Posts

የእለቱ የሲዳማ ዞን ዜና በደቡብ ቲቪ 2/6/2013

Image
http://www.youtube.com/watch?v=NfHARRtr_k4

በሲዳማ ዞን የማጅራት ገትር ወረርሽን ተከስቷል

Image
አዲሰ አበባ ፣ ጥር 29 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የተከሰተውን የማጅራት ገትር በሽታ በቁጥጥር ስር ለማዋል የተጠናከረ ጥረት እየተደረገ ነው ። በአስር አመት አንድ ጊዜ የሚከሰተው የማጅራት ገትር (ማኔንጃይትስ) ወረርሽኝ ፥ ሰሞኑን በደቡብ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ተከስቶ እንደነበር ነው መረጃዎች የሚያሳዩት። ከእነዚህም ውስጥ በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ፣ በጋሞ ጎፋ ዞን አርባ ምንጭ ከተማና አላባ አካባቢ ፥ ከ100 በላይ ምልክቶቹ የታየባቸው ሰዎች በላቦራቶሪ ምርመራ በበሽታው መያዛቸውን ማረጋገጥ ተችሏል ነው ያለው የክልሉ ጤና ቢሮ። በሽታው ከመከሰቱ በፊት ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፥ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም የማስተማር ስራ መሰራቱን በጤና ቢሮው የህዝብ ግንኙነትና የጤና ኮሚዩኒኬሽን የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ቀድርላ አህመድ ተናግረዋል። በሽታው ተከስቶባቸዋል ተብሎ የተረጋገጡ ቦታዎች ላይ አስፈላጊው የመከላከል ስራ እየተሰራ እንደሆነ ጠቅሰው ፥ በሽታውን ለመቆጣጠር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው ብለዋል። ወረርሽኙ ወደ ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች እንዳይዛመት  የበሽታው መመርመሪያ ማሽን በክልሉ በስፋት ተሰራጭቶ ስራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት። በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች በስጋት ያልተጣራ መድሃኒት እየወሰዱ በመሆናቸው ፥ በዚህ ዙሪያም አስፈላጊ ጥንቃቄ ህብረተሰቡ እንዲያደርግ ነው የጠየቁት። ማህበረሰቡ ወደ ሌሎች አካባቢዎችም ይዛመታል ከሚል ከስጋት ነጻ ይሆን ዘንድም በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዙ መድሃኒቶች በስፋት እየተሰራጩ እንደሆነም ይናገራሉ። ከቅድመ መከላከል ባለፈም በአርባምንጭ ከተማ ብቻ

አርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት አዳዲስ አገልግሎቶችን እየሠጠ ነው

አርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት የምስጢራዊ ህትመት፣ የማማከር፣ ጥገና፣ የግራፊክ ዲዛይንና ፕሌት ቀረፃ እንዲሁም የህትመት ቴክኖሎጂ ሥልጠና አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ። ድርጅቱ የተመሰረተበትን  82 ኛ ዓመቱንና የሐዋሳ ቅርንጫፍ የተቋቋመበትን ስድስተኛ ዓመት ምስረታ በዓልን እንዲሁም የደንበኞች ቀንን በሐዋሳ ከተማ አክብሯል ። በከተማዋ ሌዊ ሆቴል ከደንበኞች ጋር የፓናል ውይይት ባካሄደበት ወቅት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተካ አባዲ እንደተናገሩት፤ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ብቸኛው የህትመት ቴክኖሎጂ ሥልጠና በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው ። ድርጅቱ በእስካሁኑ ሂደት ወደ  500  ያህል ሠልጣኞችን ያስመረቀ ሲሆን፤ ሁሉም ምሩቃን ወደ ሥራው ዓለም ተቀላቅለዋል። በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ምሩቃን ድርጅቱ የማሽንና የሌሎች መሳሪያዎች ድጋፍ ያደርጋል። እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ ድርጅቱ ከአዳዲስ አገልግሎቶች መካከል የምስጢራዊ ህትመት አገልግሎትን ጀምሯል። በእስካሁንም ሂደት ከሠራቸው ምስጢራዊ ህትመቶች መካከል የደቡብና የሐረሪ ክልልን እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ፈተናን ለአብነት ጠቅሰዋል። ይህንንና ሌሎችንም ምስጢራዊ ህትመቶችን በቀጣይ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አመልክተዋል። ድርጅቱ የግራፊክ፣ የዲዛይንና የፕሌት ቀረፃ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በተለይም በሰዓት እስከ አንድ ሺ ድረስ ፕሌት ማውጣት የሚችል ማሽን መግዛቱን ተናግረዋል። ማተሚያ ድርጅቱ ለተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የማማከርና የጥገና አገልግሎት እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ የበርካታ ዩኒቨርሲቲዎችን ማተሚያ ማሽኖች ለመጠገን የሚያስችሉ የጥገና ስምምነት መፈራረሙን ገልጸዋል። በቅርቡም የጥገና ሥራው እንደሚጀመርም ነው

በቅርቡ ሲዳማ ውስጥ የምካሄደውን የኣካባቢ ምርጫ ለማሸነፍ ብቸኛው ኣማራጭ የህዝቡን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችን መመለስ ብቻ ነው

