Posts

በሲዳማ ዞን በዘንድሮዉ የበጋ ወራት ከ38 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በመስኖ እየለማ ነው፡፡

አዋሳ ጥር 2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን በዘንድሮዉ የበጋ ወራት ከ38 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት ላይ የተለያዩ ሰብሎችና አትክልትና ፍራፍሬ እየለማ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ ። በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች በመስኖ እየለማ ካለዉ መሬት ከስድስት ሚልዮን ኩንታል የሚበልጥ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጧል ። በመምሪያ የመስኖ ልማትና ተቋማት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ማሞ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በሁለት ዙር በሚካሄደዉ የበጋ መስኖ ልማት ከ530 ሺህ የሚበልጡ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ ነዉ ። የመስኖ ልማቱ እየተካሄደ ያለዉ በየአካባቢው የሚገኙ ምንጮችን በማጎልበት፣ አነስተኛ ጉድጓዶችን በመቆፈር፣ ወንዞችን በመጥለፍና በቤተሰብ ደረጃ የኩሬ ውሃ በማሰባሰብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች እየተካሄደ ባለዉ የመስኖ ልማት እስካሁን ከ12ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአትክልትና ፍራፍሬ ፣በስራስርና በስራ ስርና በሌሎች ቋሚ ሰብሎች ተሸፍኗል ። ቀደም ሲል አብዛኛው የዞኑ አርሶ አደሮች የዝናብ ወቅትን ጠብቀዉ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በማምረት የድካማቸዉ ተጠቃሚ ሳይሆኑ መቆየታቸዉን አመልክተዉ በአሁኑ ጊዜ በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ በማምረት ኑሯቸዉን ማሻሻል ጀምረዋል ። በመልጋ ወረዳ፣ የጉጉማ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደሮች አቡሌ ክፍሌ እና መላኩ አበጀ ከሶስት ዓመታት በፊት እጅግ አስቸጋሪ የኑሮ ደረጃ ላይ እንደነበሩ አስታውሰዉ ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ በመጠቀም የመስኖ ልማት ከጀመሩ ወዲህ ኑሮአቸው እየተለወጠ ከመምጣቱም ባሻገር እስከ አገር አቀፍ ድረስ ሞዴል አርሶ አደር በመሆን ለሽልማት መብቃታቸውን ገልጸዋል፡፡

ለክብራን የሲዳማወራንቻ ብሎግ ኣንባቢያን በሙሉ

Image
ክብራን የሲዳማወራንቻ ብሎግ ኣንባቢያን ለኣንድ ወር ያህል ስራ ያቆምን መሆናችንን እና ከኣንድ ወር በኃላ በኣዳዲስ ዝግጅቶች የምንመለስ መሆናችንን እናስታውቃለን። እናመሰግናለን መልካም የገና በዓል !

የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ (ሲኣን) ኣዲሱ ኣመራር የሲኣንን የቀድሞ ዝና ለመመለስ እና የሲዳማ ህዝብ ፖለቲካዊ መብት መከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደምታገል ኣስታወቀ ፤ በቅርቡ ለምካሄደው የኣከባቢ ምርጫ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነው።

Image
የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ (ሲኣን) ኣዲሱ ኣመራር የሲኣንን የቀድሞ ዝና ለመመለስ እና የሲዳማ ህዝብ ፖለቲካዊ መብት መከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደምታገል ኣስታወቀ ፤ በቅርቡ ለምካሄደው የኣከባቢ ምርጫ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነው። ዝርዝሩን በምከተለው ሊንክ ያዳምጡ:: ለድምጽ ጥራት ማነስ ይቅርታ እንጠይቃለን!   ሲዳማ ተናገር የሬዲዮ ፕሮግራም

የሲዳማ ወጣቶች ንቅናቄ መግለጫ

Statement to Sidama youth movement On 2009, as we all know, the children of Sidama massacred by the current prime Minister of Ethiopia Haile Mariam Desalgn, at Awassa, Loque vicinity, Sidama state and the whole sidama population response to a massacre unprecedented in its nature and scale. On the occasion of the tenth anniversary of that uprising, the youth and students, the children, parents, teachers and other professionals; the workers in town, in commerce, industry and the farms; the religious community - in fact, the entire oppressed population together bound together by the blood that covered the streets of Awassa, the blood that has since soaked the soil of our motherland in even bigger quantities. On this truly historic occasion the nation will pay fitting tribute to the young heroes and martyrs. And so the repression we experience today is not new. But as we can see today the sacrifices of those heroes and martyrs were not in vain. The declaration of eviction of Sid

በሴቶች የፕሪምየር ሊግ ውድድር ሲዳማ ቡና ሩብ ፍፃሜ ገባ

Image
ሰኞ, 24 ታህሳስ 2012 11:05 በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ደደቢትና ሲዳማ ቡና ከየምድባቸው በበላይነት አጠናቀዋል። የምስራቅ ዞን ምድብ አሁንም መጨረሻው አልታወቀም።   ህዳር 29/2005 የተጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሴቶች ውድድር ሶስተኛ ሳምንት ቅዳሜና እሁድ ማለትም ታህሳስ 13 እና 14/2005 ቀጥሎ ተካሂዷል። በቅዳሜው ጨዋታ የማእከላዊ ዞን ምድብ አንድ ሁለት ጨዋታዎች ተከናውነዋል። በዚህም ደደቢት ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 በመርታት ምድቡን በዘጠኝ ነጥብ 1ኛ ሆኖ ያጠናቀቀበትን ውጤት ይዞ ወጥቷል። መብራት ሃይልን 3 ለ 1 የረታው ኢትዮጵያ መድህንም በ6 ነጥብ ሁለተኛ ሆኖ ሩበ ፍፃሜ መግባቱን አረጋግጧል። ኢትዮጵያ ቡናና መብራት ሃይል ከምድቡ ሳያልፉ ቀርተዋል። ቀሪ 4 ጨዋታዎች ደግሞ እሁድ ተከናውነዋል። በማዕከላዊ ዞን የምድብ ሁለት ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታድየም ሲከናወኑ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ውሃ ስራዎች ላይ ከደርዘን በላይ ግቦችን አስቆጥሯል። ንግድ ባንክ 14 ለ 0 የረታበት ጨዋታ በዘንድሮው ውድድር ከፍተኛ ግብ የተቆጠረበት ጨዋታ ሆኖ አልፏል። ከ14ቱ ግቦች ሽታዬ ሲሳይ በግሏ 7ቱን ግቦች ከመረብ ስታገናኝ፣ ረሂማ ዘርጋ 5ቱን በስሟ አስመዝግባለች። የሽታዬ ሲሳይ እህት የሆነችው ብዙነሽ ሲሳይ ደግሞ ቀሪዎቹን ሁለት ግቦች አስቆጥራለች። በዚህም መሠረት ሶስቱንም ጨዋታዎች በአሸናፊነት የተወጣው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምድቡን በበላይነት አጠናቋል። በዚሁ ምድብ እኩል የማለፍ እድል ይዘው ወደ ሜዳ የገቡት መከላከያና የቅ/ጊዮርጊስ 1 ለ 1 ተለያይተዋል። ሁለቱም 4 ነጥቦችን በመያዝ መከላከያ የተሻለ የግብ ክፍያ ስላለው ንግድ ባንክን ተከትሎ ግማሽ