የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኪሚቴ መደበኛ ስብሰባ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳተላለፍ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ ታሀሳስ 14/2005 የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኪሚቴ መደበኛ ስብሰባ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳተላለፍ ተጠናቀቀ፡፡ የግንባሩ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጸው የፌዴራል መንግስት ተቋማትን የ2005 የዕቅድ ዝግጅት ምዕራፍና ዋና ዋና የመንግሥትና የድርጅት ሥራዎችን በማስቀደም ነው የሁለት ቀናት ስብሰባውን የጀመረው፡፡ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከ2004 አፈጻጸም ግምገማ ከተለዩት ደካማና ጠንካራ የአፈጻጸም ውጤቶች በመነሳት የተካሄደውን የዕቅድ ዝግጅትና ፈፃሚ የማዘጋጀት ሂደት ፈትሿል፡፡ በዝግጅት ምዕራፍ ፈጻሚ የማዘጋጀት ሂደት ሦስቱንም የልማት ኃይሎች ማለትም የድርጅትን፣ የመንግስትንና ዋናው ፈጻሚና ተጠቃሚ የሆነውን የሕዝብ አቅም በዝርዝር ለይቶ ለመገንባት የተደረገው ጥረት ከወትሮው የተሻለ አፈጻጸም የታየበት እንደሆነ አረጋግጧል፡፡ በተለይም በእያንዳንዱ ዘርፍ ከተልዕኮው አንጻር ተጠቃሚ ወይም ተገልጋይ የሆነውን የሕዝብ ወገን በዝርዝር ለይቶ ቀጣይነት ያለውና በተጠያቂነት ላይ የተመሰረተ የተሳትፎና የግንኙነት ሥርዓት ለመገንባት የተጀመረው ጥረት መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና የመንግስትን አገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍና ለማረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ በእስካሁኑ የተሻለ ርቀት ከሄዱት ዘርፎች ልምድ በመነሳት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በአጽንኦት አሳሰቧል፡፡ በዝግጅት ሥራው ተመስርቶ በየዘርፉ የተከናወኑትን አባይት የልማት ሥራዎችን የፈተሸው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ፈጣኑ የኢኮኖሚ ዕድገት ይበልጥ ጤንነቱን ጠብቆ በመቀጠል ላይ መሆኑን ገምግሟል፡፡ የከተማውን ነዋሪ በተለይም አነስተኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል በመፈታተን ላይ የነበረው የዋጋ ግሽበት ቀደም ሲል ከ39 በመቶ በላ