Posts

Ethiopia: Who Is More Ethiopian?

COLUMN In every way, the political opposition parties of the 2005 elections were irresponsible hooligans who did not even know their own goals. Given their smear campaign, I have always wondered how they could have undertaken the job of governance had they succeeded in their quest for power. They were dividing the nation even before gaining votes. They were contradictorily promising tax cuts, whilst still planning to increase public spending. They lacked the minimum internal stability necessary for smooth administrative functioning. Amazingly, they also invited the international community to interfere in the internal affairs of the nation they were seeking to administer, with little concern for its sovereignty. I am always surprised to hear people lamenting about the 2005 elections, as if it was the turning point for Ethiopian democracy, whereas, rather, it was the point where our aspirations for democracy were crushed. By and large, Ethiopian minorities were deeply concer

ደኢህዴን በሲዳማ ዞንና በከተሞች የሚወዳደሩ ከ115ሺህ በላይ እጩዎችን ስያስመዘግብ ሲኣን ግን እስከኣሁን እጩ ኣላስመዘገበም ተባለ

Image
ሀዋሳ ጥር 20/2005 ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በሲዳማ ዞንና በሌሎች ከተሞች በመጪው ሚያዝያ ለሚካሄደዉ የአካባቢ ምርጫ ደኢህዴን ከ115 ሺህ በላይ እጩዎችን ማስመዝገቡን የዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። በዞኑና በከተሞቹ ለሚካሄደዉ ምርጫ ከ1ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውም ተገልጧል ። የጽህፈት ቤቱ አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ዱካሞ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ደኢህዴን ያስመዘገባቸው 115 ሺህ 368 ዕጩዎች ለዞን ፣ለወረዳ ፣ለከተማና ለቀበሌ ምክር ቤቶች ድርጅቱን ወክለው የሚወዳደሩ ናቸው። ደኢህዴን ለሲዳማ ዞን ፣ለሀዋሳ ፣ለይርጋለምና ለአለታ ወንዶ ከተሞች አስተዳደሮችና ለ21 ወረዳዎች ካስመዘገባቸው ዕጩዎች ውስጥ 105 ለዞን ምክር ቤት፣ 277 ለከተማ አስተዳደር ምክር ቤት፣ 1ሺ524 ለወረዳና ፣113 ሺህ 462 ለቀበሌ ምክር ቤት የሚወዳደሩ መሆኑን ተናግረዋል። ለምርጫው በዞኑና በከተማ አስተዳደሮች ፣በወረዳዎችና በቀበሌ ለመወዳደር ካስመዘገባቸው ዕጩዎች ውስጥ 53 ሺህ 289 ሴቶች ሲሆኑ ከነዚህ ዕጩዎች 38 ለዞን ምክር ቤት ፣110 ለከተማ ምክር ቤት፣ 484 ለወረዳ የሚወዳደሩ ሲሆን ቀሪዎቹ ለቀበሌ ምክር ምክር ቤት እንደሚወዳደሩ አስረድተዋል። በዞኑ ለመወዳደር ተመዝግበዉ የመለያ ምልክት ከወሰዱ አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ደኢህዴን፣ ፣ሲአን፣ኢዴአፓና ኢራፓ ውስጥ እስካሁን ዕጩዎቹን ያስመዘገበው ደኢህዴን ብቻ መሆኑን አስተባበሪዉ አመልከተዉ የዕጩዎች ምዝገባ የሚጠናቀቀው በነገዉ እለት በመሆኑ ፓርቲዎቹ ዕጩዎቻቸውን እንዲያስመዘግቡ አሳስበዋል። በተጨማሪም በዞኑ በተቋቋሙ 1648 የምርጫ ጣቢያዎች እስካለፈው አርብ ድረስ 1 ሚሊዮን 33 ሺህ መራጮች መመዝገባቸውንና ከነዚህ ውስጥ 472 ሺህ 764 ሴቶች መሆናቸውን አቶ ብርሃ

