Posts

በኢትዮጵያ ''ሃሎ ዶክተር'' የተሰኘ የምክር አገልግሎት መስጫ አገልግሎት ተጀመረ

አዲስ አበባ ታህሳስ 8/2005 በኢትዮጵያ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ሕሙማን ከሐኪሞች ምክር የሚያገኙበት ''ሃሎ ዶክተር'' የተሰኘ አገልግሎት በይፋ ተጀመረ። አገልግሎቱ በኦሮምኛ፣በትግሪኛና በሶማሊኛ ቋንቋዎች ለመጀመርም ታቅዷል። የቴሌ ሜዲስን የሕክምና አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ዮሐንስ ወዳጄ ዛሬ ለኢ ዜ አ እንዳስታወቁት ለ24 ሰዓት የሚሰጠው አገልግሎት በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ሆነው ምክር የሚፈልጉ ሕሙማንን ለመርዳት ያስችላል። በተጨማሪም ቤታቸው ሆነው የሐኪም ድጋፍ የሚፈልጉ ሕሙማንን እንደሚያግዝም አስረድተዋል። እንዲሁም በሕመም ወይም በአደጋ ለተጎዱ ሰዎች የአምቡላንስ አገልግሎት በማቀናጀት እገዛ እንደሚያደርግ ዶክተር ዮሐንስ አስታውቀዋል። ''ሕሙማን ካሉበት ሆነው በሞባይል ስልካቸው አማካይነት ወደ 8896 መደወል የሐኪም ምክር ሲጠይቁ በመሥመር ላይ ያለው ሐኪም ከሕመማቸው እንዲፈወሱ ተገቢውን ምክር በመስጠት ይረዳቸዋል።ለዚህም ከስልካቸው ሂሳብ ተቀናሽ የሚሆን መጠነኛ ሂሳብ ይቆረጣል'' ሲሉም አብራርተዋል። በአገሪቱ የሞባይል አገልግሎት መስፋፋትና የወደፊት አቅጣጫው አገልግሎቱን ለማስጀመር ጥሩ መሠረት እንደሆነም ዋና ሥራ አስኪያጁ አመልክተዋል። አገልግሎቱ ለጊዜው በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች በ10 ሐኪሞች መጀመሩንም ተናግረዋል።በያዝነው ዓመትም የሐኪሞቹን ቁጥር ወደ 50 ለማሳደግ መታቀዱን ገልጸዋል። አገልግሎቱን በኦሮምኛ፣በትግሪኛና በሶማሊኛ ቋንቋዎች ለመጀመርም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። አገልግሎቱ ቀደም ሲል በአውሮፓና በአሜሪካ፣በቅርቡ ደግሞ በደቡብ ምሥራቅ አገሮችና በላቲን አሜሪካ እንዲሁም በአፍሪካ እየተስፋፋ መምጣቱን ዶክተር ዮሐን

የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ፈተናዎችና የሦስቱ ተዋንያን ሚና ሲገመገም

Image
በጋዜጣው ሪፖርተር የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት  በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የጀመረውን ውይይት ኅዳር 30 ቀን 2005 ዓ.ም. አስቀጥሎ ነበር፡፡ በተጠቀሰው ቀን ያካሄደው የውይይት ርዕስ ‹‹ወቅታዊው የአገራችን የፖለቲካ ሁኔታና የፖለቲካ ፓርቲዎች የመሰባሰብ ሚና›› የሚል ነበር፡፡ በዚህ ውይይት ላይ የፓርቲው የፖለቲካ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙላቱ ጣሰው ለፓርቲው አባላት የመወያያ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ እሳቸው በኢትዮጵያ ሁሉም ዓይነት የዜጎች መብቶች የሚከበሩበትና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል የሚኖርበት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት፣ ባለፉት ዓመታት በተከታታይ የተደረጉት ጥረቶች ሁሉ ውጤት አላመጣም ይላሉ፡፡ በውይይቱ ላይ እነዚህ ሁሉ ጥረቶች ለምን ለውጥ እንዳላመጡ አቶ ሙላቱ ሲያብራሩ፣ ሦስት ተዋናዮችን በተወሰነ ደረጃ መመልከት አስፈላጊ መሆኑን በመጠቆም ማስረዳታቸውን ቀጠሉ፡፡ ሦስቱ ተዋንያን የተባሉት ገዥው ፓርቲ፣ ተቃዋሚዎችና ሕዝብ ናቸው፡፡ ገዥው ፓርቲ ገዥውን ፓርቲ (ኢሕአዴግ) ከትናንት እስከ ዛሬ ብለው አጠር አድርገው በተነተኑበት ክፍል የራሱን አገር አስገንጥሎ ዕውቅና የሰጠ፣ የአገሪቱን የባህር በር የዘጋ፣ የአገሪቱን ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ፣ የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅሞች አሳልፎ የሰጠና ፍትሐዊ የሀብት ክፍል የሌለበት አምባገነናዊ ሥርዓት ማስፈኑን፣ በጦርነት ወቅት የወረሳቸውን ንብረቶችና ሀብቶች በእጁ ይዞ የፓርቲ ኩባንያዎችን እያስፋፋ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ‹‹የገዥው ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የአገሪቱን ሀብት በመቆጣጠር ላይ ናቸው፡፡ አገራችን ከበቂ በላይ ለም መሬትና ዓመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች እያሏት፣ በምግብ ሰብል ራሳችንን ባለመቻላችን ሕዝባችን ለከፍተኛ ረሃብ ተዳርጓል፤›› ያሉት አቶ ሙላቱ