ከሁለት ወራት በኃላ በኢትዮጵያ ብሎም በሲዳማ የምከሄደው የኣከባቢ ምርጫ ላይ ለመሳተፊ ሃዋሳን ጨምሮ በሲዳማ ዞን ውስጥ ኣራት የምሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ተመዝግበው የምርጫ ምልክት መውሰዳቸውን ከኣገሪቱ ምርጫ ቦርድ ሰምተናል። እነዚህ በሲዳማ እንወዳደራለን ብለው የምርጫ ምልክት የወሰዱት የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ( ሲኣን ) ፤ ደኢህዴን _ ኢህኣዴግ፤ኢዴፓ እና ኢህኣፓ ናቸው። በነገራችን ላይ በምርጫ ቦርድ ኣደራጃጀት ሃዋሳ እና ሲዳማ የምል ክፍፍል የለም። በኣሁኑ ጊዜ ሃዋሳ እና ሲዳማ ተብለው የተከፋፈሉ ኣከባቢዎችን የምወክሉ ሰዎች በማንኛውም መንገድ የሲዳማ ተወላጆች መሆን ኣለባቸው። ምክንያቱ በዚህ ምርጫ ላይ ብቻ ሳይሆን በተለይ ከሶስት ኣመት በኃላ በምካሄደው ብሄራዊ ምርጫ በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የሲዳማን ብሄር የምወክሉ ግለሰቦች ከሁሉም የሲዳማ ኣካባቢዎች መምጣት ስላለባቸው ነው። ለምሳሌ ያህል ከሃዋሳ የምወከሉት ግለሰብ የሲዳማ ተወላጅ ካልሆኑ የሲዳማን ህዝብ በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የምወክሉት ተወካዮች ቁጥር ያሳንሳል በተጎዳኝ በሃዋሳ የምያሸንፈው የሌላ ብሄርሰብ ተወላጅ ለብሄረሰቡ ተጨማር የተወካይ ቁጥር ይጨምርለታል ማለት ነው። ይህ ማለት ቀድሞም ብሆን የሲዳማ ህዝብ ብዛት እና በተወካዮች ምክር ቤት ያለው ውክልና ተመጣጣኝ ኣይደለም የምል ኣመለካከት ያጠናክራል። ወደ ጉዳያችን ስንመለስ፤ በዚህ ጽሁፍ በኣራቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ትኩረት ከመሰጠት ይልቅ በሁለቱ ላይ ማለትም በሲኣን እና በደኢህዴን ላይ ትኩረት ለመሰጠት ፈልጋለሁ። እስቲ እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይዘው ነው የቀረቡ ? ለሲዳማ ህዝብ የምጠቅም ምን ይዘዋል ? በምሉት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ እንጫዎት። በኣጠቃላይ በኣገሪቱ ደረጃ ሲታይ ‹‹በግንባ

ያልተመለሱ አንገብጋቢ የምርጫ ጥያቄዎች

Image
ምርጫ መጥቶ በሄደ ቁጥር ላለፉት 22 ዓመታት በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ‹‹በግንባታ ሒደት ላይ ነው›› የሚባለው የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ከዜጎቹ፣ ከምሁራን፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ፍላጎት ካላቸው ሦስተኛ ወገን የውጭ አገር ተቋማትና አገሮች እንዲሁም ዜጎች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሌሎች አካላትና ግለሰቦች የሚነሱትን ጥያቄዎች በሒደት የመመለስ ፍላጎት ያለው አይመስልም፡፡ ለማቀራረብ እንኳን የሚከብደው ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ኢሕአዴግ የሚከተሉት ርዕዮተ ዓለም ላይ የሚቀርበው ጥያቄና የሚሰጠው ምላሽ አንዱ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ርዕሰ ጉዳይ ኢሕአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቀራርበው ለመሥራት እንዳይችሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ሌላኛው ጥያቄ በኢሕአዴግና በመንግሥት መካከል ያለውን ግልጽ ያልሆነ ግንኙነት ወይም መቀላቀል ይመለከታል፡፡ ኢሕአዴግ የፓርቲውንና የመንግሥትን ሚና በመቀላቀልና ፓርቲው ያለአግባብ የመንግሥትን ሀብት እንዲጠቀም እንዳደረገው በተደጋጋሚ ቅሬታ እንዲቀርብበት በር ከፍቷል፡፡ የምርጫ ጉዳይ አስተዳዳሪ ተቋማትና በዲሞክራሲ ግንባታ ሒደቱ ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ተቋማት ላይ የሚነሳው የነፃነትና የገለልተኝነት ጥያቄ ሌላው ጉዳይ ነው፡፡ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድና የመንግሥት የሚድያ ተቋማት አሁንም የዛሬ 18 ዓመት ይባሉ እንደነበረው ኢሕአዴግን ብቻ በማገልገል፣ በሕግ ሁሉንም ተወዳዳሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩልነት እንዲያገለግሉ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እየተወጡ አይደለም ተብለው ይተቻሉ፡፡ ኢሕአዴግ በየትኛውም መስፈርት ጠንካራ ፓርቲ ነኝ ይላል፡፡ በአንፃሩ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጠናክረው በመተባበር በመሥራት ለኢሕአዴግ ፖሊሲዎች አማራጮች ከማቅረብና ደጋፊና የድጋፍ መሠረታቸውን ከማደላደል ይልቅ፣ እ