Posts

በሃዋሳ ከተማ ስልጣንን ተገን በማድረግ ወንጀል የፈጸሙ የስራ ሃላፊዎች በእስራትና ገንዘብ ተቀጡ

አዋሳ ታህሳስ 12/2005 የሀዋሳ ከተማ ከንቲባና ማዘጋጃ ቤት ኃላፊ በነበሩበት ወቅት ስልጣናቸውን አለአግባብ በመጠቀም መሬት ለግለሰቦችና ድርጅቶች ሰጥተዋል በሚል የሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩ የከተማው ከንቲባና ሌሎች ስድስት ተከሳሾች በእስራትና ገንዘብ እንዲቀጡ ተወሰነ። የደቡብ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባስቻለው ችሎት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የነበረውን ሽብቁ ማጋኔን ጨምሮ 6 ተከሳሾች ላይ ከስምንት ዓመት እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ እስራትና ከ20ሺህ እስከ 2 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል። ፍርድ ቤቱ የክልሉ ጸረሙስና ኮሚሽን ይግባኝ በጠየቀባቸው ሽብቁ ማጋኔ፣ እንድርያስ ፉላሳ፣ ጸጋዬ አረጋ፣ ጉደታ ጉምቤ፣ አስራት ግቻሞና ከበደ ካያሞ ላይ የእስራትና ገንዘብ ቅጣቱን የወሰነው የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ በመሻር ነው። ግለሰቦቹ ለባለኮከብ ሆቴሎችና ከፍተኛ ኢንቨስትመንቶች ካልሆነ በቀር የመኖሪያ ቤት ቦታ መስጠት እንደማይቻል ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የተጻፈውን ዕገዳ በመጣስ ለግለሰቦች እንዲሁም ጋዜጠኞችን ጨምሮ በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ላልሆኑ ስምንት ሰዎች መሬት በመስጠታቸው ቅጣቱ ተጥሎባቸዋል ብሏል። በዚሁ መሰረት የሀዋሳ ከተማ የነበረው ሽብቁ ማጋኔ ላይ የአምስት አመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራትና የአምስት ሺህ ብር የገንዘብ መቀጫ ተጥሎበታል። የሃዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የመሬት ልማትና አስተዳደር የስራ ሂደት ባለቤት የነበረው እንድሪያስ ፉላሳና በማዘጋጃ ቤቱ የመሬት ልማትና አስተዳደር የስራ ሂደት ባለሙያ የነበረው ጉደታ ጉምቤ እያንዳንዳቸው በ5 ዓመት ከ6 ወር እስራትና በ15 ሺህ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። የታቦር ክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የመሬት ልማትና አስተዳደር ስራ ሂደት አስተባባሪ በነበረው አስራት ግቻ

በሀዋሳ ከተማ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመስማራት ከሃገር ውስጥም ሆነ ከውጪ የሚመጡ ባሀብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የከተማው አስተደደር አስታወቀ፡፡

