ያልተመለሱ አንገብጋቢ የምርጫ ጥያቄዎች
ምርጫ መጥቶ በሄደ ቁጥር ላለፉት 22 ዓመታት በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ‹‹በግንባታ ሒደት ላይ ነው›› የሚባለው የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ከዜጎቹ፣ ከምሁራን፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ፍላጎት ካላቸው ሦስተኛ ወገን የውጭ አገር ተቋማትና አገሮች እንዲሁም ዜጎች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሌሎች አካላትና ግለሰቦች የሚነሱትን ጥያቄዎች በሒደት የመመለስ ፍላጎት ያለው አይመስልም፡፡ ለማቀራረብ እንኳን የሚከብደው ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ኢሕአዴግ የሚከተሉት ርዕዮተ ዓለም ላይ የሚቀርበው ጥያቄና የሚሰጠው ምላሽ አንዱ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ርዕሰ ጉዳይ ኢሕአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቀራርበው ለመሥራት እንዳይችሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ሌላኛው ጥያቄ በኢሕአዴግና በመንግሥት መካከል ያለውን ግልጽ ያልሆነ ግንኙነት ወይም መቀላቀል ይመለከታል፡፡ ኢሕአዴግ የፓርቲውንና የመንግሥትን ሚና በመቀላቀልና ፓርቲው ያለአግባብ የመንግሥትን ሀብት እንዲጠቀም እንዳደረገው በተደጋጋሚ ቅሬታ እንዲቀርብበት በር ከፍቷል፡፡ የምርጫ ጉዳይ አስተዳዳሪ ተቋማትና በዲሞክራሲ ግንባታ ሒደቱ ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ተቋማት ላይ የሚነሳው የነፃነትና የገለልተኝነት ጥያቄ ሌላው ጉዳይ ነው፡፡ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድና የመንግሥት የሚድያ ተቋማት አሁንም የዛሬ 18 ዓመት ይባሉ እንደነበረው ኢሕአዴግን ብቻ በማገልገል፣ በሕግ ሁሉንም ተወዳዳሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩልነት እንዲያገለግሉ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እየተወጡ አይደለም ተብለው ይተቻሉ፡፡ ኢሕአዴግ በየትኛውም መስፈርት ጠንካራ ፓርቲ ነኝ ይላል፡፡ በአንፃሩ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጠናክረው በመተባበር በመሥራት ለኢሕአዴግ ፖሊሲዎች አማራጮች ከማቅረብና ደጋፊና የድጋፍ መሠረታቸውን ከማደላደል ይልቅ፣ እ