Posts

ከሻሸመኔ ጅምላ ንግድ አከፋፋይ ድርጅት /ጅንአድ/ መጋዘን ወጥቶ በህገ ወጥ መንገድ በሀዋሣ ከተማ ሲራገፍ የነበረ ዘይት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የክልሉ ንግድ ኢንድስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከሻሸመኔ ጅምላ ንግድ አከፋፋይ ድርጅት /ጅንአድ/ መጋዘን ወጥቶ በህገ ወጥ መንገድ በሀዋሣ ከተማ ሲራገፍ የነበረ ዘይት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የክልሉ ንግድ ኢንድስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በቢሮው የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉሌሽን ዋና የሥራ ሂደት  ጊዜያዊ አስተባባሪ ወይዘሮ መስከረም ባህሩ እንደተናገሩት ባለሦስት ሊትር 91 ካርቶንና ባለ አምስት ሊትር 234 ካርቶን ዘይት በአይሱዙ መኪና ተጭኖ በአንድ ነጋዴ መጋዘን ሲራገፍ ከክልሉ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በደረሰ ጥቆማ መሠረት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በገንዘብ ሲተመን ከ138 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ሲሆን   ወደ ኦሮሚያ ክልል ጎዴ ዞን የሚሄድ እንደነበር ነው የገለፁት፡፡ በተጠርጣሪው መጋዘን ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ባለ 2ዐ ሊትር 336 ጀሪካን ዘይትም በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነም አስተባባሪዋ ተናግረዋል፡፡ ባልደረባችን አደገ አየለ እንደዘገበው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/05TirTextN305.html

በሀዋሳ ከተማ የተጀመረው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ባለስድስት ፎቅ ህንጻ ግንባታ በመገባደድ ላይ ነው

Image
  አዋሳ ጥር /2005 የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በደቡብ ክልል ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን የብድርና የቁጠባ አገልገሎት ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ ። ተቋሙ በክልሉ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያስጀመረው የኦውቶሞቲቭ ፕሮጀክት ግንባታ በመፋጠን ላይ መሆኑም ተገልጧል ። የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሰማ ጫሊ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ባለፈው አመት በተጀመረው የፕሮጀክት ሀዋሳ ከተማ የሚገኘው የተቋሙን ዋና መስሪያ ቤት በዞን፣ በልዩ ወረዳና በወረዳ ደረጃ ካሉት 172 ቅርንጫፎች ጋር በኮምፒተር ኔት ወርክ የማያያዝ ስራ እየተካሄደ ነው፡፡ በተጨማሪ በሀዋሳ ከተማ የተጀመረው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ባለስድስት ፎቅ ህንጻ ግንባታ በመገባደድ ላይ እንደሚገኝና በሚቀጥለው ወር ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ አስረድተዋል፡፡ በክልሉ የ12 ቅርንጫፎች ባለሁለት ፎቅ ህንጻ ግንባታ በቅርቡ መጀመሩንና በ119 ንዑስ ቅርንጫፎች ከተጀመረው የቢሮ ግንባታ ውስጥም እስካሁን የ40ዎቹ ስራ ሲጠናቀቅ የቀሪዎቹ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ይከናወናል ብለዋል ። በየደረጃው ያሉት ሁሉም ቅርንጫፎ ቢሮዎችን በማሻሻል በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ የኮምፒተር ኔት

በሲዳማ ዞን በዘንድሮዉ የበጋ ወራት ከ38 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በመስኖ እየለማ ነው፡፡

አዋሳ ጥር 2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን በዘንድሮዉ የበጋ ወራት ከ38 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት ላይ የተለያዩ ሰብሎችና አትክልትና ፍራፍሬ እየለማ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ ። በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች በመስኖ እየለማ ካለዉ መሬት ከስድስት ሚልዮን ኩንታል የሚበልጥ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጧል ። በመምሪያ የመስኖ ልማትና ተቋማት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ማሞ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በሁለት ዙር በሚካሄደዉ የበጋ መስኖ ልማት ከ530 ሺህ የሚበልጡ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ ነዉ ። የመስኖ ልማቱ እየተካሄደ ያለዉ በየአካባቢው የሚገኙ ምንጮችን በማጎልበት፣ አነስተኛ ጉድጓዶችን በመቆፈር፣ ወንዞችን በመጥለፍና በቤተሰብ ደረጃ የኩሬ ውሃ በማሰባሰብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች እየተካሄደ ባለዉ የመስኖ ልማት እስካሁን ከ12ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአትክልትና ፍራፍሬ ፣በስራስርና በስራ ስርና በሌሎች ቋሚ ሰብሎች ተሸፍኗል ። ቀደም ሲል አብዛኛው የዞኑ አርሶ አደሮች የዝናብ ወቅትን ጠብቀዉ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በማምረት የድካማቸዉ ተጠቃሚ ሳይሆኑ መቆየታቸዉን አመልክተዉ በአሁኑ ጊዜ በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ በማምረት ኑሯቸዉን ማሻሻል ጀምረዋል ። በመልጋ ወረዳ፣ የጉጉማ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደሮች አቡሌ ክፍሌ እና መላኩ አበጀ ከሶስት ዓመታት በፊት እጅግ አስቸጋሪ የኑሮ ደረጃ ላይ እንደነበሩ አስታውሰዉ ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ በመጠቀም የመስኖ ልማት ከጀመሩ ወዲህ ኑሮአቸው እየተለወጠ ከመምጣቱም ባሻገር እስከ አገር አቀፍ ድረስ ሞዴል አርሶ አደር በመሆን ለሽልማት መብቃታቸውን ገልጸዋል፡፡

ለክብራን የሲዳማወራንቻ ብሎግ ኣንባቢያን በሙሉ

Image
ክብራን የሲዳማወራንቻ ብሎግ ኣንባቢያን ለኣንድ ወር ያህል ስራ ያቆምን መሆናችንን እና ከኣንድ ወር በኃላ በኣዳዲስ ዝግጅቶች የምንመለስ መሆናችንን እናስታውቃለን። እናመሰግናለን መልካም የገና በዓል !

የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ (ሲኣን) ኣዲሱ ኣመራር የሲኣንን የቀድሞ ዝና ለመመለስ እና የሲዳማ ህዝብ ፖለቲካዊ መብት መከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደምታገል ኣስታወቀ ፤ በቅርቡ ለምካሄደው የኣከባቢ ምርጫ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነው።

Image
የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ (ሲኣን) ኣዲሱ ኣመራር የሲኣንን የቀድሞ ዝና ለመመለስ እና የሲዳማ ህዝብ ፖለቲካዊ መብት መከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደምታገል ኣስታወቀ ፤ በቅርቡ ለምካሄደው የኣከባቢ ምርጫ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነው። ዝርዝሩን በምከተለው ሊንክ ያዳምጡ:: ለድምጽ ጥራት ማነስ ይቅርታ እንጠይቃለን!   ሲዳማ ተናገር የሬዲዮ ፕሮግራም