Posts

33 የፖለቲካ ድርጅቶች በምርጫ ስም ገንዘብ ማባከን እንዲቆም ጠየቁ

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቶቹ ባወጡት መግለጫ በጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአዳማ ኤክስኪዩቲቭ ሄቴል በዚህ አመት በሚደረገው የአካባቢ እንዲሁም የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ ምርጫ የግዜ ሰሌዳን አስመልክቶ  የውይይት መድረክ መጥራቱን ጠቅሰዋል። ድርጅቶቹ በመግለጫቸው ” ምርጫ ለማካሄድ ነባራዊ ሁኔታው የማይፈቅድ ስለሆነ በፖለቲካ ምህዳሩና በህዝብ ወሳኝነት ሁሪያ መወያየት አለብን ብለን ፒቲሺን ተፈራርመን ለቦርዱ ያስገባን 33 ፓርቲዎች ጉዳይ ወደ ጎን ተትቶ ቀልድ በሚመስል መልክ በጾታ ጉዳይ ልናወያያችሁ እንፈልጋለን ማለት የህዝብን የምርጫ ባለቤትነት የሚጋፋ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል።” ካሉ በሁዋላ፣ ቦርዱ ጾታን በተመለከተ እና አሁን ላለንበት ሁኔታ ቀላል የሆነ ጉዳይ ጠቅሶ በጠራው የፖለቲካ ፓርቲዎች የውይይት  መድረክ የማንሳተፍ መሆናችንን ፔቲሺን የፈረምን 33 የፖለቲካ ፓርቲዎች እናሳውቃለን።” ብለዋል። 33ቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ምርቻ ቦርድ በገለልለተኛ ወገኖች እንዲቋቋም፣ ነጻና ፍትሀዊ የመገናኛ ብዙሀን እንዲኖሩ፣ የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ሁሉንም ድርጅቶች በእኩል እንዲያገለግሉ፣ መከላከያ፣ ፖሊስና የደህንነት ተቋማት በነነጻነት እንዲዋቀሩ፣ በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርሰው ማዋከብ እንዲቆም የሚሉና ሌሎችንም በርካታ ጥያቄዎች መጠየቃቸው ይታወሳል።

ፕላምፕኔት የተሰኘውን ምግብ ለገበያ ያቀረቡ የንግድ ተቋማት እርምጃ ተወሰደባቸው

Image
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ የምግብ እጥረት ላጋጠማቸው ህጻናት በነጻ የሚሰጠውን "ፕላምፕኔት" የተሰኘ ምግብ ለገበያ ባቀረቡ 25 የንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ ነው። ምግቡን መንግስት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ከፍተኛ ወጪ እያደረገበት ለታለመላቸው ህጻናት እንዲደርስ የሚያደርግ ሲሆን ፥ የሚቀርበውም በጤና ተቋማት በኩል በነጻ እና በባለሙያ ትዕዛዝና ክትትል ብቻም ይሰጣል። ይሁን እንጂ በሃዋሳ ከተማ ይህ ህይወት አድን ምግብ ከታለመለት ዓላማ ውጪ እየዋለ መሆኑን ፥ በመምሪያው የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ስርዓት ቁጥጥር ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ዘመን ለገሰ ተናግረዋል። በተለያዩ መንገዶች ከየጤና ተቋማቱ እየወጣ ለንግድ እየቀረበ በመሆኑ ፥ ዛሬን ጨምሮ ሰሞኑን መምሪያው ይህን ምግብ ለገበያ በሚያቀርቡ የንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ተገዷል። አቶ ዘመን እንዳሉት ወደ እርምጃ የተገባው በተለያዩ መንገዶች በተደጋጋሚ ፥ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ቢሰጥም ለውጥ ሊመጣ ባለመቻሉ ነው። አስቀድሞ እርምጃ ተወስዶባቸው ዳግም ወደ ህገ ወጥ ስራው ላለመግባት ፥ መተማመኛ ፈርመው የንግድ ተቋሞቻቸው የተከፈቱላቸው እንዳሉም ነው ያስረዱት። በዚህ ህገ ወጥ ስራ ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጥረው በፍርድ ሂደት ላይ የሚገኙ ሁለት የህክምና ባለሙያዎችም አሉ ነው ያሉት አተ ዘመን። ከጉዳዩ አሳሳቢነት አንጻር የጤና መምሪያው በከተማዋ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮን ጨምሮ ፥ ዘጠኝ ያህል ባለድርሻ አካላትን ያካተተ የህብረተሰብ ጤና ተቆጣጣሪ ግብረ ሃይል ማቋቋሙን በዛብህ ማሞ ዘግቧል።

