Posts

‹‹የምርጫ ምልክቴ የሆነውን አውራ ዶሮ ከምርጫ ቦርድ የወሰድኩት ሐዋሳን ጨምሮ የሲዳማ ሕዝብ ጥያቄው የክልል ጥያቄ ስለሆነ ሕዝቡ በዚህ ምርጫ ተሳትፎ በምርጫ ካርድ መብቱን ሊያስከብር ስለሚፈልግ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ወደ ምርጫ እንድንገባ ወስኗል›› የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ፓርቲ ጸሃፊ አቶ ለገሰ ላቃሞ

Image
በመጪው ሚያዚያ ወር በሚካሄደው የአዲስ አበባ አስተዳደርና የአካባቢ ምርጫ የአፈጻጸም የጊዜ ሰሌዳ አስቀድሞ በምርጫው ፍትሃዊነት እና በሌሎች 18 አጀንዳዎች ላይ ሊወያዩ እንደሚገባ በማመን ፒትሽን ተፈራርመው ጥያቄያቸውን ለምርጫ ቦርድ ካስገቡ 33 ተቃዋሚ ፓርቲዎች አምስቱ የምርጫ ምልክታቸውን የወሰዱ ሲሆን 28ቱ ፓርቲዎች በቅርቡ ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚጠሩ አስታወቁ፡፡ የመድረክ ሥራ አስፈፃሚ አባልና የፓርቲዎች ሰብሳቢ አቶ አሥራት ጣሴ እንደገለፁት፤ ፓርቲዎቹ ጥር 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ከሦስት በላይ የአዳራሽና የመስክ ሕዝባዊ ስብሰባ ለመጥራት ያቀዱ ሲሆን ለአዲስ አበባ መስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ፈቃድ ክፍል ደብዳቤ ለማስገባት በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳውን በመቃወም ፒትሽን ከፈረሙት 33 ፓርቲዎች ውስጥ አምስቱ የምርጫ ምልክታቸውን እንደወሰዱ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡  ፡ የኢትዮጵያ ፍትህና ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ግምባር(ኢፍዲሃግ)፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሕብረት(ኢዲህ)፣ የባህር ወርቅ መስመስ ሕዝቦች ዲሞክራሲ ድርጅት(ባመህዴድ)፣ ዱቤና ደጀኔ ብሄረሰብ ዲሞክራሲያዊ (ዱብዴፓ) የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ፓርቲ(ሲአንፓ) የምርጫ ምልክት መውሰዳቸውን ቦርዱ አስታውቋል፡፡ “በሲዳማ ዞን ሕዝብ ጥያቄ በምርጫ ለመሳተፍ ተገደናል” ያለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ፓርቲ በበኩሉ የምርጫ ምልክት ወስዶ ለምርጫው ዝግጅት እያደረገ ቢሆንም በትግል ከ28ቱ ፓርቲዎች ጎን እንደሚሰለፍ ገልጿል፡፡ የ28ቱ ፓርቲዎች ሰብሳቢ አቶ አስራት ጣሴ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ “የምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ያቀረቡትን ጥያቄዎች ሳይመልስ ዐዋጁን ጥሶ ሕጋዊም፣ ሞራላዊም፣ ዲሞክራሲያዊ ባልሆነ መንገድ ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓት መጠንከር ወሳኝነት ያላቸ

በሃዋሳ ከተማ እምብርት ላይ የቆመውን እና የሲዳማ ህዝብ ባህል የምተርከውን ሀውልት ስም በትክክል መጻፍ ያልቻለው ኣዲሱ የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ድህረገጽ

Image
ሙሉ ድረገጹን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ: http://hawassacity.info/