በሲዳማ ዞንና ሃዋሳ ከተማ ከ955 ሺህ በላይ መራጮች ተመዘገቡ

Image
ሃዋሳ ጥር 20/2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞንና በሃዋሳ ከተማ በመጪው ሚያዝያ ለሚደረገው የአካባቢ ምርጫ ከ955 ሺህ በላይ መራጮች ተመዘገቡ፡፡ የሲዳማ ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ዱካሞ እንደገለጹት በዞኑ በሚገኙ 21 ወረዳዎችና በሃዋሳና ይርጋለም የከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ 1 ሺህ 648 የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ ያለምንም ችግር በመከናወን ላይ ነው። እስከ ጥር 21 ድረስ በሚቆየው የመራጮችና የዕጩዎች ምዝገባ ከ1 ሚሊዮን 282 ሺህ በላይ መራጮች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። ከታህሳስ 22 ጀምሮ በመከናወን ላይ ባለው የመራጮችና የዕጩዎች ምዝገባ ለመራጭነት ከተመዘገቡት መካከል 446 ሺህ 699 ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል። በመጪው ሚያዝያ ወር በሚደረገው የአካባቢና የማሟያ ምርጫ ላይ በመራጭነት ለመሳተፍ የመራጮች ምዝገባ በመጪው ማክሰኞ ከመጠናቀቁ በፊት ህብረተሰቡ በመመዝገብ የመራጭነት ማረጋገጫ ካርዱን መያዝ እንዳለበት አስተባባሪው አሳስበዋል። በሃዋሳ ከተማ ሚሊኒየም ቀበሌና ዋጋኔ ዋጮ ቀበሌ ለመራጭነት በመመዝገብ ላይ ከሚገኙት መካከል ወይዘሮ በላይነሽ ደምሴና አቶ ታከለ ተሾመ በሰጡት አስተያየት ያገኙትን ዲሞክራሲያዊ መብት በመጠቀም የተሻለ ለውጥ በማምጣት ይሰራልናል ብለው ያመኑትን ዕጩ ለመምረጥ የመራጭነት ማረጋገጫ ካርድ ወስደዋል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=4931&K=1

በሃዋሳ ከተማ ከ7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነባው የነዳጅ ማደያ አገልግሎት ጀመረ፡፡

Image
ሃዋሳ ጥር 20/2005 የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማሳካት የኢንዱስትሪውን ልማት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት የልማታዊ ባላሃብቶች ተሳትፎ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለዉ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ገባኤ አስታወቁ ፡፡ በሃዋሳ ከተማ ከሰባት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነባው ዳሎል ኦይል የነዳጅ ማደያ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ ምክትል አፌ-ጉባኤ አቶ ማሞ ጎዴቦ ማደያውን መርቀው ስከፍቱ እንደተናገሩት ባለፉት ሁለት አስርት አመታት በግብርና፣ በከተማ ልማት፣ በኢንዱስትሪ፣ በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በሌሎችመስኮች በክልሉ አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ በየደረጃው ለተመዘገቡ ለውጦች መንግስታዊ አደረጃጀቶች፣ መላው ህብረተሰብ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የግል ባለሃብቶች በጋራ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል ። በተለይ ይላሉ አቶ ማሞ ሁሉም ዜጋ በሀገሪቱ ውስጥ በሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ መንግስት ያስቀመጣቸው ውጤታማ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ለተመዘገበው ስኬት ቁልፍ ድርሻ አበርክተዋል፡፡ በዚህም በክልሉ ከ1986 ወዲህ ከ68 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ከአምስት ሺህ የሚበልጡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ መሰማራታቸውንና ከአንድ ሚሊዮን ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠራቸው ተናግረዋል፡፡ የሃዋሳ ከተማ ባለፉት ጥቅት አመታት ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ካሉ የሀገራችን ከተሞች አንዷ መሆኗን የጠቆሙት አቶ ማሞ የግል ባለሃብቶች ከከተማው ዕድገት ጋር የሚጣጣም የልማት አቅርቦት እንዲኖር ከመንግስት ጎን በመሆን እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ። የዳሎል ኦይል አክሲዮን ማህበር

የሲዳማ ባህል እና ኣዲስ ኣመትን የተመለከተ በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የተዘጋጀ ዶክሜንትር

Image
Sidama's Culture and New Year