በመጪው ሚያዝያ ለሚካሄደው ምርጫ የምርጫ ቁሳቁሶች ሊከፋፈል ነው

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 5/2005(ዋኢማ)   - በመጪው ሚያዝያ 6 እና 13 ለሚካሄደው የአካባቢና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች ምርጫ የምርጫ ቁሳቁሶችን ከዛሬ ጀምር ማሰራጨት እንደሚጀምር የምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ ወይዘሮ የሺ ፍቃዱ ዛሬ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ ለምርጫው የሚያስፈልጉ የምርጫ ቁሳቁሶችን ቦርዱ በማዘጋጀት በሚቀጥሉት ሁለትና ሶስት ቀናት ለሁሉም ክልሎች ለማሰራጨት ዝግጅቱን አጠናቋል። ቦርዱ ካሁን በፊት የመራጮች መመዝገቢያና የምርጫ ካርዶችን በአማርኛ ብቻ ያሳትም እንደነበረ ጠቁመው፤ በዘንድሮው ምርጫ ግን ከአማርኛው በተጨማሪ  በኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ አፋርኛና ሶማሊኛ ቋንቋዎች ማዘጋጀቱን ገልፀዋል። የዘንድሮው ምርጫ ፍትሀዊነቱ የተረጋገጠ ለማድረግም ለባለድርሻና ለአስፈፃሚ አካላት ስልጠና መሰጠቱን ተናግረው፤ በቅርቡም ከ100 በላይ ለሚሆኑ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ስልጠና እንደሚሰጥ ወይዘሮ የሺ ገልፀዋል። ምርጫውን በእውቀት ላይ የተመሰረተ ለማድረግም በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በተለያዩ ቋንቋዎች ትምህርት በመሰጠት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። የምርጫ ክልል የምርጫ አስፈፃሚዎችን የመመልመሉ ስራም መጠናቀቁን ጠቁመው፤ በዚህም 2ሺ የሚሆኑ አስፈፃሚዎች በቋንቋቸው ስልጠና እንዲወስዱ ተደርጓል ብለዋል። የምርጫ አስፈፃሚዎች ገለልተኛ እንዲሆኑ ጥረት እየተደረገ ነው ያሉት ወይዘሮ የሺ የስራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት እንዲኖራቸው በተለይም የሴቶችና የወጣቶች ተሳትፎ ከባለፈው ምርጫ የተሻለ እንዲሆን ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል። እንደ ወይዘሮ የሺ ገለፃ የመራጮችና የእጩዎች ምዝገባ ቦርዱ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከታህሳስ 22 ጀምሮ እንደሚካሄድ

የመጠለያ እጥረትና የጋራ መኖሪያ ቤት ተስፋ በሐዋሣ

Image
በአስፋው ብርሃኑ ልዩ ዘጋቢ ከሐዋሣ ሐዋሣ ከተማ በ1952 ዓ.ም. ስትቆረቆር የነዋሪዎቿ ቁጥር ከ2,500 አይበልጥም ነበር፡፡ ኀዳር 2003 ዓ.ም. የአምሳኛ ዓመት ልደቷን ስታከብር የሕዝቧ ቁጥር ከሦስት መቶ ሺሕ በላይ የደረሰ ቢሆንም ፈጣን የሕዝብ ቁጥር ዕድገት የተከሰተው ባለፉት አሥር ዓመታት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በአገራችን በፍጥነት እያደጉ ከመጡት ከተሞች ግንባር ቀደም የሆነችው ሐዋሣ ዛሬ አራት መቶ ሺሕ ለሚገመት ሕዝቧ መጠለያ እያጠራት ከመሆኑም በላይ “ለመኖሪያ የተመቸች” መባሏን ተከትሎ እንዲሁም የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴዎች መጐልበት በርካታ ዜጐች እንዲፈልሱ አስችሏል፡፡ መሰል ሁኔታ የመኖሪያ ቤት እጥረትንና የአንድ ክፍል ወርሃዊ ኪራይ ንረትን አስከትሏል፡፡ የከተማዋ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመቅረፍ የአገራዊ ፖሊሲ አካል የሆነውን የጋራ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እያደረገ ቢሆንም እጥረቱና የኪራይ ንረቱ ዛሬም ለሐዋሣ ነዋሪዎች የኑሮ ውድነቱ አካል ሆኗል፡፡  የሕዝብ ቁጥር ዕድገትና የመጠለያ እጥረት  ሐዋሣ የክልሉ መንግሥትና የሲዳማ ዞን አስተዳደር መቀመጫ መሆንዋ፣ የመሠረተ ልማት አውታሮች ግንባታ ፕሮጀክቶች መስፋፋት፣ የንግድና የቢዝነስ እንቅስቃሴዎች መበራከት የግልና የመንግሥት የትምህርት ተቋማት መንሰራፋትና ሌሎች ተያያዥ ነገሮች ለሐዋሣ ለፈጣኑ የሕዝብ ቁጥር ዕድገት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ለቢዝነስ፣ ለትምህርትና ለሥራ ጉዳይ ወደ ሐዋሣ የመጣ ዜጋ ቡና ቤት አይኖርምና ቋሚ መጠለያ ይፈልጋል፡፡ ያለው አማራጭ ከተገኘ የቀበሌ (ዕድለኛ ከሆነ) እና የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተከራይቶ መኖር ነው፡፡ ይሁንና በአጭር ጊዜ ውስጥ የአንድ ክፍል ኪራይ ዋጋ አቅም የሌላቸውን በየወሩ ቤት እንዲቀያይሩ እ

Protection of agri-food names in Africa, Sidama Coffee is among 19 covered products

Image
The European Commission signed, on 26 November, in Zanzibar, Tanzania, a cooperation agreement with the African Regional Intellectual Property Organisation (ARIPO) to improve the protection of traditional agricultural products (geographical indications or GIs) in Africa. This will involve, among other matters, promoting the GI legal framework, informing producers and other stakeholders and enhancing the public’s awareness of GIs and their potential for African producers.  The agreement has a non-legally binding status and covers 19 product names: Zanzibar cloves (clous de girofles) from Tanzania, Rift Valley coffee from Tanzania, Sidamo coffee from Ethiopia, Rooibos from South Africa, Karoo lamb from South Africa, Beurre de karité du plateau Massif from Burkina Faso, Miel blanc d’Oku from Cameroon, Poivre blanc de Penja from Cameroon, Shama shea butter from Ghana, Ghana fine flavour cocoa, Café Diama from Guinea, Rwanda mountain coffee, Mount Kenya roses from Kenya, Ngoro Ngoro