ፓርላማው መደበኛ ስብሰባዎቹን እያካሄደ አይደለም
- ከ18 መደበኛ ስብሰባዎች ስድስቱን ብቻ ተሰብስቧል በዮሐንስ አንበርብር በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት የሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑን የጀመረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በሳምንት ሁለት ጊዜ ማክሰኞና ሐሙስ ማካሄድ የሚገባውን መደበኛ ስብሰባዎች በአብዛኛው አላካሄደም፡፡ በምክር ቤቱ የአሠራር ሥነ ሥርዓት ደንብ መሠረት የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባዎች በሳምንት ሁለት ጊዜ መካሄድ ይገባቸዋል፡፡ በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ ሥራውን ከጀመረበት የመስከረም ወር መጨረሻ አንስቶ እስከ ታህሳስ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ድረስ 18 መደበኛ ስብሰባዎች መካሄድ ነበረባቸው፡፡ ይሁን እንጂ እስካሁን ያደረገው ስድስት መደበኛ ስብሰባዎችን ብቻ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በምክር ቤቱ ከሁለት ሳምንት በፊት ተገኝተው ያፀደቁት አዲስ የካቢኔ አወቃቀርና የሚኒስትሮች ሹመት የመጨረሻው ወይም ስድስተኛው መደበኛ ስብሰባው ነበር፡፡ ኅዳር 20 ቀን 2005 ዓ.ም. ከተካሄደው ከዚህ መደበኛ ስብሰባ በኋላ እንኳን አራት የመደበኛ ስብሰባ ቀናት ቢኖሩትም፣ “ዛሬ ይካሄድ የነበረው መደበኛ ስብሰባ የማይካሄድ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እንገልጻለን” የሚሉ ማስታወቂያዎችን የምክር ቤቱ አባላት መኖሪያዎች አካባቢ በሚገኙ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ እንዲሁም በምክር ቤቱ ሰሌዳዎች ላይ በመለጠፍ የመደበኛ ስብሰባ ፕሮግራሞቹን መዝለል የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡ የምክር ቤቱ ዋና ሥልጣንና ተግባሮች የሚቀርቡለትን ረቂቅ አዋጆች ተወያይቶ ማፅደቅና አስፈጻሚውን ወይም ራሱ የሚያመነጫቸውን የመንግሥት አካላት መቆጣጠር ናቸው፡፡ እስካሁን ካካሄዳቸው ስድስት መደበኛ ስብሰባዎች መካከል የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የዚህን ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሥራ ዘመን