Image
ባለፉት አራት አመታት በከተማው በባለሀብቶች በተከናወኑ የኢንቨስትመንት ስራዎች ከ23ሺህ በላይ ነዋሪዎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡ በሌላም በኩል የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ ባለሃብቶች በአጭር ጊዜ ወደ ስራ እንዲገቡ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል፡፡ የሀዋሳ ከተማ በሃገር አቀፍ ደረጃ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ከተሞች በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀስ ሲሆን ለዚህም እንደምክንያት የሚነሳው ለንግድ እንቅስቃሴ የምትመች መሆኑና የሃይቅዳር ከተማ መሆኗ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከተማዋን የቱሪስት መዳረሻ፣ የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ በተያዘው አመት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍ ገልፀዋል፡፡ በተለይ ይህን ስራ የበለጠ ማስኬድ እንዲቻል ከተማውን የማስተዋወቅ ስራ ትኩረት እንደተሰጠው አመልክተዋል፡፡ 4ኛው የከተሞች ሳምንት ተካሂዶ  ሃዋሳ ሁለት ዋንጫ በማግኘት አሸንፋ ከተመለሰች በሁዋላ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት ከሃገር ውስጥም ሆነ ከውጭ በርካታ ባለሃብቶች ጥያቄ እያቀረቡ እንዳለ አቶ ዮናስ ገልፀዋል፡፡ በዚህም የከተማ አስተዳደሩ የተሻሉ አሰራሮችን በመዘርጋት ባለሀብቶችን ለማስተናገድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ ባለፋት አራት አመታት ውስጥ ኢንቨስት ባደረጉ ባለሃብቶች ከ 23 ሺህ በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውንና ኢንቨስትመንት ይበልጥ በከተማዋ ለማስፋፋት ዘመናዊ ድረ ገጽ በመክፈት የማስተዋወቅ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል በተለያዩ ወቅቶች የኢንቨስትመንት ቦታ ወስደው ያላለሙ ባለሃብቶች እንዳሉ አረጋግጠናል ያሉት አቶ ዮናስ፣ 60 ባለሀብቶችን አሰተዳደሩ ወደ ልማት እንዲገቡ ማወያየቱንና ከስምምነት ላ

ለትምህርት ስርዓታችን ህልውና ከፖለቲካዊ ብልጠት ይልቅ ብልህነት ያሻል

  Written by  የተከበሩ አቶ ሙሼ ሰሙ ትምህርት ዜጎችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ በመቅረጽ ለራሳቸው፣ ለማህበረሰባቸውና ለሃገራቸው ጠቃሚ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያግዝ የእውቀት ማሸጋገርያ ስልት ነው፡፡ የትምህርት መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ መጣል ከጀመረ ከመቶ ዓመታት በላይ የተቆጠረ ሲሆን ከሁለተኛው አለም ጦርነት በፊት ትምህርት የሚሰጠው በመንግስትና በሃይማኖት ተቋማት ዙርያ ለአስተዳደራዊ ክህሎት፣ ለቀኖናና ለሃይማኖት እውቀት ሲባል እንደነበረ እ.ኤ.አ 2004 ላይ ዮኔስኮ የትምህርት ስርዓትን አስመልክቶ ባዘጋጀው ኮንፍረንስ ላይ የወጡ ዘገባዎች ይገልጻሉ፡፡ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የአፄ ሃይለ ስላሴ ስርዓት ዘመናዊ ትምህርትን በተደራጀ መልኩ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲሰጡ ሁኔታዎችን ያመቻቸ ቢሆንም የትምህርት ቤቶች እድገት ከማህበረሰቡም ሆነ ከሃይማኖት ተቋማት በገጠመው ተጽእኖ ምክንያት የመስፋፋቱ እድል አዝጋሚ ሆኖ ቆይቷል፡፡ የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል የተደረጉ ተከታታይ ጥረቶችም በወቅቱ ከተከሰተው ኢኮኖሚያዊ ቀውስና ድርቅ ጋር ተዳብለው ለአፄው ስርዓት ውድቀት ምክንያት ሊሆን ችሏል፡፡ ለደርግ በወቅቱ የነበረው አጣዳፊ ጉዳይ አብዮቱ በመሆኑ በመማርና ማስተማር ላይ የነበሩትን መምህራንና ተማሪዎች በነቂስ አሰልፎ አብዮቱን ለማስተዋወቅ በሚል ሰበብ ወደ እድገት በሕብረት የዕውቅትና የስራ ዘመቻ አዘመተ፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ እራሱን በጥቂቱም ቢሆን ማጎልበት የጀመረው የትምህርት ስርዓት ከባድ ፈተና ውስጥ ወደቀ፡፡ ከየመንግስት መስርያ ቤቱና ተቋማቱ ሁሉም ዓይነት ባለሙያዎች በወረንጦ እየተለቀሙ የማስተማር ሂደቱን በግድ እንዲቀላቀሉ ተደረገ፡፡ እዚህ ላይ የመምህርነትን ሙያ በፍቅር ሳይሆን በተጽእኖ እንዲቀበሉ የተገደዱ ግለሰቦች ምን ዓይነት ትውልድ