Hawassa University(HwU) awarded honorary Doctoral Degree to Mr. Yohei Sasakawa

Image
Following Hawassa University’s Senate decision to bestow an Honorary Doctoral Degree to Mr.Yohei Sasakawa on July 14, 2012, Ethiopian ambassador to Japan His Excellency Mr. Markos Tekle awarded the Doctor of Agriculture Development Honoris Causa and Medal to Mr.Yohei Sasakawa, Chair of the Nippon Foundation,on an official ceremony held at the Ethiopian Embassy in Tokyo On December 12, 2012. Mr. Sasakawa was not able to travel to Ethiopia for health reasons. On the awarding ceremony held at Ethiopian Embassy in  Tokyo Japan, His Excellency Markos Tekle said Sasakawa Global has played a significant role in his country in minimizing the rate of famine, in enabling many people to be self- sufficient in food, in protecting natural resources and generally in the development of the country.  The ambassador added that the Sasakwa Program being financed by Nippon Foundation has brought many Sub- Sahara African countries out of poverty. According to Mr. Markos, it is realizing these su

ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል ከሁለት ሚሊዮን 400 ሺህ የሚበልጥ ህዝብ ተመዝግቦ ካርድ መውሰዱ ተገለጸ

አዋሳ ጥር 08/2005 (ዋኢማ)  - በደቡብ ክልል በመጪው ሚያዝያ በሚካሄደው የአከባቢ ምርጫ እስካሁን ከሁለት ሚሊዮን 400 ሺህ የሚበልጥ ህዝብ ተመዝግቦ ካርድ መውሰዱን በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገለጸ።  ኃላፊው አቶ አብርሃም ገዴቦ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት እስከትናንት ከሁለት ሚሊዮን 400 ሺህ በላይ መራጮች ተመዝግበው ካርድ ወስደዋል፡፡  ካርድ ከወሰዱት መካከል አንድ ሚሊዮን 168ሺህ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ መራጮቹ ምዝገባ ያደረጉት በክልሉ 14 ዞኖች፣ 4 ልዩ ወረዳዎችና በ22 የከተማ አስተዳደር በተቋቋመው 8ሺህ 130 ምርጫ ጣቢያዎች መሆኑን ገልፀው በክልሉ ሰባት ሚሊዮን መራጮች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል፡፡  በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎቹ 40 ሺህ ስድስት መቶ ምርጫ አስፈፃሚዎች የምርጫውን ስራ ለማስፈፀም እየሰሩ መሆኑን ጠቁመው በተመሳሳይ ቁጥርም የህዝብ ታዛብዎች ተመርጠው እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡  የአከባቢ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አስፈፃሚዎች፣ የሙያ ማህበራት፣ ህብረተሰቡና ሌሎች የባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡  የምርጫ አስፈፃሚዎች በበኩላቸው ህዝቡ ዛሬ ነገ ሳይል በመራጭነት ተመዝግቦ በህገ መንግስቱ የተረጋገጠለትን መብት መጠቀም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡  http://www.waltainfo.com/index.php?option=com_content&view=article&id=7034:----400-----&catid=58:2011-08-29-12-55-21&Itemid=383

በ2005 ዓ.ም ለሚካሄደው የአካባቢና የከተማ ምርጫ 23 ሚሊዮን የሚጠጉ መራጮች ተመዝግበዋል

Image
አዲስ አበባ ጥር 14/2005 በመጪው ሚያዚያ ወር 2005 ዓ.ም ለሚካሄደው የአካባቢና የከተማ አስተዳደሮች ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እንደቀጠለ ነው። በዘጠኙ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ከታህሳስ 22 እስከ ጥር 13 /2005 ዓ.ም ድረስ በተካሄደው የመራጮች ምዝገባ 23 ሚሊዮን የሚጠጉ መራጮች መመዝገባቸውን የምርጫ ቦርድ አስታወቋል፡፡ የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ይስማ ጅሩ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከተመዘገቡት መራጮች መካከል 10 ሚሊዮን 794 ሺህ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡ ቦርዱ በአጠቃላይ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለመምረጥ ይመዘገባል ተብሎ ከሚጠበቀው ከ28 ሚሊዮን በላይ መራጭ መካከል 83 በመቶ የሚሆኑት የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውንም ጠቁመዋል፡፡ በተለያየ ምክንያት የመራጭነት ካርድ ያልወሰዱ መራጮችም በቀሪዎቹ 10 ቀናት የመራጭነት ካርዱን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=4804&K=1