Posts

በሃዋሳ ከተማ በመገንባት ላይ ያለው የህጻናትና የአረጋዊያን ማዕከል ግንባታ ከ70 በመቶ በላይ ተጠናቀቀ

Image
ሃዋሳ ጥር 24/2005 በሃዋሳ ከተማ ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተሰራ ያለው የህጻናትና የአረጋዊያን ማዕከል ግንባታ ከ70 በመቶ በላይ መጠናቀቁ ተገለጠ ። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሜሪ ጆይ ልማት ማህበር ጋር በመሆን በተለያዩ ማህበረሰብ አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ተባብረው ለማስራት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድም መፈራረማቸው ተገልፀዋል፡፡፡፡ በክልሉ መንግስት፣ በህብረተሰብ ተሳትፎና በሌሎች የልማት አጋሮች ድጋፍ ከሁለት ዓመት በፊት የተጀመረው የህጻናትና የአረጋዉያን ማእከል ግንባታ ዉስጥ እስካሁን ከሰባ በመቶ በላይ ተጠናቋል ። የሃዋሳ ከተማ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያና የበጎ ፈቃደኞች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ዘለቀ ከበደ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ከሃዋሳ ከተማ አስተዳደር በነፃ በተሰጠው ከ6ሺህ 400 ካሬ ሜትር በላይ ያለዉ ማእከል 22 የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች አሉት ። ማዕከሉ በዋናነት ቤተ መፃህፍት፣ የምክር አገልግሎት መስጫ /ካውንስልንግ/ የህክምና ክፍል፣ የመዝናኛ ፣ ዎርክሾፕና ሴራጅም እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት መስጫዎች አካቶ የያዘ መሆኑን አስረድተዋል ማእከሉ ባለፉት ስድስት ዓመታት ከሜሪ ጆይ የልማት ማህበር ጋር በመተባበር በተለይም ሴት አረጋዊያንን በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎች በማሳተፍ ከኢኮኖሚ ጥገኝነት እንዲላቀቁ ባከናወናቸዉ ስራዎች አበረታች ውጤት መመዝገቡ ተገልጧል ። የሜሪ ጆይ ልማት ማህበር መስራችና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘብይደር ዘውዴ በበኩላቸው ማህበሩ በአዲስ አበባ እና በደቡብ ክልል 12 ከተሞች ለችግር የተጋለጡ ከ42ሺህ በላይ ህፃናትና 800 አረጋዉያን በቋሚነት የአልባሳት፣ የጤና፣የትምህርት፣የስነልቦና፣ የመጠለያ፣ የምግብና ሌሎች ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛ

በደቡብ ክልል ከአምስት ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብ በመራጨነት ተመዘገበ

ሃዋሳ ጥር 24/2005 በመጪው ሚያዝያ በሚካሄደው የአከባቢና ከተማ አስተዳደር ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ከአምስት ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብ በመራጭነት ተመዝግቦ ካርድ መውሰዱን በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ሕዝቦች ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገለጸ። በደቡብ ክልል በመራጭነት ተመዝግቦ ካርድ ከወሰደው ህዝብ መካከል ከሁለት ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚበልጡት ሴቶች ናቸው፡፡ ኃላፊው አቶ አብርሃም ጌዴቦ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በሀገር ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ በሚካሄደው የአከባቢና ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ከታህሳስ 21/2005 እስከ ጥር 21/2005 ድረስ ከአምስት ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብ ተመዝግቧል መራጮቹ ምዝገባውን ያደረጉት በክልሉ 14 ዞኖች 4 ልዩ ወረዳና በ22 የከተማ አስተዳደር በተቋቋሙ 8 ሺህ 130 ምርጫ ጣቢያዎች መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ከ40 ሺህ ስድስት መቶ የሚበልጡ ምርጫ አስፈፃሚዎች እየሰሩ መሆኑን አስታውቀው በተመሳሳይ ቁጥር የህዝብ ታዛቢዎች ተመርጠው እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የአከባቢ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አስፈፃሚዎች፣ የሙያ ማህበራት፣ ህብረተሰቡና ሌሎች የባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ምርጫ አስፈፃሚዎች በበኩላቸው ጥር 24 እና 25 በሚካሄደው ልዩ ምዝገባ ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ያልተመዘገቡ መራጮች ተመዝግበው ካርድ በመውሰድ ህገ መንግስታዊ መብታቸውን መጠቀም እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=5093&K=1