ፓርላማው መደበኛ ስብሰባዎቹን እያካሄደ አይደለም

-    ከ18 መደበኛ ስብሰባዎች ስድስቱን ብቻ ተሰብስቧል በዮሐንስ አንበርብር በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት የሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑን የጀመረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በሳምንት ሁለት ጊዜ ማክሰኞና ሐሙስ ማካሄድ የሚገባውን መደበኛ ስብሰባዎች በአብዛኛው አላካሄደም፡፡ በምክር ቤቱ የአሠራር ሥነ ሥርዓት ደንብ መሠረት የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባዎች በሳምንት ሁለት ጊዜ መካሄድ ይገባቸዋል፡፡ በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ ሥራውን ከጀመረበት የመስከረም ወር መጨረሻ አንስቶ እስከ ታህሳስ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ድረስ 18 መደበኛ ስብሰባዎች መካሄድ ነበረባቸው፡፡ ይሁን እንጂ እስካሁን ያደረገው ስድስት መደበኛ ስብሰባዎችን ብቻ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በምክር ቤቱ ከሁለት ሳምንት በፊት ተገኝተው ያፀደቁት አዲስ የካቢኔ አወቃቀርና የሚኒስትሮች ሹመት የመጨረሻው ወይም ስድስተኛው መደበኛ ስብሰባው ነበር፡፡ ኅዳር 20 ቀን 2005 ዓ.ም. ከተካሄደው ከዚህ መደበኛ ስብሰባ በኋላ እንኳን አራት የመደበኛ ስብሰባ ቀናት ቢኖሩትም፣ “ዛሬ ይካሄድ የነበረው መደበኛ ስብሰባ የማይካሄድ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እንገልጻለን” የሚሉ ማስታወቂያዎችን የምክር ቤቱ አባላት መኖሪያዎች አካባቢ በሚገኙ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ እንዲሁም በምክር ቤቱ ሰሌዳዎች ላይ በመለጠፍ የመደበኛ ስብሰባ ፕሮግራሞቹን መዝለል የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡ የምክር ቤቱ ዋና ሥልጣንና ተግባሮች የሚቀርቡለትን ረቂቅ አዋጆች ተወያይቶ ማፅደቅና አስፈጻሚውን ወይም ራሱ የሚያመነጫቸውን የመንግሥት አካላት መቆጣጠር ናቸው፡፡ እስካሁን ካካሄዳቸው ስድስት መደበኛ ስብሰባዎች መካከል የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የዚህን ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሥራ ዘመን

ፌዴራል ፖሊስ አገሪቱን በስለላ ካሜራዎች ለማጥለቅለቅ አቅዷል

ታህሳስ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የፌዴራል ፖሊስ ከሁለት ዓመት በፊት በአዲስአበባ ተክሎ ሥራ ላይ ያዋላቸው የስለላ ካሜራዎች (cctv ካሜራዎች) ውጤታማ በመሆናቸው ወደክልሎች ለማስፋፋት ማቀዱን አስታወቀ፡፡ ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው በኢትዮጵያ የፖሊስ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስአበባ ዋናዋና መንገዶች ላይ ካሜራዎችን በመግጠም የመቆጣጠሪያ ክፍል በማቋቋም በመንገዶቹ ላይ የሚሰሩ ሕገወጥ ድርጊቶችንና የትራፊክ አደጋዎችን በአነስተኛ የፖሊስ ኃይል ያለብዙ ወጪና ድካም ለመቆጣጠርና ጸጥታ ለማስከበር መቻሉን ይጠቅሳል፡፡ ይህንኑ ቴክኖሎጂ በከተማውና በክልሎች ለማስፋፋትና ተጨማሪ ሥራ እንዲያከናውን ለማድረግ ተከታታይ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን መረጃው ጠቅሶ ፣ “ተጨማሪ ሥራዎች” ያላቸውን ስራዎች ግን ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡ በሚሊየን ዶላር ወጪ በአዲስአበባ ከተማ የተተከሉት እነዚሁ ዘመናዊ ካሜራዎች ዋንኛ ጥቅማቸው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ዜጎችን ለመሰለል ካለው ጥልቅ ፍላጎት ጋር የተያያዘ መሆኑን በመግለጽ መንግስት ለሕዝብ የሚያስብ ቢሆን ኖሮ ገንዘቡን ድህነትንና የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ ባዋለው ነበር ሲሉ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቃውሞ አሰምተው እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በተያያዘ ዜና ፌዴራል ፖሊስ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመታገዝ የሚፈጸሙ የሳይበር ወንጀሎችን ለመከታተልና አጥፊዎችን ለመያዝ ቢሮ ከፍቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ(ICT) በመደገፍ የሚሰሩ ወንጀሎች(ሳይበር ክራይም) አሳሳቢ እየሆኑ በመምጣታቸው ወንጀሎችን ለመከታተል፣ለመመርመርና ለማጣራት፣አጥፊዎችንም ለፍርድ ለማቅረብ በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ በፎረንሲክ ዳይሬክቶሬት ስር የሳይበር ላብራቶሪ ተቋቁሟል፡፡ላብራቶሪ

የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ዛሬና ነገ ይቀጥላል

Image
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እግር ኳስ ውድድር ዛሬና ነገ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተሞች ይቀጥላል። ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመከላከያ በ9 ሰዓት ፥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት በ11 ሰዓት ይጫወታሉ። ውድድሩ ነገ ቀጥሎ ፥ ደደቢት ከኢትዮጵያ መድን ፣ መብራት ኃይል ከኢትዮጵያ ቡና በ9 እና በ11 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታድየም ይጫወታሉ። አዳማ ላይ አዳማ ከነማ  ድሬዳዋ ከነማን ሃዋሳ ላይ ደግሞ ሃዋሳ ከነማ ሲዳማ ቡናን ያስተናግዳሉ። አርባ ምንጭ ከነማ የሳምንቱ አራፊ ቡድን እንደሚሆን አራያት ራያ ዘግባለች።