢት በ18 ነጥብና በ9 ተጨማሪ ግብ ሁለተኛ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በተመሳሳይ ነጥብና በ6 ግብ ክፍያ ሶስተኛ፣ ኢትዮጵያ ቡና በ16 ነጥብ 4ኛ ሆነው ይከተላሉ፡፡ በዘንድሮዉ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ለፍጻሜ ግማሽ የደረሱት ቡድኖች በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮናና ኮንፌዴሬሽን ካፕ የሚሳተፉት ቅዱስ ጊዮርጊስና ደደቢት የመልስ ጨዋታቸውን የካቲት 23 እና 24 አዲስ አበባ ስታዲየም ካከናወኑ በኋላ ለማካሄድ መታቀዱንም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡ በተመሳሳይ የሴቶች ምድብ ጥሎ ማለፍ በመጪው የካቲት 10/2005 ይካሄዳል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ከአርባምንጭ ፣ ደደቢት ከቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አበባ ላይ ይጫወታሉ፡፡ ሙገር ከአዳማ ፣ ሐረር ቢራ ከመብራት ሃይል ፣ ሐዋሳ ከነማ ከመከላከያ በዕለቱ የሚከናወኑ ግጥሚያዎች ናቸው ፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫ በምድብ አንድ ደደቢት በ18 ነጥብ ፣ኢትዮጵያ መድህን 12 ነጥብ፣ በምድብ ሁለት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ16፣ መከላከያ በ11፣ በምስራቅ ምድብ አዳማ ከነማ በ15፣ ድሬደዋ ከነማ በ12፣ በደቡብ ምድብ ሀዋሳ ከነማ በ9 ነጥብና በ6 ተጨማሪ ግብ ሲዳማ ቡና ፣ አንደኛና ሁለተኛ በመሆን ምድቡን በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የቡና ግብይት ጥያቄ አስነስቷል

በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የቡና ግብይት ጥያቄ አስነስቷል Форум вебмастеров •    ኤክስፖርተሮች የገዙትን ቡና በጥራት ደረጃው ማግኘት አልቻሉም •    ንግድ ሚኒስቴር ችግሩን ደርሼበታለሁ ብሏል  የአገሪቱን የግብይት ሥርዓት ዘመናዊ ለማድረግ ከአምስት ዓመት በፊት ሥራ የጀመረውና ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ዝናን ያተረፈው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት (ኢሲኤክስ) የተዝረከረከና ሕገወጥ አሠራር እየተንሰራፋበት መሆኑን ተገልጋዮች ገለጹ፡፡ መንግሥት በገበያ ማዕከሉ የሚስተዋለውን አሳሳቢ ችግር ደርሼበታለሁ፤ በሕገወጥ ሥራ ተሰማርተው በተገኙ ሠራተኞች ላይም ዕርምጃ እየወሰድኩ ነው ይላል፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ በቡና ኤክስፖርት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የገበያ ማዕከሉ በሚያስተዳድራቸው የቡና መጋዘኖች ውስጥ የቡና ቅሸባ ተንሰራፍቷል፡፡ ይህም ከውጭ አገር ደንበኞች ጋር እያጋጫቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የገበያ ማዕከሉ ከአገር ወስጥ አቅራቢዎች ቡናን በመረከብ የቡናውን ናሙና በመውሰድ የቀረበው ምርት የኤክስፖርት ደረጃን ማሟላት አለማሟሟላቱን ካረጋገጠ በኋላ፣ ላኪዎች እንዲጫረቱበት ያደርጋል በማለት የግብይት ሥርዓቱን የሚናገሩት እነዚሁ ቅሬታ አቅራቢዎች፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በዚህ የግብይት ሥርዓት ውስጥ አሳሳቢ ችግሮች እየተስተዋሉ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ በግብይት ሥርዓቱ መሠረት የኤክስፖርት ደረጃን አሟልቷል የተባለ ቡና ጨረታን ካሸነፉ በኋላ ምርቱን ወደ ውጭ ለመላክ ያሸነፉበትንና የከፈሉበትን ማስረጃ በመያዝ ወደ ገበያ ማዕከሉ መጋዘኖች በሚሄዱበት ወቅት፣ የቡና ምርቱን በደረጃው እንደማያገኙ ከዚህ በተጨማሪም የከፈሉበት የቡና ምርት ከመጠኑ አንሶ እንደሚያገኙት ተናግረዋል፡፡ ይህም ከውጭ ገዥዎች ጋር እያጋ