Ethiopia Combating Stunting in Children in Aleta-Wondo Woreda town of the Southern Regional State of Ethiopia

Image
BY Mekonnen Teshome Adugna Mitiku had never realized the advantage of giving colostrum to her children within an hour of their birth and also did not exclusively feed her breast in the six months after their birth, contrary to doctors’ advice to help them physically and mentally develope. Adugna (Right) and her daughter Meron embracing her ten-month old son Rather Adugna, a resident in 04 Dela Kebele of the Aleta-Wondo Woreda town of the Southern Regional State of Ethiopia, spilled out the colostrum before feeding breast her daughters as she thought it was something unclean and unpleasant for them to take against the teaching of health professionals. She also gave her babies Hamessa, juice of a “medicinal” plant that usually affects newborn babies’ kidney, with in few hours of their birth thinking that it would make the newly born babies strong and healthy according to the tradition of her society. She also didn’t start complementary food when they get six months old

የጋዜጠኞች መገደል

Image
ሃያ-ስምንት የኤርትራ ጋዜጠኞች በዳርዊሽ ቋንቋ «የማያዉቁትን ፈንጂ ረግጠዉ» ከማይታወቅ ሥፍራ ከተከረቸሙ ዓመታት አልፏቸዋል።ዳ ብዙ ኢትዮጵያዉያን ጋዜጠኞች እስር ቤቶችን ተመላልሰዉባቸዋል። ዉብሸት ታዬ፥ ርዕዮት ዓለሙ፥ እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም ዛሬም በየወሕኒ ቤቱ ይማቅቋሉ። 19 12 12 የተገባደደዉ የጎርጎሮሳዉያኑ ዓመት 2012 ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ጋዜጠኞች የተገደሉበት፥ በርካቶች የታሠሩ ወይም የተንገላቱበት ዓመት እንደሆነ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች አስታወቁ።ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች የተሰኘዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅትና ሌሎች ተቋማት እንዳስታወቁት የግብፅ ሕዝባዊ አብዮት፥ የሶሪያዉ ጦርነት፥ የሶማሊያ ግጭት ለበርካታ ጋዜጠኞች ሞት ምክንያት ሆኗል።እንደ ጎሮጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ከ1995 ወዲሕ በአንድ ዓመት ዉስጥ በርካታ ጋዜጠኞች ሲገደሉ ዘንድሮዉ ከፍተኛዉ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ አጭር ዘገባ አለዉ። «ሶሪያ ዉስጥ ጋዜጠኛ መሆን ፈንጂ በፈሰሰበት ምድር እንደመራመድ ነዉ።ብዙ የማይነኩ ነገሮች አሉ።አንዳዶቹ ለምሳሌ ፖለቲካዊ፥የሰብአዊ መብቶች ወይም የሥርዓቱ ባሕሪያት የመሳሰሉት ርዕሶች በግልፅ ይታወቃሉ።ሌሎች ደግሞ ቀይ መስመራቸዉ የማይታወቅ ግን አይነኬ ብዙ ጉዳዮች አሉ።እና ፈንጂዉን መቼ እንደምትረገጠዉ፥መቼ እንደሚፈነዳም የሚያዉቅ የለም» ብሎ ነበር። ሶሪያዊዉ ጋዜጠኛ ማዘን ዳርዊሽ፥-ሐቻምና መጋቢት። ዳርዊሽ ፈንጂዉን እንዴት እንደረገጠዉ በርግጥ የሚያዉቅ የለም።ብቻ ፈነዳ። ግን አልገደለዉም። ካልታወቀ ስፍራ-አሳሰረዉ እንጂ።ዳርዊሽ የዘንድሮዉን የድንበር የለሽ ዘጋቢዎችን ሽልማትን አግኝቷል። ሕይወትን ለሙያ ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች እንደሚለዉ ሃያ-ስምንት የኤርትራ ጋዜጠኞች በዳርዊሽ ቋንቋ «የማያዉቁትን ፈንጂ ረግጠዉ» ከማይታወቅ ሥፍ