ሲዳማ ብሔረሰብ

Image
የሲዳማ ብሔረሰብ በደቡብ ክልል ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ነው። ሲዳማ የሚለው ቃል ለሕዝቡና ለመሬቱ የተሰጠ ስያሜ ሲሆን  «  ሲዳንቾ »  የሚለው ቃል ደግሞ ለሁለቱም ፆታዎች ሲዳማነታቸውን የሚገልጽ ነው፡፡ ብሔረሰቡ በዋናነት ከሚኖርበት አካባቢ ውጪ በኦሮሚያ ክልል በባሌ፣ በጉጂ፣ በምዕራብ አርሲ ዞኖች እና በክልሉ በወላይታና በጌዴኦ ዞኖች ውስጥ ይኖራል። የብሔረሰቡ ዋና የኢኮኖሚ መሠረት እርሻና ከብት እርባታ ሲሆን፤ አነስተኛ የዕደ ጥበብ እና የንግድ እንቅስቃሴዎች በተወሰኑ የማኅበረሰቡ ክፍሎች ይከናወናሉ። በብሔረሰቡ እንሰት፣ ቡና፣ በርበሬ፣ ጐመን፣ ሽንኩርት፣ በቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍ፣ አጃ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ቦሎቄ፣ አቦካዶ፣ አናናስ፣ ማንጐ፣ ሙዝ፣ ፓፓያ፣ አብሽ፣ ኮረሪማ፣ በሶብላ፣ ድንች፣ ስኳር ድንች፣ ቦይና፣ ሸንኮራ አገዳና ጫትን በዋናነት ያመርታል። የብሔረሰቡ ቋንቋ  « ሲዳምኛ »  ሲሆን ከምሥራቅ ኩሻዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ ይመደባል። ከካምባታ፣ ከጠምባሮ፣ ከኦሮሞ፣ ከሀላባ ከቀቤና እና ከጌዴኦ ቋንቋዎች ጋር ይቀራረባል። ብሔረሰቡ ከአፍ መፍቻ ቋንቋው በተጨማሪ አማርኛ፣ ኦሮምኛ እና ወላይትኛን ኩታ ገጠም በሆኑ አካባቢዎች ይጠቀማል። የሲዳማ ብሔረሰብ የራሱ የሆነ ባህላዊ አስተዳደርና የፍትህ ሥርዓቶች ያሉት ሲሆን፤ አጥፊዎች የሚዳኙበት  « ሴራ »  የተባለ ሕግ አላቸው። የባህላዊ አስተዳደሩ የበላይ አካል  « ወማ » ( ንጉሥ ) ነው። ሥልጣኑም በዙር የሚተላለፍ በመሆኑ እያንዳንዱ ጐሣ የራሱ ወማ አለው። በብሔረሰቡ በርካታ የጋብቻ ሥርዓቶች ያሉት ሲሆን  « ሁጫቶ »  በቤተሰብ ፈቃድ የተመሠረተ፣  « አዱልሻ »  ማስኮብለል፣  « ዲራ »  ጠለፋ፣  « ራጌ »  የውርስ ጋብቻ እና  « አዳዋና »  ሴቆ -  ቱጋ ሴት ልጅ ዕድ

The current regime and its policies in Sidama While noting some positive changes initiated by the current regime, ... The following are details of what has occurred in Sidama since the replacement of an overly arrogant central rule by a ...

Image
The current regime and its policies in  Sidama  While noting some positive changes initiated by the current regime,  ...  The following are details of what has occurred in Sidama  since the replacement of an overly arrogant central rule by a  ... Read more:  http://books.google.com.gt/books?id=sbddoOdnkyAC&pg=PA174&dq=sidama&hl=en&sa=X&ei=RjcJUZa8B4iu8ASjnYGwCw&ved=0CEcQ6AEwBg#v=onepage&q=sidama&f=false

ሃዋሳን ጨምሮ በክልሉ ከተሞች ከ130 የሚበልጡ የሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራትና 32 ዩኒየኖች ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ገበያን ማረጋጋት ስራውን በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦን ማበረከታቸውን አስታውቀዋል፡፡

Image
በደቡብ ክልል ከ500 ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ስኳርና ስንዴ ተሰራጨ አዋሳ ጥር 22/2005 በደቡብ ክልል በተጠናቀቀው ግማሽ የጀት ዓመት ከ500 ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ስኳርና ስንዴ በማሰራጨት ገበያውን በማረጋጋት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የክልሉ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡ የቢሮ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ የኔወርቅ ቁምላቸው ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በክልሉ ያለውን ህብረተሰብ ከሚጎዱ የንግድ አሰራሮች በመከላከል ገበያን የማረጋጋቱ ስራ ውጤታማ ሆኗል፡፡ የክልሉ መንግስት መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ስርጭት የሚመራበትን አሰራር ቀይሶ በሁሉም አከባቢ የስራ መዋቅሮችን በመዘርጋት ባለፉት ስድስት ወር ከ508ሺህ 054 ኩንታል በላይ ስኳርና ስንዴ በማሰራጨት ገበያን የማረጋጋት ስራ ማከናወኑን አስታውቀዋል፡፡ ስርጭቱ ፍትሃዊና ተደራሽ በሆነ መንገድ የተከሄደው በየአከባቢው የሚገኙ የጅንአድ ቅርንጫፍ ማዕከላት፣ ከ14 ዞኖችና ከ22 የከተማ አስተዳደር በተመረጡ የጅምላ ንግድ ፈቃድ ባላቸው ነጋዴዎችና በተደራጁ የህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ነው ብለዋል፡፡ በዘይት አቅርቦት በኩል የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ በስምንት የጅንአድ ማዕከላትና በየከተሞች በተቋቋሙ ዩኒየኖች አማካኝነት ከ14 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለተጠቃሚዎች መከፋፈሉን ተናግረዋል፡፡ በተለይ ሃዋሳን ጨምሮ በክልሉ ከተሞች ከ130 የሚበልጡ የሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራትና 32 ዩኒየኖች ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ገበያን ማረጋጋት ስራውን በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦን ማበረከታቸውን አስታውቀዋል፡፡ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትና ገበያን ለማረጋጋት የሚሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑና ስርጭቱን ፍትሃዊ፣ ግልፅና ተደራሽ ለማድ